በ MCPS ቀጣይ ትምህርት እየተጀመረ ነው

የተወደዳችሁ ወላጅች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

ሰኞ፣ ማርች 30 የመጀመሪያውን ምእራፍ/first phase የኦንላይን ትምህርት ፕሮግራም እንጀምራለን። የትምህርት ቤቶቻችን ህንጻዎች እስከ ኤፕሪል 24 በ MCPS ቀጣይ ትምህርት እየተጀመረ ነው

የተወደዳችሁ ወላጅች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

ሰኞ፣ ማርች 30 የመጀመሪያውን ምእራፍ/first phase የኦንላይን ትምህርት ፕሮግራም እንጀምራለን። የትምህርት ቤቶቻችን ህንጻዎች እስከ ኤፕሪል 24 ዝግ ቢሆኑም፣ የተማሪዎቻችንን አካደሚያዊ እና አካደሚያዊ ያልሆኑ ፍላጎቶችን ምላሽ ለመስጠት ትምህርት የሚቀጥልበትን እቅድ በማዘጋጀት  (ከቤት/የርቀት ትምህርት = remote/distance learning) ለማመቻቸት ሠራተኞቻችን ለሣምንታት በትጋት ሲሠሩ ቆይተዋል።

እንደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ያለ ትልቅ የትምህርት ሲስተም ውስጥ የርቀት ትምህርት እቅድ መዘርጋት ቅንጅት፣ ትብብር፣ ስልጠና እና የተግባር ልምምድ ይጠይቃል። ሠራተኞች እና ተማሪዎች በአዲስ እና ያልተለመዱ ሁኔታዎች እንዲያስተምሩ እና እንዲማሩ እየተጠየቁ ናቸው። ሲሥተሙ የተሟላ/እንከንየሌሽ እንደማይሆን በመረዳት እያስተካከልን እንደምንቀጥል እርስበርሳችን ትእግስት እንዲኖረን እና እንድንገነዘብ ያስፈልጋል።

በመጀመሪያው ሣምንት የመጀመሪያ ምእራፍ/phase one የርቀት ትምህርት (ማርች 30 - ኤፕሪል 3)፣ የሚከናወገው፦

 1. ተማሪዎችን እና መምህራንን እንደገና ማገናኘት
 2. ተማሪዎች በኦንላይን ትምህርት ለመሣተፍ መቻላቸውን እና በኦንላይን መሣሪያዎች/online tools መጠቀም እና ስራዎቻችውን/assignments ማቅረብ መቻላቸውን ማረጋገጥ
 3. ሠራተኞች ተፈላጊውን የርቀት ትምህርት ለተማሪዎች በጥራት ለማቅረብ አስፈላጊ ሙያዊ እውቀት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ
 4. ተማሪዎች እቤት ውስጥ መቼ በትምህርት ላይ እንደሚሆኑ መርሃግብር ለማዘጋጀት ቤተሰቦችን መርዳት
 5. 3ኛውን የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የማጠናቀቅ ሥራዎችን/assignments መሥራት

የርቀት ትምህርት እቅዶች የተዘጋጁት ተማሪዎች በህንጻዎቻችን ውስጥ ሆነው እንደሚማሩት አንድ አይነት አቀራረብ ሞዴል እንዲሆን ታስቦ አለመሆኑን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው። የእኛ የርቀት ትምህርት ፕላን፣ በአስተማሪዎች የሚቀርብ ትምህርትን፣ ራስ ችሎ ለብቻ መማርን፣ እድሜን የሚመጥን፣ በራስ ጥረት መሥራትን፣ እና ውጤት የተሰጠባቸው ስራዎችን/assignments ማቅረብን አጠቃሎ ይሰጣል። ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እና ለቤተሰቦች እንደሁኔታው የሚለወጥ/የሚቀየር እና የተዋቀረ አሠራር እንሰጣለን። ሁላችንም ⸺ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ እና ሠራተኞች በጋራ ⸺ከርቀት ትምህርት ሁኔታ ጋር እየተለማመድን ስንሄድ ደረጃ በደረጃ ይህንን ሥራ እንገነባለን።

ምን እንደሚጠበቅ (ለኤለመተሪ ተማሪዎች ወላጆች እና ሞግዚቶች)
ሰኞ፣ ማርች 30፣ ማክሰኞ፣ ማርች 31 እና ረቡእ፣ ኤፕሪል 1፣እርስዎ እና ልጅዎ፦

 1. myMCPS Classroom and Google Classroom በመጠቀም ኦንላይን ሪሶርሶችን እና ቱቶሪያሎችን ማሰስ ትችላላችሁ።  ሰኞ፣ ማርች 30፣ ማክሰኞች፣ ማርች 31 እና ረቡእ፣ ኤፕሪል 1 በማንኛውም ሠዓት እነዚህን ዳሰሳዎች ማድረግ ይቻላል። የእነዚህ ኦንላይን ሪሶርሶች እና ቱቶሪያል አገናኝ-ሊንኮች ሰኞ፣ ማርች 30 ጠዋት ቀጣይ ትምህርት ድረ-ገጽ/Continuity of Learning website በወላጆች እና ተማሪ ሰክሽን ላይ ይገኛል።
 2. ረቡእ፣ ኤፕሪል 1፣ የእርስዎ ልጅ--፦
 3. ሐሙስ፣ ኤፕሪል 2 ከክፍል ተማሪዎች ጋር በሚኖረው የስብሰባ ወቅት አስተማሪያቸው ያነጋግራቸዋል-ታነጋግራቸዋለች።

ከረቡእ፣ ኤፕሪል 1 ጀምሮ እና እስከ ሣምንቱ መጨረሻ ድረስ፣ ኬዝ ማኔጀሮች እና የስፔሻል ኢጁኬሽን አስተማሪዎች ከተማሪዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ። የ ESOL አስተማሪዎች፣ ካውንስለሮች፣ የተማሪዎችን ሠራተኞች፣ ረዳት አስተማሪዎች/paraeducators እና ሌሎች ሠራተኞች እንደዚሁ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።
ሐሙስ፣ ኤፕሪል 2 ፣ የእርስዎ ልጅ፦

 1. ከአስተማሪው(ዋ) ጋር የመጀመሪያውን በመማሪያ ክፍል የተዘጋጀ አይነት ስብሰባ/virtual class meeting ይሳተፋል-ትሳተፋለች። መምህራቸው--፦
  1. እንደመደበኛው አሠራር ተመሣሣይ ደምቦችን እና የሚጠበቁ ነገሮችን ማዘጋጀት
  2. መደበኛ አሠራሮችን መዘርጋት
  3. በተማሪ የማህበራዊ - ስሜታዊ ትምህርት ላይ ማተኮር

ዓርብ፣ ኤፕሪል 3፣ የእርስዎ ልጅ --፦

 1. ከአስተማሪያቸው ጋር የክፍል ስብሰባ መሣተፍ። መምህራቸው--፦
  1. በተማሪ የማህበራዊ - ስሜታዊ ትምህርት ላይ በትኩረት መቀጠል
  2. ስለ ሒሳብ ትምህርት አሰጣጥ ፎርማቶችን እና ምን እንደሚጠበቅ መግለጽ። የመጀመሪያው የሒሳብ ትምህርት ቪድኦ ከተጠናቀቀ በኋላ ተማሪዎች መመሪያ ይሰጣቸዋል

በዚህ የርቀት ትምህርት መሰናዶ፣ የየእለቱ ትምህርት በቀን ስድስት ሠዓት ጋር እኩል አይደለም። K-2 ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በቀን ውስጥ በግምት 1.5 (አንድ ሠአት ተኩል) እስከ 2 ሠዓት ሥራ ማጠናቀቅ አለባቸው። 3 - 5 ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በቀን ውስጥ በግምት 2.5 (ሁለት ሠአት ተኩል) እስከ 3 ሠዓት ሥራ ማጠናቀቅ አለባቸው። ይህ ወቅት በሦስት ክፍለጊዜ የተከፋፈለ ነው፦ በማየት/በምልከታ የሚሰጡ ትምህርቶች፣ ከአስተማሪ ጋር በቀጥታ የሚተላለፍ ጊዜ፣ እና በግል/ለብቻ የሚሠሩ ሥራዎችን ማጠናቀቅ። 
በመጀመሪያ፣ በስነጽሑፍ፣ በሒሳብ እና በስፔሻልስ፣ ስነጥበብ፣ ሙዚቃ እና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እንጀምራለን። አዲሱ የትምህርት ሲስተማችን በትክክል እንደሚሠራ እርግጠኞች ከሆንን በኋላ፣ የሳይንስ ትምህርቶችን እንጨምራለን፣ ከዚያም የማህበራዊ ጥናት ትምህርቶች ይጨመራሉ።


የኤለመንተሪ ት/ቤቶች፦ የመጀመሪያ ሳምንት በጨረፍታ

የጊዜ ሠሌዳ-ገደብ

የመምህር ተግባር

የተማሪ ተግባር

የወላጅ ተግባር

የመጀመሪያ ቀን
(ሰኞ)

ሙያ ማዳበር፣
መምህራን ቴክኖሎጂ፣ እና የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ለማግኘት ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ፣
MP3 ማጠቃለያ ሣምንቱን በሙሉ

ከኦንላይን ትምህርት መድረኮች እና አክቲቪቲዎች ጋር መለማመድ

ሁለተኛ ቀን
(ማክሰኞ)

ሙያ ማዳበር እና እቅድ - ፕላን ማዘጋጀት

ከኦንላይን ትምህርት መድረኮች እና አክቲቪቲዎች ጋር መለማመድ

ሦስተኛ ቀን
(ረቡዕ)

ሙያ ማዳበር እና እቅድ - ፕላን ማዘጋጀት

ልክ እንደ ክፍል አይነት ስብሰባ የሚደረግበትን ቀን እና ጊዜ ለመምረጥ መምህራን ቤተሰቦችን ያነጋግራሉ መምህራን ኦንላይን መድረክ ስብሰባ ላይ ለሚሳተፉ ቤተሰቦች ያሳውቃሉ-ይገልጻሉ።

ከአስተማሪ መልእክት ይጠብቁ

ኦንላይን ትምህርት መድረኮችን/online learning platforms ዳሰሳ ይቀጥላል

አራተኛ ቀን
(ሐሙስ)

በቀጥታ የሚካሄድ የጠዋት ትምህርት ስብሰባ እና የማህበራዊ - ስሜታዊ ትምህርት
የሚቀጥለውን ሣምንት የትምህርት ይዘት መመልከት
ሙያ ማዳበር እና እቅድ - ፕላን ማዘጋጀት

ልክ እንደመደበኛው አይነት የክፍል ስብሰባ

ለዓርብ ቀን መደረግ ያለባቸውን እርምጃዎች ከአስተማሪ መልእክት ማግኘት

አምስተኛ ቀን
(አርብ)

ስለ Eureka Math ትምህርት ፎርማት እና የሚጠበቁ ነገሮችን ለማስተዋወቅ ቀጥታ የክፍል ስብሰባ
የቢሮ ሠአቶች
ሙያ ማዳበር እና እቅድ - ፕላን ማዘጋጀት

ልክ እንደመደበኛው አይነት የክፍል ስብሰባ

ለሰኞ ደረጃ በደረጃ ስለሚከናወኑ ነገሮች ከመምህር መልክት ማግኘት

ምን እንደሚጠበቅ (ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ወላጆች እና ሞግዚቶች)

በመጀመሪያው ሣምንት፣ አስተማሪዎች በቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞች ላይ ስልጠና ያገኛሉ፣ ከቡድኖቻቸው ጋር እቅድ ያዘጋጃሉ፣ እና በኢ-ሜይል ወይም በክፍላቸው በለመዱት አይነት ሌሎች የመገናኛ መንገዶች ከተማሪዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ።
ሰኞ፣ ማርች 30 እና ማክሰኞ፣ ማርች 31፣ እርስዎ እና የእርስዎ ልጅ የምታደርጉት፦

 1. myMCPS Classroom and Google Classroom በመጠቀም ኦንላይን ሪሶርሶችን እና ቱቶሪያሎችን ማሰስ ትችላላችሁ። ይህ ዳሰሳ በሣምንቱ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ሊደረግ ይችላል።የእነዚህ ኦንላይን ሪሶርሶች እና ቱቶሪያል አገናኝ-ሊንኮች በወላጆች እና ተማሪ ሰክሽን ላይ ይገኛልየቀጣይ ትምህርት ድረ-ገጽ/Continuity of Learning websiteሰኞ፣ ማርች 30 ጠዋት።

ረቡእ፣ ኤፕሪል 1 እና/ወይም ሐሙስ፣ ኤፕሪል 2 ፣ የእርስዎ ልጅ፦

 1. ስለ ሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ቀሪ ሥራዎች/remaining assignments እና በቀጣዩ ሣምንት ለሚደረገው ለመጀመሪያው “check-in” የመገናኛ ጊዜ ለመወሰን በአስተማሪዎቻቸው አማካይነት ውይይት ለማድረግ ያገኟቸዋል።

ከረቡእ፣ ኤፕሪል 1 ጀምሮ እና እስከ ሣምንቱ መጨረሻ ድረስ፣ ኬዝ ማኔጀሮች እና የስፔሻል ኢጁኬሽን አስተማሪዎች ከተማሪዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ። የ ESOL አስተማሪዎች፣ ካውንስለሮች፣ የተማሪዎችን ሠራተኞች፣ ረዳት አስተማሪዎች/paraeducators እና ሌሎች ሠራተኞች እንደዚሁ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።
ዓርብ፣ ኤፕሪል 3፣ የእርስዎ ልጅ --፦

 1. ስለ ሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ሥራዎች/assignments እና ለሚቀጥለው ሣምንት ዝግጅት እንደአስፈላጊነቱ አስተማሪዎቻቸውን ማግኘት ይችላሉ።

ሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ዓርብ፣ ኤፕሪል 17 ይጠናቀቃል። ሦስተኛውን የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በትክክል፣ ለመቆጣጠር-ለመሥራት በሚቻል መንገድ፣ እና ወደ አራተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የሚደረገውን ሽግግር በውጤታማነት ለማጠናቀቅ በተማሪዎች ላይ የሚኖረውን ጫና ለማቅለል የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ለሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ተማሪዎች ሥራዎቻቸውን/assignments እንደጨረሱ እንደአመቺነቱ ትክክለኛ ውጤት ለመስጠት ቁርተኞች ነን። 


የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፦ የመጀመሪያው ሣምንት በጨረፍታ

የጊዜ ሠሌዳ-ገደብ

የመምህር ተግባር

የ ተማሪ/ወላጅ/ሞግዚት ተግባር

 

ሰኞ
ማርች 30

ማክሰኞ
ማርች 31

ቴክኖሎጂ እና ቁሳቁሶች ማግኘት

ከባልደረቦቻቸው ጋር እንደገና መገናኘት እና ተመሣሣይ ኮርስ ከሚያስተምሩ ቡድኖች ጋር አብሮ ማቀድ-ፕላን ማዘጋጀት

በሙያ ማዳበር መሣተፍ

ለ3ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ማጠናቀቂያ ማቀድ-ፕላን ማድረግ እና ከተማሪዎቻቸው ጋር እንደገና መገናኘት

ቀጣይ ትምህርት ድረ-ገጽ/Continuity of Learning webpage ላይ የሚገኙትን ቪድኦዎች እና የአውታረመረብ ቱቶሪያል ይዳሥሱ

ከኦንላይን የትምህርት ፕላትፎርሞች ጋር ይላመዳሉ

በ MCPS የሚገኙትን ተጨማሪ የትምህርት ሪሶርሶችን ይዳስሱ
የቀጣይ ትምህርት ድረ-ገጽ/Continuity of Learning webpage

 

ረቡዕ
ኤፕሪል 1

ሐሙስ
ኤፕረል 2

ቀጣይ የሙያ ማበልጸግ/ፕላን-እቅድ ማዘጋጀት

የተዘረጉ አውታሮችን በመጠቀም ከተማሪዎች/ወላጆች ጋር እንደገና መገናኘት - ስለ ተማሪ ደህንነት

ለ3ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ማጠናቀቂያ ሥራዎችን/assignments እና የተገኙትን የትምህርት ተሞክሮዎችን ክለሳ ማድረግ

ለሚቀጥለው ሣምንት የትምህርት ይዘቶችን እና የሚጀመሩባቸውን ሠአቶች ፖስት የማድረግ መርሃግብር ማዘጋጀት

ሁሉም ተማሪዎች ቴክኖሎጂ እንዳላቸው እና ከፕላትፎርሙ ጋር መገናኘታቸውን ማረጋገጥ

ከአስተማሪ መልእክት ይጠብቁ

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜውን ለማጠናቀቅ መጪው ምን እንደሆነ መረዳት

ስለ ቀጣዩ ሣምንት መርሃግብር ማወቅ

አስፈላጊ ቴክኖሎጂ መኖሩን እና ከማስተማሪያ መድረኩ/platform መገናኘቱን ማረጋገጥ

የ3ኛ ማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ ሥራ ማጠናቀቅ መጀመር እና እንደአስፈላጊነቱ ከአስተማሪ ጋር check in ማድረግያ ጊዜ መመደብ

አርብ
ኤፕረል 3

ማቀድ እና መዘጋጀት

የሥራ ሠዓቶች

እንደአስፈላጊነቱ አስተማሪ ጋር መገናኘት

ለአዲስ መደበኛ ሥራዎች እና ለቀጣዩ ሣምንት መርሃግብሮች መዘጋጀት

ምን እንደሚጠበቅ (በስፔሻል ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች ወላጆች)
የእርስዎ ልጅ የሚከታተለው/የምትከታተለው በ፦ Longview, RICA, Stephen Knolls, Rock Terrace ወይም Carl Sandburg Learning Center ከሆነ ይህን ደብዳቤ ያንብቡ በመጀመሪያው ሣምንት የእርስዎ ልጅ ምን መጠበቅ እንደሚችል/እንደምትችል ለተጨማሪ ዝርዝር እባክዎ ይህንን ደብዳቤ ያንብቡ። ኬዝ ማኔጀሮች እና የስፔሻል ኢጁኬሽን መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር መገናኘት ይጀምራሉ። በስፔሻል ትምህርት ቤት የስፔሻል ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎች የተሻሻለ መርሃግብር ይኖራቸዋል እንዲሁም ለእነርሱ አጠቃቀም ተስተካክለው የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን ያገኛሉ።

ለስፔሻል ኢጁኬሽን ተማሪዎች ድጋፎች
የስፔሻል ኢጁኬሽን አስተማሪዎች እና ኬዝ ማኔጀሮች እንደየኬዞቻቸው ስለግላዊ የማስተማር ድጋፍ እና የማስተማር መማር እቅዱ ስለሚቀጥልበት ሁኔታ እና የ IEP ግቦችን ተግባራዊ ስለማድረግ ስትራቴጂዎችን ለመነጋገር ተማሪዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ። እባክዎ ይህንን ደብዳቤ ያንብቡ IEPs ወይም Section 504 plans የታቀፉ ተማሪዎቻ ላሏቸው ወላጆች እና ሞግዚቶች የተላከ ነው።

ለ ESOL ተማሪዎች የሚሰጡ ድጋፎች
የ ESOL አስተማሪዎች፣ ካውንስለሮች፣ ፑፒል ፐርሶኔል ሠራተኞች፣ ረዳት አስተማሪዎች፣ እና ሌሎች ሠራተኞች ሣምንቱን በሙሉ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች ጋር ይገናኛሉ።


መከታተያ ዝርዝር፦ ልጅዎን ለኦንላይን ትምህርት ማዘጋጀት

ልጅዎ ለውጤታማ የርቀት ትምህርት ተሞክሮ እንዲዘጋጅ/እንድትዘጋጅ ለመርዳት እነዚህን እርምጃዎች መተግበር ይችላሉ፦

 1. ቴክኖሎጂ ማግኘት
  1. የልጅዎን myMCPS እና/ወይም Google Classroom password ማወቅዎን ያረጋግጡ። ዝርዝር ነገሮች፣ ትምህርቶች እና ስለ myMCPS በተደጋጋሚ ስለሚነሱ ጥያቄዎች የተዘጋጁ መልሶች እዚህ ይገኛሉ።
  2. ወደ myMCPS ወይም Google Classroom መክፈት/ሎግኢን ማድረግ ይለማመዱ።
  3. የእርስዎ ልጅ እቤት ውስጥ ላፕቶፕ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት ከሌለው-ከሌላት፣ Chromebook በተውሶ ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ትምህርት ቤትዎን ከኤፕሪል 1 በፊት ይጠይቁ። 
 2. ለመማር ይዘጋጁ
  1. ሪኮርድ የተደረጉ ኦንላይን ቱቶሪያሎችን ከልጅዎ ጋር ኤፕሪል 1 ይመልከቱ
  2. ስለ 1ኛው ሣምንት መርሃግብር ከልጅዎ ጋር ይመልከቱ (ማርች 30 - ኤፕሪል 3)
 3. ተስማሚ የሆነ የሥራ አካባቢ ይፍጠሩ
  1. እቤት ውስጥ ልጅዎ ሥራው(ዋ)ን ለመጨረስ የሚችልበት-የምትችልበት ሥፍራ ያግኙ። ቦታው ማዘናጊዝያ የማይበዛበት ሥፍራ ቢሆን ይረዳል።
 4. እንዲዘወተር ያድርጉ
  1. የተለመደ ሲሆን ለልጆች በጣም አስፈላጊ ነው። ልጅዎ መከታተል እንዲችል/እንድትችል በየቀኑ አንድ አይነት-ወጥ የሆነ መርሃግብር ለማድረግ ይሞክሩ።
  2. የልጅዎን የሥራ መርሃግብር በአስተማማኝነት ለመገንባት፣ ለትምህርት የተመደቡ ሠዓቶችን እና የአስተማሪ የቢሮ ሥራ ጊዜዎችን (ምን ጊዜ እንደሚገኙ) ማወቅ አለብዎት።
 5. እንዴት እርዳታ ማግኘት እንደሚችሉ ይወቁ
  1. የትምህርት ቤት ርእሰመምህር(ት) ያግኙ። በሌላ ቋንቋ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ AskMCPS በስልክ ቁጥር 240-740-3000 ይጠይቁ።
  2. የልጅዎን አስተማሪዎች የሚያገኙበትን መረጃ በቀላል ማግኘት በሚችሉበት ስፍራ ያስቀምጡ።

ተስፋ እናደርጋለን
በዚህ ሽግግር ውስጥ እያለን ስለግንዛቤዎ እና ስለ ትእግስትዎ እናመሰግናለን። እባክዎ ያስታውሱ ሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ዓርብ፣ ኤፕሪል 17 የሚጠናቀቅ መሆኑን ይህንን ዓለም አቀፋዊ ወረርሽኝ በጋራ በምንጋፈጥበት አስቸጋሪ ወቅት ላይ ከባድ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኙትን ሠራተኞቻችንን በጣም ልናመሰግናቸው እንወዳለን። ከርቀት ስለሚሰጥ ትምህርት ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፣ እባክዎ ይህንን ድረ-ገጽ Continuity of Learning webpage ይመልከቱ።
ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools 
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ