Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: June 7, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

ስለ ዘረኝነት እና ኢፍትኃዊነት እየተካሄደ ያለውን አገርአቀፋዊ ውይይትን በመመርኮዝ፣ የትምህርት ሲስተም እንደመሆናችን መጠን ባለፈው ሣምንት እኛ ትኩረት ያደረግነው የተማሪዎቻችንን እና የሠራተኞቻችንን ማህበራዊና-ስሜታዊ ደህንነትን በመደገፍ ላይ ነው። እነዚህ አሳዛኝ ክስተቶች የ MCPS ተማሪዎች በጠቅላላ በሙሉ አቅማቸው ካሰቡበት መድረስ እንዲችሉ ሠላምና ደህንነትን፣ ምቹ ሁኔታን መፍጠር፣ አብሮነት እና አቃፊነት ላይ በየቀኑ መሥራትና መገንባት እንደሚኖርብን ያስታውሱናል። በዚህ ጊዜ የራሳቸውን ታሪክ በማካፈልና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማሰማት በአገራችን ያለውን ተቋማዊ የዘረኝነት ሁኔታ እንዲፈርስ የተንቀሳቀሱትን ተማሪዎቻችንን እና ሠራተኞችን እውቅና ለመስጠት ፈልጋለሁ። ባለፈው ሣምንት እንዳካፈልኳችሁ ሁሉ፣ የተሻለ፣ ፍትሃዊ፣ ሚዛናዊ እና ልክ ተቀባይነት ያለው ሊሆን የሚገባ ማህበረሰብን ለልጆቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን እና ለራሳችን ለመገንባት አጥብቀን መሥራት አለብን። የማህበረሰባችን አባላት በኢፍትሃዊነት እና በፍርሃት ስቃይ እየኖሩ እኛ በስንፍና ዝም ብለን መቆም አንችልም። በዚህ ሁላችን አንድ ላይ ከሆንን፣ ሁላችንም ሃላፊነት ወስደን የራሳችንን ድርሻ መሥራት አለብን። MCPS ማለት ሁሉም ማለት በእርግጠኝነት ሁሉንም የሚያቅፍ መሆኑን በሚያረጋግጥ ሁኔታ ፍትሃዊነት ሚዛናዊነት እና እጅግ በጣም ጥሩ ሁኔታን ለማስፈን በከፍተኛ ስሜት፣ በስፋት እና በጥልቀት ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

ከዚህ በታች ያሉት በርካታ አስፈላጊ ወቅታዊ መግለጫዎች ሲሆኑ፣ ስለ ሠመር ትምህርት ቤት መረጃ፣ ስለአዲሱ የማርክ ውጤት አሰጣጥ አማራጮች ስልት እና ስለ ትምህርት ዓመት መጠናቀቅ እና የመዝጋት ሂደት ለቤተሰብ የቀረቡ መረጃዎች ናቸው።

በዚህ እጅግ አሳሳቢና አስፈላጊ ሥራ ላይ የእኛ አጋሮች በመሆናችሁ እናመሰግናለን። ሠላም ይሁንላችሁ።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D. 
Superintendent of Schools


ማውጫ

| የሰመር ት/ቤት ፕሮግራሞች | የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማርክ ውጤት አሰጣጥ አማራጮች | ለቤተሰቦች የዓመቱ መጨረሻ የመዝጊያ ሒደት | ስለ ሠመር የምግብ አገልግሎት | ስለ ሠመር ክሮምቡክ እና Mi-Fi ስርጭት/Summer Chromebook and Mi-Fi Distribution | ስለተገቢነት፣ ትክክለኛነት እና ሚዛናዊነት የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂ ክፍል፣ የ MCPS ቤተሰቦችን ለመርዳት የሚችሉ ሪሶርሶች አሉት | ትምህርት ቤቶች በተናጠል ስለሚያካሄዷቸው ቨርቹወል የምረቃ ስነ ስርአት የጊዜ ሠሌዳ | ብቃት ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች በሞንትጎመሪ ኮሌጅ በነፃ የሠመር ኮርሶችን መውሰድ ይችላሉ። | በኮቪድ-19 ተገልሎ መቆየት የቤት ውስጥ ጭቅጭቅና ጠብ ሠለባዎች ስጋት እንዲባባስ እያደረገ ነው | የሞንትጎመሪ ካውንቲ በኮቪድ-19 ወቅት ስለህፃናት እንክብካቤ ፍላጎቶችን ከወላጆች ለመስማት ዳሰሳ እያደረገ ነው |


የሰመር ት/ቤት ፕሮግራሞች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በርካታ የሠመር ትምህርቶችን እና እውቀት/ልምድ የማዳበር እድሎችን ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሪጅናል፣ በትምህርት ቤትቶች የተመሠረቱ እና ሌሎች ዲስትሪክት አቀፍ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። በጣም ከፍተኛ የተማሪዎች ቁጥር ይኖራል ብለን በገመትነው የሠመር ፕሮግራሞች ላይ ለማስተማር እና ለመሣተፍ የተዘጋጁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች አሉን።

ከማህበረሰብ ግብረመልስ ካገኘን በኋላ በሠመር ወቅት በቀጣይ ስለሚሰጡ ፕሮግራሞች እና የትምህርት እድሎች MCPS ለርእሰመምህራን፣ ለመምህራን እና ለማህበረሰብ በመጪው ሣምንት፣ በርካታ መረጃዎችን ያስተላልፋል። አብዛኛዎቹ ፕሮግራሞች ጁላይ 13 ይጀመራሉ። ስለ ሠመር ፕሮግራሞች የወላጆች አስተያየት የሚቃኝበት ዳሰሳ እስከ ጁን 12 ድረስ ክፍት ይሆናል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ቨርቹወል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት "MCPS Virtual High School Summer School" እንዲሁም ጁላይ 13 ተጀምሮ እስከ ኦገስት 14 ለሚካሄደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ኮርሶች ምዝገባ ዓርብ፣ ጁን 12 ይጀመራል። ተማሪዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ በሶሻል ስተዲስ፣ በሳይንስ፣ በሒሳብ፣ እና በስነጥበብ፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ እና በጤና ትምህርት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሶች ደግሟል/ደግማለች ወይም የመጀመሪያውን ክሬዲት "repeat or original credit" ሊያገኙ ይችላሉ።

ስለ እያንዳንዱ የኮርስ አሰጣጥ፣ የ ኦንላይን ኮርስ መስፈርቶች እና የምዝገባ ሊንኮች ዝርዝሮቹ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የሠመር ስኩል ድረገጽ ላይ MCPS Summer School Webpage ይገለጻሉ።


የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማርክ ውጤት አሰጣጥ አማራጮች

በዚህ ሠመር ሥራ ላይ በሚውለው ክለሳ በተደረገው የውጤት አሠጣጥ መሠረት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሶችን የሚወስዱ ተማሪዎች ለመጨረሻው ሴሚስተር ውጤት በፊደል የሚሰጥ ማርክ ወይም አልፏል-አልፋለች/አላለፈም-አላለፈችም "letter grade or Pass/Incomplete" ለመምረጥ ይችላሉ። አለበለዚያ፣ ተማሪዎች አሁን በቀጥታ ተደራሽነት ያለውን በ MCPS Google account አማካይነት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የውጤት አሰጣጥ ምርጫቸውንም "Grading Options Tool" ለመጠቀም ይችላሉ። ተማሪዎች ስለ ማርክ የውጤት አሰጣጥ አማራጮቻቸውን እስከ ጁን 12 ለመምረጥ ይችላሉ። መመሪያዎቹ ለተማሪዎች ኢሜይል ተደርገዋል እና ለወላጆች ባለፈው ሣምንት ተልኳል። ስለ እያንዳንዱ ኮርስ በእውቀት በጥንቃቄ ለመወሰን እንዲረዳ grade calculator አጠቃቀም ጭምር ዝርዝር መመሪያ ከዚህ በታች ይገኛል። ከዚህ ጊዜ በኋላ ምርጫዎቻቸውን እንደገና ለማየት የሚፈልጉ ተማሪዎች/ወላጆች አሁን ያለውን የማርክ ውጤት አሠጣጥ ለውጥ ሂደት በሚመለከት ከትምህርት ቤት ካውንስለር ጋር መሥራት ይችላሉ። ተማሪዎች የትምህርት ዓመቱ እስከሚያልቅ ድረስ በኮርስ ሥራ ላይ መሆንን መቀጠል አለባቸው።

ለተማሪዎች/ለወላጆች መመሪያዎች
ለሴሚስተር 2፣ የአንተ(ቺ)ን የውጤት አሰጣጥ ምርጫዎችህ(ሽ)ን ስለማቅረብ፣

  1. ይህንን ድረ-ገጽ ጎብኝ(ኚ)፦ https://bit.ly/mcpsmd-grade-display-preference
  2. ሎግኢን ለማድረግ፦ የተማሪ MCPS Google username (ex., student_id@mcpsmd.net) and password to log in ተጠቀም(ሚ)።
  3. አማራጮችህ(ሽ)ን ምረጥ(ጪ)። ለእያንዳንዱ ኮርስ የበለጠ የሚጠቅመውን ለመምረጥ "Grade Calculator" ተጠቀም(ሚ)። ከጨረስክ(ሽ) በኋላ Submitየሚለውን ተጫን(ኚ)
  4. አማራጮችህ(ሽ)ን ካቀረብክ(ሽ) በኋላ፣ ሪኮርድ እንዲደረግልህ(ሽ) ለ MCPS Google account የኢሜይል ማረጋገጫ ይላካል።

አስፈላጊ መረጃዎች

  • Timeline/የጊዜ ገደብ → መካከልጁን 4/2020 እና ጁን 12/2020፣ተማሪዎች የሴሚስተር 2 የማርክ ውጤቶች በሪፖርት ካርዳቸው ላይ እንዴት እንዲታይ እንደሚፈልጉ ምርጫዎቻቸውን ለማቅረብ ይችላሉ።
  • የየእለቱ ገደቦች/Daily Limits → ተማሪዎች በመሃል በርካታ ጊዜ ምርጫዎቻቸውን ለማስተካከል ይችላሉ፣ ነገር ግን በቀን ሦስት ጊዜ ማድረግ/እና ማቅረብ ብቻ ይቻላል።
  • የኮርስ ዝርዝር/Course List  → መገልገያው (The tool) ለተማሪዎች የሚያሳየው ክሬዲት የሚሰጥባቸውን ኮርሶች ብቻ ነው።
  • Default Choice → ምርጫ ካልተገለጸ የ "The default report card"  በፊደል የተመዘገው የማርክ ውጤት አጠቃላይ GPA ን የሚያሻሽል እስከሆነ ድረስ በካርድ ላይ የሚቀመጠው በፊደል “Letter” ይሆናል። ካልሆነም “P” ይመዘገባል።

ስለ ማርክ አሰጣጥ ስልት ጥያቄ ካለ ወይም እርዳታ ካስፈለገ፣ እባክዎ help guide የሚለውን ይመልከቱ።


ለቤተሰቦች የዓመቱ መጨረሻ የመዝጊያ ሒደት

ቤተሰቦች የተማሪዎችን የግል እቃዎቻቸውን ከትምህርት ቤቶች ለመረከብ የሚችሉበትን እድል ለማመቻቸት MCPS ሲስተምአቀፍ ጥረቶችን እያስተባበረ ነው። በመጪዎቹ ቀናት፣ የእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን ስም (last names) መሠረት በማድረግ የአገልግሎቶች እቅድ እና ዝግጅት መርሃግብር ይገለጻል። ወላጆች የሚከተሉትን የአሠራር ሒደት መጠበቅ አለባቸው፦

  • የተማሪዎች እቃዎች በሙሉ በከረጢት ተደረገው ስም ተጽፎባቸው ይዘጋጃሉ። (ስም፣ ክፍል፣ አክቲቪቲ፣ ወዘተ)
    • በትምህርት ክፍል ሠራተኞች፣ በአስተዳዳሪዎች እና ከዋናው ጽ/ቤት ድጋፍ የሚሰጡ ሠራጠኞች አማካይነት የተማሪዎች እቃዎች በሙሉ በከረጢት ተዘጋጅተዋል።
  • በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት በመኪና ተነድቶ የሚገባበት እና በእግር የሚገባበት አማራጭ ይኖራል።
  • ሒደቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቤተሰቦች በመኪናዎቻቸው ውስጥ ወይም ለእግረኞች በተመደበላቸው አካባቢ እንዲቆዩ ይጠበቃል።
    • የእርስዎ ልጅ እቃ እስከመኪናዎ ድረስ ወይም ለእግረኞች በተመደበላቸው አካባቢ ድረስ ይመጣል። (እቃዎችን በሚያስረክቡበት ወቅት የ MCPS ሠራተኞች ራሳቸውን መከላከያ ይለብሳሉ።)
    • በከረጢት የተዘጋጁ እቃዎችን ከረከቡ በኋላ፣ ከሌሎች ጋር ንክኪ እንዳይኖር እባክዎ በፍጥነት ግቢውን ይልቀቁ።
  • የእቃ መረከቢያው ሂደት ጁን 15 ከሚሆንበት ሣምንት ጀምሮ ጁን 29 እስከሚሆንበት ሣምንት ድረስ ይቀጥላል።

የልጆችን እቃ ለማስረከብ ይህንን አሠራር የቀየስነው የማህበረሰባችንን ስጋት በሚቀንስ አኳኋን ቤተሰቦችን ለማገልገል ነው። የጊዜ ሠሌዳን በሚመለከት ርእሰመምህራን ለትምህርት ቤቶቻቸው ማህበረሰብ በቀጥታ ያሳውቃሉ።


ስለ ሠመር የምግብ አገልግሎት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በካውንቲው ውስጥ ከ50 በሚበልጡ ጣቢያዎች ላይ እስከ ጁን 30/2020 የቁርስ፣ ምሣ እና እራት ምግቦችን መስጠት ይቀጥላል። ዲስትሪክቱ በሠመር ወራት ስለሚከናወኑት አገልግሎቶች እቅድ እያዘጋጀ ነው። ስለ ዝርዝሩ በፍጥነት ይገለጻል።


ስለ ሠመር ክሮምቡክ እና Mi-Fi ስርጭት/Summer Chromebook and Mi-Fi Distribution

በሠመር ወቅት በሙሉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በየቀኑ የቴክኖሎጂ ስርጭት ይቀጥላል። ተማሪዎች ከሰኞ እስከ ዓርብ 10 a.m. እስከ 12 p.m. ከ 45 W. Gude Drive in Rockville - "Chromebooks እና Mi-Fi ዲቫይሶችን ለመቀበል እና ማናቸውንም የማይሰሩ መገልገያዎችን-non-functioning devices ተመላሽ በማድረግ ልዋጭ ለመውሰድ ይችላሉ።


ስለተገቢነት፣ ትክክለኛነት እና ሚዛናዊነት የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂ ክፍል፣ የ MCPS ቤተሰቦችን ለመርዳት የሚችሉ ሪሶርሶች አሉት

ለሠራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች በጠቅላላ ወቅታዊ እና ፋይዳ ያለው ድጋፎችን እና ሪሶርሶችን ለመስጠት MCPS Equity Initiatives Unit ስለ ፍትኃዊነትና-ሚዛናዊነት አስፈላነት EquityMatters! የተሰኘ ልዩ የመረጃ መፅሄት እትም አዘጋጅቷል።

የዚህ ወቅት የትምህርት ባለሙያዎች መመሪያ የሚጀምረው በሦስት ግላዊ ይዘቶች ሲሆን፣ በአራት የተከፈሉ ሪሶርሶች እና መሣሪያዎች-resources and tools ይኖሩታል፦

  •      ራስዎን ያስተምሩ
  •       በጸረ-መድሎአዊነት አስተሳሰብ ይመሩ/ይምሩ
  •       ተማሪዎችን ስለማሳተፍ ለትምህርት ባለሙያዎች ጠቃሚ መሣሪያዎች-Tools
  •       ስለ ዘረኝነት ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ለመነጋገር የሚጠቅሟቸው ሪሶርሶች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የስነልቦና አገልግሎት ዲቪዝዮን-MCPS Division of Psychological Services እንደዚሁ ሠራተኞች እና ቤተሰቦች ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚረዱ ሪሶርሶች አሉት። ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

ስለ ዘር እና የተለየ መብት፣ ጥቅም፣ ክብር ግንዛቤ ማግኘት-Understanding Race and Privilege
ስለ ረብሻ ከልጆች ጋር መነጋገር-Talking to Children About Violence
ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የማስተማሪያ እቅድ ዝግጅት-Lesson Plans for Secondary Students


ትምህርት ቤቶች በተናጠል ስለሚያካሄዷቸው ቨርቹወል የምረቃ ስነ ስርአት የጊዜ ሠሌዳ

ሊካሄድ ባለው የቨርቹወል ዩንቨርሳል የምረቃ ስርአት በተጨማሪ ዛሬ ምሽት - tonight at 6 p.m.፣ እያንዳንዱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተመራቂ ተማሪዎች ቨርቹወል የምረቃ ስርዓት ያካሄዳል። ስለእነዚህን የምረቃ ሥነ ሥርአቶች የጊዜ ሠሌዳ እዚህ መመልከት ይቻላል።


ብቃት ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች በሞንትጎመሪ ኮሌጅ በነፃ የሠመር ኮርሶችን መውሰድ ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ራፕቷር ሬዲ ፕሮግራም-Montgomery College’s Raptor Ready Program የ 2020 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች በኦንላይን ወይም.ስለ ኮሌጅ ኮርሶች በቅድሚያ እንዲያውቁ ለመርዳት ዝግጁ ነው በ online ወይም structured remote environment።

የስኮላርሽፑ ፕሮግራም የትምህርት ክፍያዎችን ለአንድ ኮርስ ይሸፍናል (four billed hours maximum) እና በሞንትጎመሪ ኮሌጅ-MC ጁላይ 11 ለሚጀመረው የሁለተኛ ሠመር ክፍለጊዜ ለቴክኖሎጂ ወይም የትምህርት ግብአቶችን ለመሸፈን $530 ግራንት ይሸፍናል። ፕሮግራሙ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች የሆኑ ለ2020 ስፕሪንግ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህት ቤት ተመራቂዎች (ጁን ላይ ይደረጋሉ ተብሎ የሚታሰቡትን የምረቃ ሥነ ሥርአቶች ጭምር) ነው።

የበለጠ መረጃ/ኢንፎርሜሽን እዚህ ይገኛል።


በኮቪድ-19 ተገልሎ መቆየት የቤት ውስጥ ጭቅጭቅና ጠብ ሠለባዎች ስጋት እንዲባባስ እያደረገ ነው

ህዝብን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ተብሎ እቤት ውስጥ የመቆየት ትእዛዝ/stay-at-home orders ምክንያት የቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ሠለባዎችን በከፍተኛ ስጋት ላይ እየጣለ ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቤተሰብ ፍትህ ማእከል "Montgomery County Family Justice Center" የቤት ውስጥ ጥቃት ሲፈጠር ወይም እርዳታ ሲያስፈልጋቸው ሰዎች ሪፖርት የሚያደርጉበት ኢሜይል አዘጋጅቷል። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል


የሞንትጎመሪ ካውንቲ በኮቪድ-19 ወቅት ስለህፃናት እንክብካቤ ፍላጎቶችን ከወላጆች ለመስማት ዳሰሳ እያደረገ ነው

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህጻናት እንክብካቤ ማስተባበሪያ ካውንስል "Montgomery County’s Early Childhood Coordinating Council" ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው እንክብካቤ ፍላጎቶቻቸውን ለመስማት ይፈልጋል። በምናገኘው መረጃ ስለፕሮግራሞቹ እና በካውንቲው ስለሚሰጡት አገልግሎቶች ውሳኔዎችን ለመስጠት እንጠቀማለን። ዳሰሳውን እዚህ ይሙሉ።


Important Online Resources: