Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 17, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

የ 2019-2020 ትምህርት ዓመት ሊያልቅ ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ብቻ መቅረቱን ለማመን ይከብዳል። በቨርቹወል ትምህርት ከተሠማራን ስምንት ሣምንት አሳልፈናል እና፣ በመንገዳችን ላይ በርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እየተጋፈጥን፣ ተማሪዎቻችን፣ ሠራተኞች እና ማህበረሰባችን ከመጀመሪያው እስካሁን ድረስ እጅግ አስገራሚ የሆነ ጥንካሬ እና ትእግስት በማሳየት እርስ በርስ ለመደጋገፍ የሚያስችሉ መንገዶችን በመፍጠር በንቃት ተሳትፈዋል ። ሁላችሁም ባደረጋችሁት ጥረት በበኩሌ በእውነት ተነቃቅቻለሁ።

ስለ ትምህርት ዳግም ማንሰራራት እና በመጨረሻም ትምህርት ቤቶች ስለሚከፈቱበት ሁኔታ ሁለገብ እቅድ በማዘጋጀት ሠራተኞቻችን በትጋት እየሠሩ መሆናቸውን እባክዎ እንዲገነዘቡ እንፈልጋለን። ከገቨርነሩ እና ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት መመሪያ የሚጠይቁ በርካታ ገና ያልታወቁ ነገሮች እና ጥያቄዎች ቢኖሩም፣ ለተማሪዎቻችን በሙሉ የዳበረ ትምህርት፣ ወቅታዊ ድጋፎችን እና ሪሶርሶችን ለመስጠት እየተዘጋጀን መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

ከዚህ በታች ያሉት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ሦስተኛውን ምእራፍ ኦንላይን ትምህርት ጨምሮ - Phase III of online learning in MCPS፣ የ2021 ባጀት ዓመት የ MCPS ሥራ ማስኬጃ ባጀት - Fiscal Year 2021 MCPS Operating Budget፣ ስለ ምዋእለህፃናት ምዝገባ፣ ከትምህርት ቤት ህንፃዎች የግል ቁሳቁሶችን ስለመውሰድ፣ እና ስለመጪው ቨርቹወል የታወንሆል ስብሰባዎች የሚገልጹ በርካታ የወቅታዊ ይዞታ መግለጫዎች ናቸው።

የልጆቻችን፣ የሠራተኞች እና የማህበረሰባችን ጤንነት እና ደህንነት ለእኛ ቁጥር አንድ ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጥበት ጉዳይ ሆኖ ይቀጥላል። ተማሪዎቻችን፣ ቤተሰቦች እና ሠራተኞች በቀጣይነት እቤት ውስጥ መቆየት እንዳለባቸው ከካውንቲ ሥራ አመራር እና ከጤና ባለሙያዎች የተሰጠውን መመሪያ እንዲከተሉ በማሳሰብና በመደገፍ ከጎናቸው እንቆማለን። የዚህን ገዳይ ወረርሽኝ ሥርጭት ለመግታት የየራሳችንን ድርሻ መፈጸም መቀጠል አለብን።

ከአክብሮት ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D. 
Superintendent of Schools


ማውጫ

| Phase III of Online Learning - ሦስተኛው ምዕራፍ ኦንላይን ትምህርት | ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ | ስለ ኤክስትራካሪኩለር እንቅስቃሴዎች አካደሚያዊ ብቃት - Academic Eligibility for Extracurricular Activities | ከትምህርት ቤቶች የግል የሆኑ እቃዎችን ስለመውሰድ | የ2021 በጀት ዓመት የበጀት ምልከታ - Fiscal Year 2021 Budget Outlook | ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል ምርጫ | ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል ምርጫ | ስለ LGBTQ+ ቨርቹወል ታወንሆል ሜይ 27 ይካሄዳል | በኮቪድ - COVID-19 ወቅት ስለ ኮሌጅ የምዝገባ ሒደት መቀኛት | የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የ2020-2021 የዓመቱ መምህርት - 2020-2021 MCPS Teacher of the Year |


Phase III of Online Learning - ሦስተኛው ምዕራፍ ኦንላይን ትምህርት

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሦስተኛው ምዕራፍ የርቀት ኦንላይን ትምህርት ሰኞ፣ ሜይ 18 ይጀመራል፤ ከዚያም ሰኞ፣ ጁን 15 ይጠናቀቃል። በዚህ ምእራፍ ወቅት፣ ትምህርቶች እና የማስተማር እንቅስቃሴዎች በቀጥታ ስርጭት እና በቅድሚያ ሪኮርድ የተደረጉትን የማቅረብ እንቅስቃሴ የሚቀጥል ሲሆን መምህራን ተማሪዎችን ለማሳተፍ በተዘጋጁ መርሃግብሮች እና ሒደቶች ሥራቸውን ይቀጥላሉ። ለሠራተኞች እና ለተማሪዎች የማህበራዊ-ስሜታዊ-ስነልቦናዊ የመማር እድሎችን መሰጠት ይቀጥላል። መምህራን እና ትምህርት ቤቶች በተሠናዳ ሁኔታ የቤት ሥራዎቻቸውን እንዲሠሩ እና የቁጥጥር ጊዜአቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲጠብቁ ተማሪዎችን ለመርዳት ያላቸውን የካለንደር አሠራር መርኃግብር ይጠቀማሉ፣ እና ወላጆች/ሞግዚቶች የቤት ትምህርትን እየረዷቸው ስለሆነ እነዚህን መረጃዎች ለእነርሱም ለመስጠት የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሒሳብ፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበብ እና የ ESOL ይዘት ያላቸውን የህትመት ማስተማሪያ ጥራዞችን በየሣምንቱ ረቡእ መስጠቱን ይቀጥላል። በህትመት የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን ዝርዝር በሙሉ እዚህ ይመልከቱ ሜይ 13 እና ሜይ 20 - እነዚህን ጥራዞች ለመውሰድ በሁሉም  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የምግብ አገልግሎት ጣቢያዎች - MCPS meal service locations-ይገኛሉ።

ምዕራፍ ሦስት - Phase III ለኤለመንተሪ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦች

የሳይንስ ትምህርትን ፍላጎት ለማዳበር፣ የእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት የሥራ ባልደረባ ሜይ 18 በሚሆንበት ሣምንት ጀምሮ ተማሪዎችን በኤለመንተሪ የሳይንስ ትምህርት ሪሶርሶች እንዲሳተፉ ያደርጋል/ታደርጋለች። ትምህርቱ ሲሰጥ ተማሪዎቹች በማይኖሩበት ጊዜ የሥራባልደረባው(ዋ) ትምህርቱን ሪኮርድ ያደርጋል-ታደርጋለች። የሳይንስ ትምህርቶች ስለሚሰጡት ጊዜ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦችን ያነጋግራሉ። ሜይ 18 በሚሆንበት ሣምንት የኤለመንተሪ ማህበራዊ ጥናት ሪሶርሶችንም "Elementary social studies resources" እናስተዋውቃለን። እነዚህ አክቲቪቲዎች ታሳቢ የተደረጉት ለቤተሰቦች እንደተጨማሪ ማበልፀጊያ እንዲጠቀሙበት ነው። የኤለመተሪ ሳይንስ እና ሶሻል ስተዲስ-የማህበራዊ ጥናት ትምህርቶች ለመማር ከፈለጉ የሚወሰዱ የትምህርት እድሎች መሆናቸውን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ስለ ሦስተኛው ምዕራፍ - Phase III አፅንኦት የሚሰጡ ነገሮች

የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሪኮርድ በተደረጉ ቀጥታ በሚተላለፉ የማስተማር ስርጭቶች ይቀጥላሉ እና እንደአካባቢው ትምህርት ቤት መርኃግብር ትምህርት ላይ ስለመገኘታቸው ቀጥታ ቁጥጥር አስፈላጊነት ላይ ያተኩራሉ። ተማሪዎች ትምህርት ላይ መገኘታቸውን ለመምህራቸው የሚያሳውቁበት ሠዓት-check-ins አስተማሪዎች ከተማሪዎች ጋር ለመገናኘት፣ ተማሪዎችን በመማር ማስተማር ሒደት ላይ ለማሳተፍ፣ ማስተማርን ለመቀጠል እና ድጋፍ ለመስጠት አስፈላጊ ሠዓቶች ናቸው። ተማሪዎች አራተኛውን የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ-4th Marking Period በስኬታማነት እንዲያጠናቅቁ እና በ revised grading policy-የተሻሻለውን የውጤት አሠጣጥ መርህ የሴሚስተር ማጠቃለያ ውጤትን ተግባራዊ ለማድረግ መምህራን በትጋት ይሠራሉ።


ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ

ሜይ 12፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሻሽሎ የቀረበ የውጤት አሠጣጥ መርህን አጽድቋል። የተደረገው ለውጥ አካል እንደመሆኑ መጠን፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በፊደል ውጤት ለማግኘት ይችላሉ ወይም ምርጫቸው ከሆነ “Pass” - አልፏል/አልፋለች የሚል እንደ መጨረሻ ሁለተኛ ሴሚስተር ውጤት በእያንዳንዱ ኮርስ course-by-course basis ሊያገኙ ይችላሉ።

ተማሪዎች ስለውጤት አሰጣጥ የሚጠቅማቸውን አማራጭ የመውሰድ አድቫንቴጅ እንዲኖራቸው የሚያረጋግጡ ሲስተሞችን በአሁኑ ጊዜ እያዘጋጀን እንገኛለን፣ እና ተማሪዎች/ቤተሰቦች ለመወሰን የሚያስችላቸው እውቀት ኖሯቸው የመረጡትን እንዲወስኑ መረጃ ይሰጣቸዋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሶች ላይ ስለ ውጤት አሰጣጥ አማራጮችን እንዴት መምረጥ እንዳለባቸው መረጃ በሚቀጥለው ሣምንት እንልካለን፣ ነገር ግን ተማሪዎች/ቤተሰቦች ይህንን ለመወሰን እንደአመቺነቱ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ እንደሚኖራቸው አፅንኦት ለመስጠት እንፈልጋለን።

መሥፈርቱን - መመዘኛውን ያላሟሉ ተማሪዎች በ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ኮርስ ያላለፉ ከሆነ “Incomplete” ይሰጣቸዋል እና በሠመር ትምህርት ፕሮግራም እና/ወይም በትምህርት ማካካሻ ወቅት አሻሽለው ለማለፍ የሚያስችላቸውን ውጤት የማግኘት እድል ይሰጣቸዋል። በሠመር ትምህርት ፕሮግራሞች ያሉትን እድሎች በሚመለከት የበለጠ መረጃ-ኢንፎርሜሽን በመጪዎቹ ሣምንቶች እናስተላልፋለን።


ስለ ኤክስትራካሪኩለር እንቅስቃሴዎች አካደሚያዊ ብቃት - Academic Eligibility for Extracurricular Activities

 አሁን በሥራ ላይ የሚገኘውን የአካደሚያዊ ብቃት አስፈላጊነት መስፈርት የትምህርት ቦርድ ሜይ 12 በጊዜያዊነት እንዲቀር ወስኗል Board Policy IQD፣ Academic Eligibility for Extracurricular Activities። በኤክስትራከሪኩለር እንቅስቃሴዎች-extracurricular activities ለሚሳተፉ ተማሪዎች የአካደሚያዊ መስፈርት ለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ለቀሪው ጊዜ እና ለ  2020-2021 የመጀመሪያው ሴሚስተር ተሠርዟል።


ከትምህርት ቤቶች የግል የሆኑ እቃዎችን ስለመውሰድ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሠራተኞች የግል እቃዎቻቸውን እና ቁሳቁሶቻቸውን እንዲወስዱ የመፍቀድ ሒደት ጀምሯል። በዚህ ሒደት የሠራተኞች እና የተማሪዎች ጤንነት ዋነኛው ቀዳሚ ትኩረት ይሆናል። መከላከያ የተላበሱ ሠራተኞች ቁሳቁሶችን ከማገጃ ቦታ-curbside ለመውሰድ ያዘጋጃሉ። ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ወደ ህንፃው እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም። ይህ ሒደት ሊጓተት ስለሚችል ከጁን 15 በኋላም ይቀጥላል። ርእሰመምህራን፣ ከማእከላዊ አገልግሎቶች ጋር በመተባበር፣ ይህ ሒደት መቼ እንደሚጀምር ጊዜውን ትምህርት ቤቶች ለየራሳቸው ማህበረሰብ ያሳውቃሉ።


የ2021 በጀት ዓመት የበጀት ምልከታ - Fiscal Year 2021 Budget Outlook

ሜይ 15፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ስለ ካውንቲው የበጀት ዓመት-Fiscal Year (FY) 2021 የሥራ ማስኬጃ ባጀት $5.9 ቢሊዮን ዶላር እና የበጀት ዓመት-FY21-26 የካፒታል ማሻሻያዎች ፕሮግራም-Capital Improvements Program (CIP) ኮንስትራክሽን፣ መሠረተ ልማት እና የማህበረሰብ ፕሮጀክቶችን MCPS ን ጨምሮ ለሁሉም የካውንቲ ኤጀንሲዎች $4.4 ቢሊዮን እንደሚሆን የመጀመሪያ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከካውንቲው የሥራ ማስኬጃ ባጀት ከግማሽ በላይ—$2.76 ቢሊዮን የ MCPS ፈንድ ይሆናል። በሜሪላንድ ስቴት በተሰጠ ሥልጣን መሠረት፣ ይህን ያክል ፈንድ የእኛን ዲስትሪክት ባለው የትጋት ደረጃ ያስኬደዋል። ይህ የሚገልጸው በ FY20 ከፀደቀው ባጀት የ $74.9 ሚሊዮን ዶላር እድገት ወይም 2.8 ፐርሰንት ጭማሪ ያመለክታል። ነገር ግን፣ ፌብሩወሪ 10/2020 የትምህርት ቦርድ ከጠየቀው ያነሰ ነው። ይህ ቅነሳ ዲስትሪክቱ ስትራቴጂያዊ ቁልፍ ሥራዎችን የማስፋፋት ተግባርን እንዳያከናውን ሊያደርግ ይችላል። የካውንቲው ካውንስል የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ እዚህ ያንብቡ።

የካውንቲው የስድስት ዓመት አጠቃላይ $4.4 ቢሊዮን የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ለ MCPS ጠቅላላ $1.74 ቢሊዮን የሚጨምር ሲሆን፣ ይኼውም በመጀመሪያ በትምህርት ቦርድ ከተጠየቀው $81.5 ሚሊዮን የሚያንስ እና በዚህ ወቅት ከፀደቀው $7.3 ሚሊዮን የሚያንስ ነው። ከ MCPS CIP ማስታወሻ አንዳንድ ነገሮች-items የሚያካትቱት የውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - Woodward High School and the Northwood High School ተጨማሪ/ፋሲሊቲ ማሻሻያ መርኃግብር እና ለ በርንት ሚልስ ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት፣ ኒልስቪል መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የካፒታል ፕሮጀክት ማሻሻያን የሚጨምሩ ይሆናል። ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - Col. Zadok Magruder High School and Poolesville High School በትምህርት ቦርድ ንድፈኃሳብ የቀረበ መርኃግብርን ያካትታል። በውድሊን፣ ሳውዝ ሌክ እና ስቶንጌት ኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶች - Woodlin, South Lake and Stonegate elementary schools, እና በደማስከስ እና ቶማስ ኤስ. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች - Damascus and Thomas S. Wootton high schools ዋና ዋና የካፒታል ፕሮጀክቶችም በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚቀጥሉ ፀድቋል። ለወደፊቱ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ካፒታል ፕሮጀክቶችን በመለየት ገንዘብ-ፈንድ ስለሚገኝበት ሁኔታ ከትምህርት ቦርድ እና ከካውንስሉ ጋር መሥራታችንን እንቀጥላለን። 

በ COVID-19 ዓለም አቀፋዊ የጤና ወረርሽኝ ምክንያት በጣም ትልቅ የፋይናንስ አስተማማኝ ያለመሆን ችግር መፈጠሩን የምንገነዘብ ስለሆነ የትምህርት ቤቶችን ሥራ ማስኬጃ እና የማስተማር መሠረተ ልማትን ለማስቀጠል እና በጥራት እና ፍትሃዊነት ላይ ትኩረታችንን እንደምናደርግ በእርግጠኝነት ቁርጠኞች ነን። በቀጣዩ ዓመት የተለያዩ የትምህርት ተሞክሮዎችን ስለመስጠት እና የተማሪዎችን እና የሠራተኞችን ደህንነት ስለመጠበቅ የዲስትሪክቱን ሥራዎች የሚያንፀባርቁ መንገዶችን በተመለከተ ባጀት ስለማፅደቅ የትምህርት ቦርድ ጁን ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል። ይህ ማለት ስለዲስትሪክታችን ምን ማለት እንደሆነ ይበልጥ ለማወቅ All In blog post ሁላችንም በጋራ-በአንድነት የሚለው አገናኝ መረብ ይመልከቱ።


ስለ ምዋእለህፃናት ምዝገባ-Kindergarten Registration

ሴፕቴምበር 1/2020 አምስት(5) ዓመት ለሚሞላቸው ልጆች የምዋእለህፃናት ምዝገባ አሁን ተጀምሯል። ተማሪዎች የዲስትሪክቱን የምንባብ እና የሒሳብ ግቦችን በከፍተኛ ደረጃ በማከናወን ከሚታወቁት መካከል የ MCPS ምዋዕለህፃናት ፕሮግራም በአገር አቀፍ ደረጃ በጣም ምርጥ ከሚባሉት አንድኛው እንደሆነ በስፋት የታወቀ ነው። ስኬታማ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኣምራች ዜጋ ለማዘጋጀት እጅግ ወጣት የሆኑት ተማሪዎቻችን ከጅምሩ የበለፀገና ሁለገብ የሆነ የትምህርት ተሞክሮ መቀበል እንዳለባቸው እናምናለን። ልጆቻቸውን ማስመዝገብ የሚፈልጉ ቤተሰቦችን ለመርዳት MCPS አዲስ ኦንላይን ምዝገባ/ምደባ ሂደት ጀምሯል። ቤተሰቦች ሒደቱን በሦስት መንገዶች ሊያጠናቅቁ ይችላሉ፦

  1. ኦንላይን፣ ከዚህ ይጀምሩ የምዝገባ ቅኝት
  2. በስልክ፦ 240-740-5999 በመደወል
  3. በወረቀት ቅጾች-ይህንን የምዝገባ ቅኝት ይሙሉ ወይም ወደ እርስዎ ቤት በፖስታ እንዲላክልዎት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-5999 ደውለው ይጠይቁ።
የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን-State Schools Superintendent Karen Salmon፣ የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ፎል ላይ ትምህርት ቤቶች እንደገና የሚከፈቱበት የመጠባበቂያ እቅድ እንዲኖራቸው መመሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በእኛ በኩል ልጅዎ ከእኛ ጋር እንደሚሆን-እንደምትሆን እያቀድን ነው። ለፎል ስለሚኖርዎት እቅድ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ነገር ግን ልጅዎን ትምህርት ቤት ክፍት በሚሆንበት ጊዜ የሚልኩ ከሆነ፣ እባክዎ አሁኑኑ ያስመዝግቡ(ቧ)ት። ስለ ምዋእለህፃናት ትውውቅ እና ስለመጪው የትምህርት ዓመት ዝርዝሮችን በመጪዎቹ ሣምንቶች እንገልጻለን። የማስመዝገቢያ ማቴሪያሎችን ያገኛችሁ ቤተሰቦች በተቻለ ፍጥነት ቅጾቹን ሞልታችሁ እንድታቀርቡ ትጠየቃላችሁ።

ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የምዋእለህፃናት ፕሮግራም - MCPS Kindergarten Program ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ
ልጅዎን አሁኑኑ ያስመዝግቡ-Enroll Your child Now

ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል ምርጫ

ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል - Student Member of the Board (SMOB) ምርጫ ሜይ 20/2020 ይደረጋል። ለ 43ኛው ተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) የቀረቡት ሁለቱ እጩ ተወዳዳሪዎች Mr. Nick Asante, a junior at Richard Montgomery High School, እና Miss Victoria Kidder, a junior at Col. Zadok Magruder High School ናቸው። ስለ ተወዳዳሪዎቹ የግል ታሪካቸውን ለማንበብ እዚህ ክሊክ ያድርጉ፣ እና ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ አቋማቸውን ለማወቅ ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ-watch this video። ተወዳዳሪዎቹ እጩዎች COVID-19 ስለሚያስከትለው ተጽእኖ የራሳቸውን አስተሳሰብ በመግለጽ እዚህ ቪድኦ ሪኮርድ አድርገዋል። ምርጫውን በሚመለከት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በጠቅላላ ሜይ 20 ሊንኩ በኢሜይል ይደርሳቸዋል-ያገኛሉ።


ስለ LGBTQ+ ቨርቹወል ታወንሆል ሜይ 27 ይካሄዳል

MCPS Pride Town Hall በ COVID-19 ወረርሽኝ ወቅት የ LGBTQ+ ተማሪዎችን ከማህበረሰብ አባላት ጋር የሚያገናኝ ታወንሆል ያካሄዳል። ይህ ቨርቹወል ሁነት ረቡእ፣ ሜይ 27 6 p.m. በ MCPS ድረገጽ እና በ MCPS YouTube የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ይህ ሁነት በሚካሄድበት ወቅት፣ የመድረክ ተናጋሪዎቹ ከ LGBTQ+ ወጣቶች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲሁም ከማህበረሰብ አባላት ጋር ይገናኛሉ፦

  • ሪሶርሶችን እና ድጋፎችን ለማካፈል
  • ለተማሪዎች፣ ለወላጆች እና ለቤተሰቦች ስላሉት ድጋፎች እና ሪሶርሶች ለመነጋገር
  • እንግዶች ድርጅቶች ጋር የጥያቄ እና መልስ ለማካሄድ
ከ "MCCPTA, CASA Ruby, the Montgomery County Family Justice Center, PFLAG, MoCo Pride Center and the MoCo Pride Student Organization" ጨምሮ ከበርካታ ድርጅቶች ተወካዮች በሁነቱ ላይ ይሳተፋሉ።

ተሳታፊዎች "webinar anonymously by using an incognito window in Google Chrome or an InPrivate window in Internet Explorer" ክሊክ በማድረግ ማንነታቸው ሳይገለጽ ለመሣተፍ ይችላሉ meeting link፣“Join a Meeting” prompt በሚለው ላይ በራሳቸው የአውታረመረብ ቅኝት-browser ስም እና ለመጠቀም የሚፈልጉትን ተውላጠ ስም በመግለጽ ለመሣተፍ ይችላሉ።

ተሣታፊዎች ማንነታቸውን ሳይገልጹ በ YouTube እና በ MCPS ድረገጽ መመልከት ይችላሉ።

በኮቪድ - COVID-19 ወቅት ስለ ኮሌጅ የምዝገባ ሒደት መቀኛት

በዘመነ COVID-19 ስለ ኮሌጅ የምዝገባ ሒደት ቅኝት ወላጆች እና ተማሪዎች ይህንን መረጃ ሰጪ ሁነት እንዲመለከቱ ይበረታታሉ። ፕሮግራሙ ትኩረት የተደረገው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየሮች እና ለቤተሰቦቻቸው ነው። ሁነቱ ላይ የተሳፉት እንግዶች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካውንስለሮች እና የኮሌጅ ተወካዮች፣ ስለ ውጤት እና ሪፖርት አሰጣጥ፣ ስለ SAT እና ACT፣ Advanced Placement tests፣ እና ስለ ኮሌጅ ምዝገባ እና ማመልከት ሌሎች ርእሶችን በሚመለከት ውይይት አድርገዋል።


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የ2020-2021 የዓመቱ መምህርት - 2020-2021 MCPS Teacher of the Year

ምናልባት ያላዩት ከሆነ፣ ሜይ 15 የ MCPS Teacher of the Year ቨርቹወል ሁነት በተከበረበት ወቅት ከስላይጎ ሚድል ስኩል መምህርት-Sligo Middle School teacher-Inge Chichester የ"2020–2021 MCPS Teacher of the Year" በመሆን ተሰይማለች። እንጌ ቺቼስተር/ Chichester በስላይጎ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Sligo Middle School አለም አቀፋዊ ጥናት ባለሙያ ናት። እርሷ በ MCPS 19 ዓመት በጀግንነት ያገለገለች ስትሆን፣ በቀጣይነት ለሜሪላንድ የዓመቱ መምህርነት - Maryland Teacher of the Year ለመሆን ውድድሯን ትቀጥላለች። አከባበሩን በዚህ አውታረመረብ መመልከት ይችላሉ።


Important Online Resources: