Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 10, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

በ MCPS ለሚገኙ እናቶች በሙሉ "መልካም የእናቶች ቀን" እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
ስላደረጋችሁት ሁሉ እናመሰግናለን።

ስለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት፤ ቀሪው የትምህርት ጊዜ በሙሉ ትምህርት ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ ገቨርነር ላሪ ሆገን እና የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን (Governor Larry Hogan and State Superintendent of Schools Karen Salmon) ረቡእ፣ ሜይ 6፣ አሳውቀዋል። የትምህርት ቤቶቻችን ህንጻዎች ዝግ ቢሆኑም እንኳ፣ እስከ ጁን 15፣ የመጨረሻው የትምህርት ቀን ድረስ የ MCPS ኦንላይን ትምህርት ይቀጥላል።

የሜሪላንድ የትምህርት ማካካሻ-ማገገሚያ እቅድ የ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ "COVID-19 pandemic በትምህርት ቤት ሲስተማችን ላይ ከዚህ በፊት በማናቸውም ክስተቶች ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የትምህርትን መልክ-landscape of education የተቀየረ መሆኑ ተጠቅሷል። በዚህ ደረጃ የሚከሰቱ ሁኔታዎች ለተማሪዎቻችን ትምህርት በምንሰጥበት ሁኔታ ላይ በእርግጠኝነት ተፅእኖ ያደርጋሉ። በመጪዎቹ ወራት ተማሪዎች እና ሠራተኞች በሆነ አይነት ወደ ትምህርት ቤት ህንፃዎቻችን መመለስ እንደሚችሉ እጅግ በጣም ተስፋ እያደረግን ነው። ቢሆንም ግን፣ ከዚህ በፊት ትምህርት ቤት ምን ይመስል እንደነበረ ከምናውቀው በጥብቅ የተለየ እንደሚሆን እናውቃለን። ለተማሪዎቻችን፣ ለሠራተኞች እና ለቤተሰቦች ፊት-ለ-ፊት በአካል መገናኘት፣ እና መተባበር አለመቻል በጣም ከባድ ነው። ትምህርት ቤቶች የካውንቲአችን እና የማህበረሰባችን ልብ-ማእከሎች ናቸው። ተማሪዎችን ከማስተማር በተጓዳኝ የተማሪዎቻችንን አካላዊ፣ ማህበራዊ-ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ፍላጎቶቻቸውን ጭምር መርዳት እንደምንቀጥል እንዲያውቁም እንፈልጋለን።

ብዙ ነገሮች የተለወጡ ቢሆንም፣ ጥቂት ነገሮች እንደቀድሞው አንድ አይነት ናቸው። በጣም የሚገርሙ ተማሪዎቻችን እና ሠራተኞቻችን መልካም ምሳሌ-ሞዴል የመሆንን አስፈላጊነት በማሳየት ደግነት እና ርኅሩህነትን ፣ እና በጥልቀት የመሣተፍ እና የግንኙኘት ደረጃ የፈጠራ ችሎታቸውን በጋለ ስሜት እየተጠቀሙ ናቸው። ተማሪዎች እና ሠራተኞች ስለሚያደርጉት ትጋትና ጥረት በአካባቢ እና በብሔራዊ ደረጃ እውቅና እያገኙ ናቸው— እንደ Michael Doggett ለመሣሰሉ መምህራን ከ "Box Tops for Education and Chance the Rapper" በቅርቡ የ $30,000 ሽልማት አሸንፏል። Mr. Doggett፣ እና የ MCPS መምህራን እና ሠራተኞችን በሙሉ ተማሪዎቻችንን ለመደገፍ ስለምታደርጓቸው ነገሮች በጠላላ እናመሰግናለን።

ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ስለ MCPS ሦስተኛ ምዕራፍ-Phase III ኦንላይን ትምህርት፣ ስለ ምረቃ በዓል አከባበር እና ስለ ዲስትሪክቱ የማካካሻ እቅድ በርካታ ወቅታዊ ጠቃሚ መግለጫዎችን ያካትታሉ። ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው ማቴሪያሎችን ለመቀበል እና ለመመለስ የሚያሳዩትን ጉጉት እናደንቃለን። የእኛ ቅድሚያ ትኩረት በተለይም የህብረተሰብን ጤና የመጠበቅ ጥንቃቄ ቁጥጥር ባለበት በዚህ ወቅት ጤንነትን መጠበቅ ላይ ነው። የዓመቱን የተግባር እንቅስቃሴዎች እንዴት መከናወን እንዳለባቸው ጠቅላላ እቅድ እየሠራን ስለሆነ በመጪዎቹ ሣምንታት ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ ዝርዝሮቹ ይገለጻሉ።

እባካችሁ እርስበርስ በመደጋገፍ ጤንነታችሁን ጠብቁ።
እነዚህን ቀስ በቀስ እያደጉ የመጡትን ክስተቶችና ሁኔታዎችን በምንጋፈጥበት ወቅት በቀጣይነት የሚያደርጉትን ድጋፍ እናደንቃለን።

Jack R. Smith, Ph.D. 
Superintendent of Schools



የ MCPS ሦስተኛ ምእራፍ - Phase III ኦንላይን ትምህርት

ሜይ 18፣ ወደ ሦስተኛ ምእራፍ - Phase III ኦንላይን ትምህርት እንሻገራለን። የትምህርት ዓመቱ እየተገባደደ ባለበት በዚህ ቀጣይ ምእራፍ የእኛ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ለሁሉም ተማሪዎች አዲስ ትምህርት መስጠት እና የእነርሱን ማህበራዊ-ስሜታዊ ፍላጎቶችን ድጋፍ መቀጠል ይሆናል። የማካካሻ እና ተመልሶ የመግባት እቅድን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር አብረን እንሠራለን (የሠራተኛ ማህበራት፣ የሥራ ባልደረቦች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት)። ስለ ሦስተኛው ምእራፍ - Phase III ኦንላይን ትምህርት በመጪዎቹ ቀኖች ይበልጥ መረጃዎች ይሰጣሉ።


የምግብ አገልግሎት

የቁርስ፣ ምሣ እና እራት ምግቦችን በሣምንት አራት ቀኖች ከ50 በላይ ጣቢያዎች ላይ መስጠት እንቀጥላለን። ለቤተሰቦች የሣምንት መጨረሻ የምግብ ከረጢቶችን ለመስጠት ከ "Manna Food Center እና Women Who Care Ministries" ጋር ትብብራችንን እንቀጥላለን። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል። በተጨማሪ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምግብ ካውንስል-Montgomery County Food Council የግንኙነት መረብ-interactive map የምግብ እርዳታ ሰጪዎችን አዘጋጅቷል። እንዲሁም በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቅማጥቅሞች ማመልከቻ ጣቢያዎችን የግንኙነት መስመር ዘርግቷል። በቦታ/ጣቢያ፣ የእርዳታ ምግብ አይነት፣ ተደራሽነት እና በርካታ ሌሎች ልዩ ገፅታዎችን ማፈላለግ ያስችላል። ይህ መተግበሪያ ቤተሰቦች በአካባቢያቸው የሚገኙትን ሪሶርሶች በፍጥነት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።

ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ

ማሳሰቢያ፦ ማክሰኞ፣ ሜይ 12 የትምህርት ቦርድ ስለ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የውጤት እና ሪፖርት አሠጣጥ በመወያየት እርምጃ ይወስዳል። እቅዱ-ፕላኑ ስለ አጠቃላይ የሴሚስተር ውጤት፣ ስለ አማካይ ውጤት (GPA) ስሌት፣ እና አጠቃላይ ውጤት እንዴት በትራንስክሪፕቶች ላይ ሪፖርት እንደሚደረግ ያካትታል። ስብሰባው በ 11:30 a.m. የሚካሄድ ሲሆን ቀጥታ ስርጭቱ በ በ MCPS ድረ-ገጽ እና በ MCPS-TV ይተላለፋል። እባክዎ ይህንን ጠቃሚ ውይይት ከፍተው ያዳምጡ። ቦርዱ የማጠቃለያ እርምጃ-ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ለማህበረሰቡ ወቅታዊ መረጃ እንሰጣለን።

MCPS ስለማርክ መስጫ ክፍለጊዜው ተማሪ “Pass” ውጤት ለማግኘት ይችል-ትችል እንደሆነ ለመወሰን መመዘኛ-framework አዘጋጅቷል። ማሳሰቢያ፦ ይህ መመዘኛ-framework የሚያተኩረው ስለ ተማሪው(ዋ) አጠቃላይ ትኩረትና ተሳትፎ አስፈላጊነት፣ እና የተሰጡ የቤት ሥራዎችን ማጠናቀቅ፣ ትምህርት ማግኘትን በተግባር ለማሳየት መቻል፣ ከመምህራን ጋር በርካታ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም መገናኘት፣ እና የመምህራን ሙያዊ ግምገማ የመሣሰሉ በርካታ መመዘኛዎችንም ይጨምራል። በዚህ ማእቀፍ ውስጥ፣ መምህራን የቤት ሥራዎች መሠራታቸውን ለመከታተል እና ለተማሪዎች ግብረመልስ ለመስጠት የእነርሱን "gradebook" መጠቀማቸውን ይቀጥላሉ። ነገር ግን ተማሪዎች እና ወላጆች ከለመዱት አይነት በ "parent portal" ላይ ከተዘረዘረው የውጤት አሰጣጥ የተለየ እንደሚሆን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። በ "portal" ላይ ስላሉት ውጤቶች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ የልጅዎን አስተማሪ ያነጋግሩ።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መሃከለኛ ጊዜ/የሽግግር ጊዜ ሪፖርቶች-Interim Reports for Secondary Students
ስለ 4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ "Pass/Incomplete" የሽግግር መስፈርት ማዕቀፍ እንዳለ ሆኖ፣ MCPS በዚህ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ኮርስ የማለፍ አደጋ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች በተዘጋጀ መስፈርት መሠረት መሃከለኛ ጊዜ/የሽግግር ጊዜ ሪፖርት-Interim Report ይልክላቸዋል። የሲንየሮች መሃከለኛ ጊዜ/ሽግግር ጊዜ ሪፖርት ሜይ 11 በሚውልበት ሣምንት የሚላክ ሲሆን፣ ከ 6ኛ-11ኛ ክፍሎች ለሚገኙ ተማሪዎች ሜይ 18 በሚውልበት ሣምንት ውስጥ ይላካል።


የማካካሻ እቅድ-Recovery Plan

የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ሜይ 6፣ የማካካሻ እቅድ አስተላልፏል። ሪፖርቱን እዚህ መመልከት ይችላሉ። የስቴት ሪፖርቱ ይዘት የህብረተሰቡ የጤና መሻሻል የሚታይበት ሁኔታ እያደገ መሄድን ተከትሎ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አማራጮችን ለማዘጋጀት እና ለመገምገም ለአካባቢ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች መመሪያ እንደሚሆን ታስቦ ነው። MCPS የትምህርት ቤት ሲስተምን ትምህርታዊ እና ሥራ የሚካሄድበት ፍላጎቶችን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በተለያየ ደረጃ ሁኔታዎችን በማገናዘብ አመቺ የሚሆን በተለይ ዲስትሪክቱን የሚመለከት የማካካሻ እቅድ ላይ እየሠራ ነው። በመጪዎቹ ሣምንቶች የበለጠ ዝርዝር መረጃ እንሰጣለን።


የ 2020 ተማሪዎች ምረቃ እና የመመረቂያ እቅድ

በዚህ ዓመት የ 2020 ተመራቂ ተማሪዎች ስላከናወኗቸው ሥራዎች በሙሉ MCPS አድናቆት ይሰማዋል። በቅርቡ፣ ሲንየሮች እና ቤተሰቦቻቸው ስለምረቃ በአል አከባበር ምርጫዎቻቸውን ለማወቅ ቅኝት አድርገናል።
ከ 8,000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች በተገኘ ግብረመልስ ላይ በመመርኮዝ የተቀላቀለ የምረቃ ይዘት እንዲሆን ወስነናል። ጁን ቀደም ያሉ ቀኖች ላይ ለ 2020 ተመራቂ ተማሪዎች እና ለቤተሰብ በጠቅላላ "universal virtual graduation" እናካሄዳለን። ወደፊት ለህብረተሰብ ጤንነት አሳሳቢ የሆነው በብዛት የመሰባሰብ እገዳ ከተነሣ በኋላ በአካል ተገኝቶ የሚከበርበት ሥነ-ሥርአቶችን "in-person ceremonies" እናካሄዳለን። በሚመጡት ቀናት ስለ ቨርቹወል የምረቃ አከባበር "virtual commencement celebration" በዝርዝር እናሳውቃለን። በተጨማሪ፦ ከ ሜይ 14 - 22 ሲንየሮቻችንን በማህበራዊ ሚድያ ላይ እናከብራለን። ተማሪዎች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከጨረሱ በኋላ ስለሚኖራቸው እቅድ—ወደ ኮሌጅ ይሄዱ እንደሆን፣ ወይም ተለማማጅ ሆነው ይሰሩ እንደሆን፣ ወይም በቀጥታ ወደ ሥራ ግብረሃይል ይቀላቀሉ እንደሆነ እቅዳቸውን አጫጭር ቪድኦ ወይም ፎተግራፎችን በ Twitter እንዲያካፍሉ እናበረታታለን። ሠራተኞች፣ ወላጆች፣ ተመራቂዎች እና የቤተሰብ አባላት ለሲንየሮች የመልካም ምኞት መልእክቶቻችሁን በቪድኦ እና በፎተግራፍ እንድታበረክቱላቸው እናበረታታለን። ይህንን ሃሽታግ #MCPSClassof2020 መጠቀም እንዳለብዎት አይዘንጉ። ቪድኦ ወይም ፎተግራፍ በኢ-ሜይል ለመላክ ከፈለጉ በዚህ pio@mcpsmd.org ይላኩ።


በኮቪድ - COVID-19 ወቅት ስለ ኮሌጅ የምዝገባ ሒደት መቀኛት

MCPS ዓርብ፣ ሜይ 15 በኮቪድ - COVID-19 ወቅት ስለ ኮሌጅ የምዝገባ ሒደት ቅኝት የመረጃ ልውውጥ ውይይት "informational talk show" ያቀርባል። ይህ ፕሮግራም በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ የሚለቀቅ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየሮች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ያተኩራል። እንግዶቹ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካውንስለሮች እና ከኮሌጅ ተወካዮች የተወጣጡ ናቸው። አርእስቶቹ የሚያካትቱት ስለ ማርክ እና የሪፖርት አሠጣጥ፣ ስለ SAT እና ACT፣ Advanced Placement tests፣ ሌሎች የኮሌጅ ምዝገባ እና ማመልከቻ ርእሶች ናቸው። ውይይቱ በቅድሚያ ሪኮርድ የተደረገ ስለሚሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየሮች እና ቤተሰቦቻቸው/ሞግዚቶቻቸው የዝግጅቱ ተሳታፊዎች እንዲመልሱ የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ጥያቄዎችን እዚህ ለማቅረብ ይችላሉ። በስፓንሽ ቋንቋ ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎ እዚህ ያቅርቡ።

ዝግጅቱ ሰኞ እና ዓርብ ቀን 8 p.m. ላይ በ "Comcast channel 34፣ Verizon channel 36 እና RCN channel 89" በድጋሚ ይተላለፋል።
ውይይት የሚያቀርቡ እንግዶች፦  Wanda Canales, director of admissions and recruitment at Washington Adventist University; Calvin Wise, director of recruitment at Johns Hopkins University; James Massey, director of undergraduate admissions at the University of Maryland, College Park; Alphonso Garett, director of admissions and recruitment at the University of Maryland, Eastern Shore; ከ MCPS ተወካዮች ናቸው።

በስፓንሽ ቋንቋ ሰኞ እና ዓርብ በ 6:30 p.m. በ "Comcast channel 33፣ Verizon channel 35 እና RCN channel 88" በድጋሚ ይተላለፋል። ውይይት አቅራቢ እንግዶች፦ Maria Garcia, ESOL counselor with MCPS; Wanda Canales, director of admissions and recruitment at Washington Adventist University; and Alexandra Gonzales, admissions representative at Montgomery College ናቸው።


Important Online Resources: