Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 06, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


አስፈላጊ ወቅታዊ መረጃ

የተወደዳችሁ ወላጅች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

የሜሪላንድ የህዝብ ትምህርት ቤቶች-(ሜሪላንድ ፐብሊክ ስኩልስ) ለ2019 - 2020 የትምህርት ዓመት ቀሪውን ጊዜ በሙሉ ዝግ እንደሚሆኑ ዛሬ (ሜይ 6) ገቨርነር ላሪ ሆገን እና የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን-Governor Larry Hogan and State Superintendent of Schools Karen Salmon አሳውቀዋል። ለሜሪላንድ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ጤንነትና ደህንነት ሲባል ይህ ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ በጥብቅ እናምናለን። ይህ ዜና የማይጠበቅ ባይሆንም፣ በትምህርት ቤቶች ለመማርና ለማስተማር ለመሥራት አብረን ባለመሆናችን፣ በአትሌቲክስ እና በሥነጥበብ ሁነቶች ላይ ለመሣተፍ አለመቻል እና የትምህርት ዓመት መጨረሻ ፕሮግራሞችን እና የምረቃ ሥነስርአቶችን በጋራ ለመሳተፍ ያለመቻሉ የብዙዎችን ልባዊ ሃዘን እና ተስፋ መቁረጥ ሊመልስ አይችልም ይሆናል።

በዚህ ሣምንት መጨረሻ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እና ኦንላይን ስለሚሰጡ ትምህርቶች፣ ስለምረቃ፣ ፕሮም፣ የፕሮሞሽን ስነ ስርአቶችን እና ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት የቀጣይ እርምጃዎችን ወቅታዊ ይዞታ እንገልጻለን። እነዚህን የመገናኛ ብዙሃን አውታረ-መረቦቻችንን እንድትመለከቱ እናበረታታለን፦
coronavirus webpage
frequently and sign up to receive important alerts through the Alert Montgomery system

እባካችሁ እርስበርስ በመረዳዳት ጤንነታችሁን ጠብቁ። የማህበረሰባችንን ጤንነት እና ደህንነት ለመደገፍ MCPS በርካታ ሪሶርሶችን አዘጋጅቷል-አዳብሯል። ሪሶርሶቹን እዚህ መመልከት ይችላሉ። በመተዛዘን እና በመደጋገፍ በጋራ ተባብረን ከሠራን ይህንን እጅግ በጣም አስከፊ ጊዜ ልናልፈው እንችላለን።

ከአክብሮት ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools