Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 03, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

 በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ኦንላይን ትምህርት ወደ 4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ እና ምዕራፍ II (ኤፕሪል 20–ሜይ 15) ሽግግራችንን ስንቀጥል ስለሚያደርጉት ድጋፍ በሙሉ እናመሰግንዎታለን። በጉዞአችን ላይ በርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እያጋጠሙን መልሰናቸዋል-መፍትሔ አግኝተንላቸዋል፣ እና በርካታ ሠራተኞቻችን እያደረጉ ያሉትን አዳዲስ ፈጠራዎችንመሠማራታቸውን እና የሚያበረታቱ ነገሮችን በኦንላይን መድረኮቻችን ላይ ማየት እንቀጥላለን። ተማሪዎቻችን እንዴት ጽኑ እና ፈጠራ የሚችሉ መሆናቸውን ማሳየታቸውን ይቀጥላሉ፣ ከኦክላንድ ተሬስ ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት - Oakland Terrace Elementary School አንድ ቡድን እንዴት ራሳችንን ለመግለጽ እና እርስበርሳችን ለመበረታታት ስነጥበብን መጠቀም እንደምንችል ያስተምሩናል።

ተማሪዎቻችንን፣ ቤተሰቦችን እና ሠራተኞቻችንን ቶሎ ለማየት እንደምንችል ተስፋ እያደረግን፣ የትምህርት ቤት ህንጻዎቻችን ምንም ያህል ጊዜ ተዘግተው ቢቆዩ እንኳ ጠንካራና ጤነኛ ኦንላይ ትምህርት መስጠት እንደምንችል በማረጋገጥ ስራዎቻችንን እንቀጥላለን። ከማህበረሰባችን የምናገኛቸውን ግብረመልሶች እና የዳታዎችን ትንታኔ መሠረት በማድረግ እቅዶቻችንን በማጣራት እና በማሻሻል እንቀጥላለን።
እባክዎ እነዚህን ጠቃሚ የእለታዊ ይዞታ መግለጫዎችን ያንብቡ። በ 4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ተማሪዎች “Pass” የሚለውን የማለፊያ ውጤት ለማግኘት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርት እና የተማሪዎችን ተሳትፎ እንዴት እንደምንቆጣጠር ጭምር የተለያዩ አርእስቶችን ያካትታሉ።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools


ማውጫ

| የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ 4 ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማርክ-ውጤት መስጫ መስፈርት | ለኤለመንተሪ ትምህርት ቤት 4ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የውጤት አሰጣጥ |የኤለመንተሪ ሳይንስ | የተማሪን ተሳትፎ መቆጣጠር፦ | ስለ MSDE የቀጣይ ትምህርት እቅድ | በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ስለ ርቀት ትምህርት መሰል-ቨርቹወል ውይይት-Virtual Discussion on Remote Learning in MCPS ምናልባት አምልጦዎት ከሆነ፦ | ወላጅ/የማህበረሰብ በጎፈቃደኞች እና በተወሰነ-ጊዜ አስጠኚዎች-In-Session Tutoring | በቤተሰብ የሚነሣ የጠብ እና ጭቅጭቅ ግንዛቤ እና መከላከል |


የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ 4 ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማርክ-ውጤት መስጫ መስፈርት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለ4ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ተማሪዎች “Pass” የማለፊያ ውጤት እንዴት እንደሚያገኙ ሠራተኞች ለመወሰን የሚያስችላቸውን መስፈርት ማእቀፍ-framework አዘጋጅቷል። የእኛ አውታረ-ሥርዓት/framework የሚያተኩረው ተማሪዎች የተሰጣቸውን ጠቃሚ የቤት ሥራ በመሥራት ላይ ያሳዩትን አጠቃላይ ትጋትና ተሳትፎ ግልፅና ትክክለኛ ውጤቶችን/ደረጃዎችን ይሆናል። የቤት ሥራዎችን ማጠናቀቅ፣ መማራቸውን ማረጋገጥ፣ በተለያዩ በርካታ መንገዶች ከአስተማሪዎቻቸው ጋር መሥራት፣ እና ከአስተማሪዎቻቸው የሚሰጥ ሙያዊ ግምገማ የመሣሰሉትን በርካታ መስፈርቶች ይጨምራል። መምህራን ለተማሪዎች የተሰጡትን የቤት ሥራዎች ለመከታተል እና ግብረመልስ ለመስጠት "gradebook"ን እንደ መሣሪያ መጠቀም ይቀጥላሉ፣ ነገር ግን በ "parent portal" የሚታይ አይነት የውጤት አሰጣጥ መደቦች፣ ፐርሰንቶች፣ እና በፊደል ማርክ አሰጣጥ የተለመደው አይነት “normal” የማርክ ተመሣሣይ ትርጉም እንደማይኖረው ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ማለፊያ ውጤት ለመወሰን የሚጠቅሙ ተጨማሪ ሌሎች በርካታ መስፈርቶች መለኪያዎችም አሉ (ከዚህ በታች ያለውን ቻርት-ሠንጠረዥ ማየት ይችላሉ)።

ለማርክ አሠጣጥ መሥፈርት የመመዘኛዎች-አውታር ከዚህ በታች ይገኛል፦

ተማሪ “PASS” ውጤት ለማግኘት ቢያንስ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበ(ባ)ት፦

1.

የቤት ሥራ ማጠናቀቅ፦ የቤት ሥራዎቻቸውን በአስተማማኝነት ማጠናቀቅ (ቢያንስ የቤት ሥራዎችን 50 ፐርሰንት)

2.

ይዘት እና ክህሎቶች፦ የቤት ሥራ ጽንሰሃሳቦች ወይም የክህሎት ትግበራ ውጤቶች፣ መመዘኛ ወይም ሌላ ርእሶች ወይም ትእዛዞች

3.

መሣተፍ-ትጋት፦ በአስተማሪዎች የቁጥጥር መከታተያ መደበኛ ሆነው መሣተፍ፣ ከአስተማሪ ጋር ቀጣይ የትምህርት ግንኙነት ማድረግ፣ ወይም እንደ discussion boards ወይም digital classroom የመሣሠሉ ሌሎች እቅስቃሴዎች ላይ በመደበኛነት መሣተፍ

4.

የአስተማሪ ሙያዊ ግምገማ፦ በወረርሽኙ ምክንያት ያለውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪው(ዋ)ን የሚጠቅሙ ያሉትን ማስረጃዎች እና የተማሪን አጠቃላይ የሥራ ይዘት መመርኮዝ

አጠቃላይ የሴሚስተሩ ውጤት ስለሚሠላበት ሁኔታ፣ የአማካይ ውጤት አሰጣጥ መስፈርት (GPA) ወይም በትራንስክሪፕቶች ላይ ማርኮች እንዴት ሪፖርት መደረግ እንዳለባቸው ገና ውሳኔ ላይ ያልተደረሰ መሆኑን ለቤተሰቦች ማስታወስ እንፈልጋለን። የማጠቃለያ-የመጨረሻውን እቅድ የትምህርት ቦርድ ሜይ 12/2020 በሚኖረው የሥራ-የቢዝነስ ስብሰባ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል። ስብሰባው በ MCPS ድረ-ገጽ (www.montgomeryschoolsmd.org) እና በ MCPS-TV (Comcast 34, Verizon 36 and RCN 89) በቀጥታ ይተላለፋል። ቦርዱ የመጨረሻ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ለማህበረሰቡ ወቅታዊ መረጃ እንሰጣለን።


ለኤለመንተሪ ትምህርት ቤት 4ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የውጤት አሰጣጥ

ለ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በፊደል ማርክ-ውጤት አይሰጥም። ትኩረት የሚሰጠው በትምህርት ላይ የተማሪዎችን ተሳትፎ በማዳበር እና በተቻለ መጠን ከበርካታ ተማሪዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ ላይ ይሆናል። ተማሪዎች የትምህርት ትጋት፣ እርምጃ ማሳየታቸውን እና የትምህርት ዓላማን እያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ በእኛ በኩል፦

  1. ለተማሪዎች የተለያየ አይነት የመማሪያ-የትምህርት መልመጃዎችን እድሎችን መስጠት
  2. ተለይተው የታወቁ ትኩረት ማድረግ በሚያስፈልጋቸው ነገሮች ዙርያ ከተማሪዎች እና ከወላጆቻቸው/ከሞግዚቶቻቸው ጋር ክትትል ማድረግ
  3. ተማሪዎች በአካደሚያዊ እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ
  4. ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት በሚመለሱበት ጊዜ፣ በየትኛው ችሎታቸው ላይ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው እንዲያውቁ፣ እና በሚቀጥለው ክፍል ትምህርታቸው ላይ እንዴት ማሳተፍ እንዳለባቸው ለአስተማሪዎች መረጃ-ኢንፎርሜሽን መስጠት

የኤለመንተሪ ሳይንስ

የሳይንስ ሙከራዎች ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ከሜይ 4/2020 ጀምሮ በ "myMCPS classroom" ላይ ይኖራሉ። ለቤተሰብ ተጨማሪ የሳይንስ ሙከራዎች ሜይ 11/2020 በሚውልበት ሣምንት ይኖራሉ። የሳይንስ ሙከራዎቹ ለተማሪዎች እና ለቤተሰብ በቀጣይነት ትምህርት እንዲሆኑ የተነደፉ-የተዘጋጁ ናቸው።


የተማሪን ተሳትፎ መቆጣጠር፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አጠቃላይ-ሁለገብ የተማሪ ተሳትፎ መቆጣጠሪያ-ክትትል የማድረግ ፕሮግራም -ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ይኼውም በርካታ የመረጃ-ዳታ ምንጮችን የሚያካትት እና በዲስትሪክቱ ውስጥ የእያንዳንዱን ተማሪ እና የቤተሰብ ፍላጎት ለማሟላት ሠራተኞችን እና ሪሶርሶችን ማደራጀት፣ ማሰማራት፣ ማንቀሳቀስን ያካትታል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪ ተሳትፎ-ስምሪት እቅድ ሦስት ምዕራፎች ይኖሩታል—የእያንዳንዱን ተማሪ ተሳትፎ በትምህርት ቤት እና በዋናው ጽ/ቤት ደረጃ ክትትል ማድረግ እና ትንታኔ መስጠት፣ ተማሪዎችን መድረስ እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት ጉዳዮችን የመከታተል እና የመምራት እቅዶችን መፍጠር "case management action plans" ፣ እና የተማሪን ተሳትፎና ትጋት ጥራት በትንታኔ እና በቁጥር ማሳየት። በቀጣይነት ትምህርት ፕሮግራም መሣተፍ በብዙ መንገዶች ሊከናወን እንደሚችል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ተማሪዎች እና ወላጆች/ሞግዚቶች (በተማሪዎች ምትክ) ከአስተማሪዎች ጋር በኢ-ሜይል፣ በስልክ፣ በቴክስት እና በጽሑፍ ወረቀት ፓኬት ቁሳቁሶች አማካይነት ይገናኛሉ። ሁሉም ተማሪዎች መገኘታቸውን-መሳተፋቸውን-መከታተላቸውን በመቆጣጠሪያ ዳታ ላይ ማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት Visit our Continuity of Learning የሚለውን ይመልከቱ።


ስለ MSDE የቀጣይ ትምህርት እቅድ

የሜሪላንድ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች በጠቅላላ ስለ ቀጣይ ትምህርት እቅድ ለሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ኤፕሪል 24/2020 እንዲያቀርቡ ይፈለጋል። የ MCPS የትምህርት ቀጣይነት እቅድ አሁን ስላለው ሁኔታ የሚገልጽ ግብረመልስ እና ዳታዎችን በማገናዘብ በየጊዜው የትምህርት እቅዱ ስለሚዳብርበት ሁኔታ ወቅታዊ እደሚደረግ ይገልጻል። እባክዎ አሁን ያለውን ወቅታዊ የቀጣይ ትምህርት እቅድ ለማወቅ ይህንን አገናኝ this link ይመልከቱ።


በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ስለ ርቀት ትምህርት መሰል-ቨርቹወል ውይይት-Virtual Discussion on Remote Learning in MCPS ምናልባት አምልጦዎት ከሆነ፦

የ MCPS ሠራተኞች ኤፕሪል 27 በርካታ አርእስቶችን እና ስለ MCPS ኦንላይን ትምህርት ሁለተኛው ምእራፍ-Phase II ከማህበረሰብ የተነሱ በርካታ ጥያቄዎችን በመመለስ ቨርቹወል ውይይት አካሄደዋል። ምናልባት ያልሰሙ ከሆነ ይህንን አስፈላጊ-ጠቃሚ ውይይት እዚህ መመልከት ይችላሉ።


ወላጅ/የማህበረሰብ በጎፈቃደኞች እና በተወሰነ-ጊዜ አስጠኚዎች-In-Session Tutoring

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የበርካታ ወላጆች እና የማህበረሰብ በጎፈቃደኞች እንዲሁም ከውጭ የግል መምህራን ወይም ተማሪዎችን የሚያስጠኑ/ትዩተሮች ስለሚሰጡት ድጋፍ MCPS ልባዊ አድናቆት አለው። በመደበኛው የሥራ ጊዜ፣ እነዚህ በጎፈቃደኞች የ MCPS ሠራተኞች እየተቆጣጠሯቸው የተማሪዎቻችንን ፍላጎት ድጋፍ ያደረጉ ቢሆንም፣ አሁን እየተካሄደ ባለው የርቀት ማስተማር ወቅት የእኛ መምህራን እና አስተዳደር ለተማሪዎች ድጋፍ በመስጠት ላይ ማተኮር አለባቸው። ለዚህ ትምህርት ዓመት በቀሪው ጊዜ የእኛን ኦንላይን የማስተማር ተግባር ድጋፍ ለመስጠት በጎ ፈቃደኞች እና ተማሪዎችን የሚያስጠኑ/ትዩተሮች አይፈቀድላቸውም። ይህ ጥረት የሚደረገው ፈቃድ የማግኘት እና ህግ የማክበር ጉዳዮችን በተመለከተ ሠራተኞቻችንን እና ተማሪዎቻችንን (እና በጎፈቃደኞችን) ለመጠበቅ-ለመከላከል ነው። በሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎፈቃደኞች ማእከል ዝርዝር ውስጥ ያሉትን ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ለመድረስ-ለማነጋገር የሚፈልግ-የምትፈልግ ማንኛውም የ MCPS ማህበረሰብ አባል ይህንን ማድረግ ይችላል-ትችላለች www.montgomeryserves.org ድረ-ገጽ አብዛኛዎቹ እነዚህ ድርጅቶች የተማሪዎችን እና የቤተሰቦችን ፍላጎቶች የሚደግፉ-የሚረዱ ናቸው። ብዙ ሳይቆይ በጎፈቃደኞቻችንን በህንፃዎቻችን ዳግም እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እንደምንችል ተስፋ እናደርጋለን።


በቤተሰብ የሚነሣ የጠብ እና ጭቅጭቅ ግንዛቤ እና መከላከል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ-Montgomery County ስለ ቤተሰብ ጭቅጭቅ ጠብ እና ረብሻ ግንዛቤ ስለመስጠት እና መከላከል አዲስ ዘመቻ ጀምሯል፣ ይሄውም የተነደፈው በየቤታችሁ ቆዩ - "stay-at-home order" በተባለበት ወቅት የቤተሰብ ጭቅጭቅ ጠብ እና ረብሻ ለሚያጋጥማቸው የካውንቲው ነዋሪዎች ድጋፍ ለመስጠት እና ለማሳወቅ ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቤተሰብ ፍትህ ማእከል- Montgomery County Family Justice Center (FJC) በወረርሽኙ ጊዜ ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት ይቀጥላል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቤተሰብ ፍትህ ማእከልን- Montgomery County Family Justice Center (FJC) በዚህ ስልክ ቁጥር፦ 240-773-0444 ወይም በዚህ ኢሜይል፦ safe@montgomerycountymd.gov ለማግኘት ይቻላል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ከባድ ችግር-ቀውስ ማእከል በየቀኑ 24 ሠዓት በሳምንት ሰባቱንም ቀን ክፍት ስለሆነ በዚህ የስልክ ቁጥር 240-777-4000 ለማግኘት ይቻላል-The Montgomery County Crisis Center is open 24 hours a day, seven days a week and can be reached at 240-777-4000

county safety table


Important Online Resources: