Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: April 26, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የኦንላይን ትምህርት ሌላኛውን ሣምንት ለመጀመር እየተዘጋጀን፣ በተማሪዎቻችን እና በሠራተኞቻችን ጥንካሬ፣ ፅናት እና የፈጠራ ችሎታ እየተደነቅሁ ነኝ። ለማስተማር እና ለመማር አዲስ አይነት ዘይቤዎችን በመቀየስ ይህንን ከባድ ጊዜ በፅናት እየተወጡት ይገኛሉ።

ተማሪዎቻችን በማህበረሰባችን ውስጥ በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉትን ለመርዳት እና እርስበርሳቸው ለመደጋገፍ ያሳዩትን የተነሣሽነት መንገዶች በማየት እጅግ እኮራባቸዋለሁ። ባለተሰጥኦ፣ የፈጠራ ችሎታ እና ሩህሩህ የሆኑ ተማሪዎቻችን ለጤና እና ሌሎች በጣም ለሚያስፈልጋቸው ሠራተኞች፣ የግል መከላከያ ቁሳቁሶችን (PPE) እየሠሩ የምግብ እርዳታዎችን በመሰብሰብ እና መሰል/ቨርቹወል ፕሮም በማደራጀት ፣ እና ታናናሽ ተማሪዎችን በ መሰል/ቨርቹወል አዳዲስ ችሎታዎችን እያስተማሩ ሰንብተዋል

ለማስታወስ ያህል፦ አሁን እኛ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ የትምህርት ቀጣይነት ፕላን እየተሸጋገርን እንገኛለን (ኦንላይን መማር/በርቀት ማስተማር)። በመጀመሪያው ምዕራፍ የተተኮረው ተማሪዎች እና ሠራተኞች በርቀት ትምህርት መማርና ማስተማርን እንዲለማመዱ ማመቻቸት እና በ3ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜን በማጠናቀቅ ላይ ነበር። በሁለተኛው ምዕራፍ፦ የእኛ ግብ ይበልጥ ቀጥተኛ የሆነ አዲስ ትምህርት መስጠት እና ቀጣይ የተማሪዎች ተሳትፎ ላይ ያተኩራል።የትምህርት ዓላማዎችን በማሳካት ላይ ትኩረታችንን እንቀጥላለን፣ ተማሪዎች መገልገያዎችን እና ሪሶርሶችን በትክክል እንዲያገኙ ማመቻቸት፣ እና ተማሪዎች የሚፈልጉትን አካደሚያዊ፣ ማህበራዊ-ስሜታዊ ድጋፍ መስጠት ላይ እናተኩራለን።
በሁለተኛው ምዕራፍ ወቅት የኤለመንተሪ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስለሚሰጥበት ሁኔታ በሚቀጥለው ሣምንት የበለጠ መረጃ እናካፍላችኋለን።

በጋራ መሥራታችንን ከቀጠልን፣ እርስበርሳችን ከተደጋገፍን፣ እና የኮሮናቫይረስ-COVID-19 በማህበረሰባችን ላይ እያደረሰ ያለውን አሰቃቂነት ለመቀነስ የየራሳችንን ድርሻ ከሠራን፣ በግልም ሆነ እንደትምህርት ቤት ዲስትሪክት ከዚህ ሁኔታ ውስጥ የተሻልን እና ጠንክረን እንደምንወጣ እምነት አለኝ።

እባክዎ ጥቂት ደቂቃዎችን ወስደው ከዚህ በታች የሚገኙትን-ወቅታዊ ይዞታ መግለጫዎችን ያንብቡ። ስለ ማርክ አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ፣ ስለ አዲስ የ MCPS ተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ፣ ስለሲንየሮች የመጨረሻው የትምህርት ቀን፣ እና ለጠቅላላ ቤተሰብ የሚሆን አዲስ የጤንነት እንቅስቃሴ መገልገያዎች የመሣሠሉትን በርካታ አርእስቶችን ይሸፍናሉ። ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 28/2020 ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች የትምህርት ቀን መሆኑን ለቤተሰቦች ማስታወስ እንፈልጋለን። ስለ ኮሮናቫይረስ እና ኦንላይን ትምህርት የሚተላለፉ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ሪሶርሶችን በሚመለከት ድረ-ገፆቻችንን ዘወትር እንድትመለከቱ-እንድትከታተሉ-እንድታነቡ እናበረታታለን።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.  
Superintendent of Schools



ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ

በኤፕሪል 19 የማህበረሰብ ደብዳቤያችን ላይ ፣እንደገለጽንላችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የፊደል የማርክ አሰጣጥን አይጠቀምም። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች “Pass/Incomplete” የተሰኘ የተለመደ አይነት የማርክ እና ሪፖርት አሰጣጥ ሥርአት እያዘጋጀን ነው። ይሄ እንዴት ሊተገበር እንደሚችል በርካታ ጥያቄዎች እንዳሉ ስለምናውቅ ከባለድርሻ አካላት (ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ ከእኛ የሠራተኛ ማህበራት እና ኮሌጅ/ዩንቨርስቲ የምዝገባ ጽ/ቤቶች) ተጨማሪ ግብአቶችን ከሰበሰብን በኋላ “Pass” የማለፍ ውጤትን በተመለከተ በርካታ ግልጽ መስፈርቶች እና መመዘኛዎች እንደሚኖሩ ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። በእነዚህ እርምጃዎች ብቻ የሚያበቃ ባይሆንም የሚያካትቱት፦ የተሰጡ ሥራዎችን-የቤት ሥራዎችን ማጠናቀቅ፣ የሚጠበቅባቸውን ያህል የሚመጥን ሥራ ማከናወን፣ ትምህርት ስለመከታተል የሚደረገውን የመምህራን ቁጥጥር ማሟላት እና የመምህር ሙያዊ ውሳኔ፣ እና ሌሎችም ናቸው። ስለ ሴሚስተር አጠቃላይ የውጤት አሰጣጥ ስሌት፣ ስለ አማካይ ውጤት (GPA) ወይም በትራንስክሪፕቶች ላይ ውጤቶች እንዴት ሪፖርት እንደሚደረጉ ገና ውሳኔ ላይ ያልተደረሰ መሆኑን በድጋሚ ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን። በማጠቃለያ እቅዱ ላይ የትምህርት ቦርድ (ቦርዱ) ሜይ 12/2020 በሚኖረው መደበኛ የሥራ ስብሰባ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል። ስብሰባው በ MCPS ድረ-ገጽ እና በ MCPS-TV ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ይካሄዳል። ቦርዱ የመጨረሻ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ለማህበረሰቡ ወቅታዊ መረጃ እንሰጣለን። ስለ ማርክ ውጤት እና የሪፖርት አሰጣጥ ቦርዱ የሚያካሄደውን ውይይት ኤፕሪል 21 እዚህ መመልከት ይችላሉ።


የ 3ኛው ማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ ሪፖርት ካርዶች

የ 3ኛው ማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ ሪፖርት ካርዶች ኤፕሪል 27 በፖስታ ይላካሉ።በዚህ ያልተጠበቀ ልዩ ወቅት፣ የተሰጡት የማርክ ውጤቶች ትክክለኛ እና ፍትሃዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መምህራን፣ ርእሰመምህራን እና የዋና ጽ/ቤት ሠራተኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደረጉ መሆናቸውን መግለጽ በጣም አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ደግሞ የሚፈልጉትን ውጤት ግብ ለመድረስ በጠቅላላ በማርክ መስጫው ክፍለጊዜ የሠሩ ተማሪዎች ይህንኑ የማድረግ እድል ማግኘታቸውን ልናረጋግጥ እንወዳለን።

በኤለመንተሪ ደረጃ—በተደረገው ጥረት የውጤት ማርኮች የተሰጡት በከፍተኛ ደረጃ ሁኔታዎችን በማገናዘብ፣ ትክክለኛ እና ፍትሃዊ —መሆኑን በኤለመንተሪ ሪፖርት ካርድ ላይ ለሳቱት “M” የሚል ውጤት አለመኖሩን ወላጆች ያስተውሉ ይሆናል። በማርክ መስጫ ክፍለጊዜው የተራዘመ የትምህርት ቤት መዘጋት እና በርካታ የተደናቀፉ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ይህ አቀራረብ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን። ያልተመዘገበው ውጤት-ማርክ በእርስዎ ልጅ የክፍል መሻገር፣ በአገላለጽ ወይም ሌላ የትምህርት ሁኔታዎች ላይ ወደፊት ምንም አይነት ተፅእኖ እንደማይፈጥር ልናረጋገጥልዎት እንወዳለን።

ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ በሪፖርት ካርዶች ላይ ለእያንዳንዱ ኮርስ የፊደል ማርክ ውጤት ያሣያል። በኦንላይን ትምህርት ወቅት የ3ኛው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ የመጀመሪያው ምዕራፍ የሦስተኛውን ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በስኬታማነት ለማጠናቀቅ ተማሪዎች (በቢሮ የሥራ ሠዓት) የተሰጣቸውን ሥራ ለመጨረስ በቂ ጊዜ ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የኦንላይን የማርክ መስጫው ክፍለ ጊዜ መራዘሙን ያመለክታል። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ተማሪዎች የማርክ መስጫውን ክፍለጊዜ እንዲያጠናቅቁ እና የማለፊያ ውጤት ለማግኘት እንዲችሉ ተጨማሪ እድሎችን ለመስጠት “Incomplete”/አላጠናቀቀ(ች)ም የሚል ውጤት ያገኛሉ። “Incomplete” ስለሚለው ውጤት-ማርክ ወይም የቤት ሥራዎችን በሚመለከት ጥያቄዎች ካለዎት እባክዎ የእርስዎን ልጅ መምህር ያነጋግሩ። “Incomplete” ስለሚለው ውጤት ተማሪው(ዋ) ቀሪዎቹን የቤት ሥራዎች ስለማጠናቀቅ እና ማለፊያ ውጤት ስለማግኘት እቅድ ለማዳበር ትምህርት ቤቶች ቤተሰብን ያነጋግራሉ።

የስፔሻል ኢጁኬሽን አገልግሎት ስለሚያገኙ ተማሪዎች፣ ግለትምህርት ፕላን (IEP) ግቦችን ስለመድረስ ያለውን እርምጃ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የእርስዎን ልጅ የ3ኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ሪፖርቶችን ያመሣክሩ። ስለ IEP ውሳኔዎችን በሚመለከት የ3ኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ተለይቶ የሚወሰድ ዳታ አለመሆኑን እናረጋግጣለን።

ስለአዲስ የ MCPS ተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ

ልጆቻቸውን ማስመዝገብ የሚፈልጉ ቤተሰቦችን ለመርዳት MCPS አዲስ ኦንላይን ምዝገባ/ምደባ ሂደት ጀምሯል። ለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት ልጆቻቸውን ወደ ቅድመ ምዋእለ ህፃናት/ሄድ ስታርት እና ምዋእለ ህፃናት ፕሮግራሞች እንዲሁም K-12 እና ለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ዓለምአቀፍ ምዝገባ ለሚያስመዘግቡ ቤተሰቦች በሦስት መንገድ ማከናወን ይችላሉ፦

  1. ኦንላይን፣ በዚህ የምዝገባ ዳሰሳ ይጀምራሉ Registration Survey
  2. በስልክ፦ 240-740-5999 በመደወል
  3. በወረቀት ቅጾቹ-ፎርሞች ወደቤት በፖስታ እንዲላክልዎት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-5999 ደውለው ይጠይቁ።

ለሲንየሮች የመጨረሻ የትምህርት ቀን እና ስለ ምረቃ የዳሰሳ ጥናት

ለሲንየሮች የመጨረሻው የትምህርት ቀን ሜይ 22/2020 ይሆናል። በ 2020  ስለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ስለምረቃ ሁኔታ እርግጠኛ መሆን አለመቻላችሁን ብዙዎቻችሁ ስጋታችሁን ገልጻችሁልናል። በ 2020 ስለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች እውቅና ለመስጠት እና አከባበር MCPS እንዴት ወደፊት ማስኬድ እንዳለበት የእርስዎን አስተያየት ለመስማር እንፈልጋለን፣ እና የሲንየር ተማሪዎች ወላጆች እባካችሁ መጠይቅ እንድትሞሉ ይህንን አጭር መጠይቅ-this brief survey እስከ ዓርብ፣ ሜይ 1/2020። ሲንየሮች በኢሜይል ሌላ የዳሰሳ መጠይቅ ይደርሳቸዋል።


የኮሌጅ ቦርድ እና IB ወቅታዊ ይዞታ መግለጫዎች

 የአድባንስድ ምደባ (AP) ፈተናዎች ከሜይ 11 እስከ ሜይ 22 በቤት  “at-home” format እንደሚካሄዱ የኮሌጅ ቦርድ አስታውቋል። ፈተናዎቹ የሚያካትቱት አብዛኛውን የ AP አስተማሪዎች እና ተማሪዎች ማርች መጀመሪያ ላይ የሠሩትን አርእስቶች እና ሙያዎች-skills ብቻ ናቸው። እንደ አብዛኛዎቹ የኮሌጅ ደረጃ ፈተናዎች ሁሉ፣ ፈተናዎቹ በ "open book/open note" የሚሠሩ ናቸው። ስለ "AP World Languages and Cultures" ፈተናዎችን ስለ ማስተናገጃ ሁኔታ የተለየ ዝርዝር መረጃ ኤፕሪል 27 በሚሆንበት ሣምንት ይገለጻል። ለሁሉ ተማሪ እቤት ውስጥ የኢንተርኔት ተደራሽነት ወይም ሌላ ዲቫይስ እንደማይኖር የኮሌጅ ቦርድ ስለሚገነዘብ ተማሪዎች የራሳቸውን ምርጥ የሥራ ውጤት ለማሳየት የሚችሉበትን መንገድ መፍትሔ የሚገኝበትን መንገድ ለመርዳት እየተሠራበት ነው።

Online AP courses ongoing AP Updates from College Board በመከታተል ወቅታዊ መረጃ ያገኛሉ።
በ MCPS መምህራን ከዳበሩት "myMCPS courses" በተጨማሪ ተማሪዎች ስለ እያንዳንዱ ኮርስ ከኮሌጅ ቦርድ ጭምር ያገኛሉ።

MCPS AP FAQ for Students አዘጋጅቷል። የኮሌጅ ቦርድ ለትምህርት ባለሙያዎች እና ለወላጆች እያገዘ-እየረዳ ያለ "webinars" ጭምር አለው parent webinars እና ለመምህራን በትምህርቱ ላይ ያተኮረ-subject-specific webinars መሆኑ ነው።

መደበኛ የ "International Baccalaureate (IB)" ፈተናዎች አይካሄዱም። የ IB ተማሪዎች የሥራ ደረጃቸውን የሚገልጽ ዲፕሎማ ይሰጣቸዋል፣ ወይም ከሙያ ጋር የተገናኘ ሠርተፊኬት ወይም የኮርስ ሠርተፊኬት ያገኛሉ። የሚያገኘው በተማሪው(ዋ) የኮርስ ሥራ እና በተዘጋጀው የመመዘኛ ምጡቅነት፣ እና በፕሮግራሙ ላይ በተገነባው ጠንቃቃነት እና የጥራት ቁጥጥር ላይ ተመሥርቶ ነው። የበለጠ መረጃ በ IB Organization website ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።


ተማሪ የቦርድ አባል ምርጫ

 ቀደም ሲል ለኤፕሪል 22/2020 በእቅድ ተይዞ የነበረው ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) ምርጫ ወደ ሜይ 20/2020 ተሸጋግሯል። ስለ እያንዳንዱ ተወዳዳሪ ለተማሪዎች መረጃ በመስጠት እና ተማሪዎች በትምህርት ቤት ህንፃ ባይሆኑም እንኳ በ ኦንላይን ጥሩ ምርጫ ለማካሄድ የሚቻልበትን መድረክ-platform ለመፍጠር ስንሠራ ቆይተናል።

ለ 43ኛው ተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) የቀረቡት ሁለቱ እጩ ተወዳዳሪዎች Mr. Nick Asante, a junior at Richard Montgomery High School, እና Miss Victoria Kidder, a junior at Col. Zadok Magruder High School ናቸው። ስለ ተወዳዳሪዎቹ የግል ታሪክ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፣ እና ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ አቋማቸውን ለማወቅ ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ-። እጩ ተወዳዳሪዎቹ በተጨማሪም ስለ ኮሮናቫይረስ-COVID-19 አስተሳሰባቸውን ለማጋራት አጭር ቪድኦ ሪኮርድ ያደረጉ ስለሆነ እዚህ መመልከት ይቻላል። ምርጫውን በሚመለከት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በጠቅላላ ሜይ 20 ሊንኩ በኢሜይል ይደርሳቸዋል-ያገኛሉ። ተጨማሪ ዝርዝሮች በመጪዎቹ ቀኖች ለተማሪዎች ይደርሳቸዋል።


በቴሌቪዥን የሚተላለፍ "Eureka Math Programming on MCPS-TV

የኤለመንተሪ ተማሪዎችተጨማሪ ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን ከ "Eureka Math on MCPS-TV cable channels Comcast 34, Verizon 36 and RCN 89" ለመማር-ለመከታተል ይችላሉ። በተከታታይ የሚቀርቡት ትምህርቶች የሚሰጡት ከ K-5 teacher-writers የትምህርት ባለሙያ-ኤክስፐርት በ Greatminds.org አማካይነት ነው። "Eureka Math programming" ለተማሪዎች ከ MCPS የቀጣይነት ትምህርት መስፈርቶች በተጨማሪ እውቀታቸውን ለማዳበር የሚረዳቸው ትምህርት ነው። Eureka Math programming በክፍል ደረጃ፣ ሞጁል እና ትምህርቱ መቼ መቼ እንደሚተላለፍ ለማወቅ ይህንን የጊዜ ሠሌዳ View the schedule ይመልከቱ።


የወላጆች አካደሚ የሚሰጣቸው ሪሶርሶች "Webinars to Families"-Parent Academy Offering Resources, Webinars to Families

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፓረንት አካደሚ-MCPS Parent Academy የስፕሪንግ 2020 አውደጥናቶችን/ዎርክሾፖችን ሠርዟል። ነገር ግን  ወላጆች እቤታቸው መመልከት እንዲችሉ ተከታታይ "series of Parent Academy To-Go videos" ቪድኦችን የማዘጋጀት እቅዶች እየተሠሩ ናቸው። በየጊዜው የፓረንት አካደሚን ድረ-ገጽ Parent Academy website በመከታተል መረጃዎችን ለማግኘት ይሞክሩ።

ይሄኛው ድረ-ገጽ በተጨማሪ ለቤተሰቦች የሚረዳ ስለ "webinars" አገናኝ መረብ እና ሪሶርሶች ይኖሩታል። እነዚህ ወላጆችን የማበረታታት ፕሮግራም እና የሚገነዘብ ህሊና - "Parent Encouragement Program and Common Sense" የሚሰጡ ጠቃሚ መረጃዎች፦


ስለ ጤንነት እና ደህና ቁመና አዲስ ተከታታይ የቪድኦ ሪሶርሶች በጨረፍታ

MCPS ወላጆች በየቀኑ ህይወታቸው ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እየተጋፈጡ ባሉበት ወቅት ስለ አእምሮ ጤንነት እና ጥሩ የጤንነት ቁመና ለማወቅ የሚጠቅም ለሠራተኞች እና ለተማሪዎች “Waymaking” የተሰኘ አዲስ ተከታታይ ቪድኦ ተጀምሯል። የቪድኦው ትምህርት የሚቀርበው በ Dr. Christina Conolly, director of psychological services for MCPS አማካይነት ነው። የመጀመሪያውን ክፍል እዚህ መመልከት ይችላሉ።