Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: April 19, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ የሥራ ባልደረቦች እና የማህበረሰብ አባላት

ዓርብ፣ ኤፕሪል 17 ገቨርነር ላሪ ሆገን እና የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን/Governor Larry Hogan and State Superintendent of Schools Karen Salmon፣ የሜሪላንድ የህዝብ ትምህርት ቤቶች እስከ ሜይ 15/2020 ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ገልጸዋል። የትምህርት ቤቶች መዘጋት የተራዘመበት ምክንያት የተማሪዎች፣ የሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ጤንነት እና ደህንነት መጠበቁን ለማረጋገጥ ይረዳል።

ምንም እንኳ ቢያንስ ለአንድ ወር ህንጻዎቻችን ዝግ ሆነው የሚቆዩ ቢሆንም፣ ተማሪዎቻችንን በኦንላይን ሞዴል ለማስተማርና ለመርዳት እንዲሁም በምግብ አገልግሎት ፕሮግራም ለመርዳት ተዘጋጅተናል።

ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት፣ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደሚቆዩ በስቴት አማካይነት የተሰጠው ውሳኔ ለቤተሰቦቻችን ከባድ መሆኑን እንገነዘባለን። ትምህርት ቤት የካውንቲያችን እና የማህበረሰባችን ማእከል ነው። ተማሪዎችን ከማስተማር በተጓዳኝ የተማሪዎቻችንን አካላዊ፣ ማህበራዊ-ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ፍላጎቶቻቸውን ጭምር መርዳት እንደምንቀጥል እንዲያውቁም እንፈልጋለን።

ከዚህ በታች ያሉት በሚቀጥለው የኦንላይን ትምህርት ምእራፍ፣ ምን ማከናወን እንደሚጠበቅ፣ ስለትምህርት ቤት ካለንደር፣ ስለ ውጤት አሰጣጥ፣ እና ስለ ሲንየሮች የሚጠበቁ የስቴት መስፈሮች የመሣሠሉትን ያካትታል። ዘወትር ጠቃሚ ስለሆኑ መረጃዎችን እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና ሪሶርሶችን በሚመለከት ለመከታተል
እነዚህን የማህበራዊ መገናኛ ድረገጾቻችንን online learning webpage ዘወትር እንድትጎበኙ እናበረታታለን።

እባካችሁ እርስበርስ እየተደጋገፋችሁ ጤንነታችሁን ጠብቁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools 
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ


የትምህርት ቤት ካለንደር

ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 14 የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ምርጫ አካሂዷል ትምህርት ቤቶች 180 የትምህርት ቀኖች ሊኖራቸው ይገባል የሚለው መስፈርት እንዲነሣ። በስቴት የትምህርት ቦርድ ውሳኔ መሠረት፣ ከማርች 16 እስከ 27 ከ10 የአስቸኳይ ጊዜ መዝጊያ ቀኖች አምስቱን ለመሠረዝ-ተቀናሽ ለማድረግ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በመጪዎቹ ሣምንቶች የትምህርት ቤት ካለንደር ክለሳ ይደረጋል። ይህ ማለት በአዲሱ መስፈርት ላይ የተቀመጠውን ቢያንስ (175) የማስተማሪያ ቀኖችን ለማሟላት አምስት ቀኖችን ብቻ የማካካሻ ቀኖች ይደረጋሉ ማለት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከእነዚህ ቀኖች ውስጥ ሦስቱን ቀን የስፕሪንግ እረፍት ቀኖችን በመቀነስ የተካካሰ ሲሆን ሌላ አንድ ተጨማሪ ቀን ደግሞ ለድንገተኛ ሁኔታ የሚዘጋበት ቀን በካለንደሩ ተካቷል። የምርጫ ቀን ወደ ጁን ስለተሸጋገረ እና አሁን ምርጫ የሚካሄደው “vote-by-mail format” በሜይል ፎርማት ስለሆነ፣ ኤፕሪል 28 የመጨረሻ የማካካሻ ትምህርት ቀን አድርገን ለመጠቀም ፕላን እያደረግን ነው የትምህርት ቤት የመጨረሻው ቀን ጁን 15/2020 ይሆናል።


በ MCPS ኦንላይን ትምህርት ከሚቀጥለው ምእራፍ ምን እንደሚጠበቅ፦

ሰኞ፣ ኤፕሪል 20፣ የኦንላይን ትምህርት ፕላን የሚቀጥለውን ምእራፍ እንጀምራለን። ቀጣይ ትምህርት በመስጠት እና የማስተማሪ አላማችንን በማሳካት ላይ ትኩረታችንን እንቀጥላለን፤ ተማሪዎች ያላቸውን መሣሪያዎች እና ሪሶርሶችን/tools and resources በመጠቀም ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን አካደሚያዊ እና ማህበራዊ-ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ድጋፍ መስጠት ላይ ትኩረታችንን እንቀጥላለን። የእኛ ኦንላይን የማስተማር-መማር ሞዴል ስለ ትምህርታዊ ተግባሮች/አክቲቪቲዎች፣ ለብቻ፣ በራስ ጥረት መሥራትን፣ እንድገባቸው/መረዳታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቨርቹወል የቢሮ ሥራ ሠዓቶችን፣ እና ተማሪዎች እንዲሠሩ የተሠጣቸውን ሥራዎች ማቅረብን ጭምር ያካተተ ነው።

የኤለመንተሪ ደረጃ፣ ተማሪዎች፦

  • በሣምንት ሦስት ቀን (ሰኞ፣ ረቡእ፣ እና ዓርብ) በሒሳብ ትምህርቶች ይሳተፋሉ
  • በሣምንት ሁለት ቀን (ማክሰኞ እና ሐሙስ) በሊተረሲ ትምህርቶች ይሳተፋሉ፣ ይህም በየቀኑ ለብቻ የማንበቢያ ጊዜን ይጨምራል PreK-1 ክፍሎች (20 ደቂቃ) እና ከ 2-5 ክፍሎች (30-40 ደቂቃ)
  • ለእያንዳንዱ ቤተሰብ አመቺ በሚሆንበት ሠዓት በስነጥበብ ሥራ፣ ሙዚቃ እና የሰውነት ማጎልመሻ (P.E.) ትምህርቶች ይሳተፋሉ (ለቤተሰቦች በቅድሚያ የተቀረጹ/የተቀዱ ትምህርቶች በየአስራ አምስቱ ሰኞ ይኖራሉ)

የኤለመንተሪ ተማሪዎች በቀጥታ ስርጭት የመማር ስብሰባዎች፣ የቤት ሥራዎቻቸውን ለማጠናቀቅ እና ማቴሪያሎችን ለመመልከት በሣምንት ከ 11-13.5 ሠዓቶችን እንደሚወስድባቸው ወላጆች ግንዛቤ መውሰድ-መጠበቅ ይኖርባቸዋል። የኤለመንተሪ ተማሪዎች ቤተሰቦች የታተሙ ጥራዞችን ዘወትር ረቡእ ቀን ከ 11 a.m. እስከ 1 p.m. ከምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎቻችን ላይ መሰድ ይችላሉ።

ሰኞ

ማክሰኞ

ሮብ

ሀሙስ

አርብ

የኤለመንተሪ ትምህርት

የሂሳብ ትምህርት
*ኪነጥበብ

ምንባብ

የሒሳብ ትምህርት
*ሙዚቃ

ምንባብ

የሒሳብ ትምህርት
*P.E.

* የሚመች ሠዓት ከሆነ (ለቤተሰቦች በሚመቻቸው ሠዓት ለመጠቀም በቅድሚያ ሪኮርድ የተደረጉ ትምህርቶች ይኖራሉ)
*art/music/P.E. - ስነጥበብ/ሙዚቃ/የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርቶች በየሁለተኛ ሣምንት ይታደላሉ

የመካከለኛ ደረጃ (ሚድል ስኩል) እና የሁለተኛ ደረጃ (ሃይ ስኩል) ተማሪዎች፦

  • በዋና ዋና ኮርሶቻቸው እና የመረጧቸው ኮርሶች በጠቅላላ አዳዲስ ትምህርቶችች እና የቤት ሥራዎችን በየሣምንቱ ይሰጣቸዋል
  • በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት መርሃግብር የቢሮ ሠአቶች መሠረት ከአስተማሪዎቻቸው ጋር የመገናኘት እና ድጋፍ የማግኘት እድሎች ይኖራቸዋል
  • ስለ ቤት ሥራዎቻቸው ከአስተማሪዎች ግብረመልስ ያገኛሉ

ሰኞ

ማክሰኞ

ሮብ

ሀሙስ

አርብ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት

መምህራን አዳዲስ ምራፎችን-ትምህርት በጠዋት ይልካሉ

ከ 1-8 ክፍል የሁሉም ትምህርት ክፍለጊዜዎች፣ በቅድሚያ ሪኮርድ የተደረጉ ሲሆን እንደየ ተማሪዎቹ ፍላጎት መሠረት ይሰጣሉ

ጠዋት:

  • ተማሪዎች ለየብቻቸው ይሠራሉ፣ መምህራን ፕላን ማዘጋጀት እና ከወላጆች ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ
  • ስፔሻል ኢጁኬሽን እና ተዛማጅ አገልግሎቶች፣ የካውንስለር እና የድጋፍ አገልግሎቶች፣ ትምህርት ቤትን በተለይ የሚመለከት መርሐግብር

 

ከሠዓት በኋላ፦

  • በትምህርት ቤቱ መርሃግብር የአስተማሪ የቢሮ ሠዓት መሠረት፣ መምህራን ጋር የሚጀመርበት ሠዓት

በአጠቃላይ፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከእያንዳንዱ ኮርስ በሣምንት ከአንድ እስከ ሁለት ትርጉም-ፋይዳ ያላቸው የቤት ሥራዎችን እንደሚያገኙ እና በየቀኑ እስከ አራት ሠዓት እንደሚሠሩ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ተማሪዎች በትምህርት ላይ የሚሠማሩበት ጊዜ ርዝመት የሚወሰነው በእያንዳንዱ ኮርስ ደረጃ እንደሚሆን እና ተማሪው(ዋ) በጠቅላላ የኮርሶቹ ትምህርት ሥራ ከሚሠጣቸው የቤት ሥራዎች ጋር የተገናዘበ መሆኑን ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል።

ተማሪዎች የቤት ሥራዎቻቸውን-assignments በ "Google Classroom, myMCPS classroom or email" ማቅረብ ይችላሉ። ምንም እንኳ አስተማሪዎች አዳዲስ የትምህርት ይዘት እና የቤት ሥራዎችን ተማሪዎች እንዲያጠናቅቁ የሚያሳዉቁ ቢሆንም፣ ተማሪዎች በዚህ ወቅት የሚያጠናቅቋቸው ሥራዎች እና ከመምህራን የሚያገኙት ግብረመልስ በትምህርት ቤት በየቀኑ ሲያገኙት የነበረውን ትምህርት የሚተካ አይደለም።

ግባችን ቁልፍ የሆኑ የትምህርት ይዘቶችን እሳቤ ለመጠበቅ፦ በትምህርት ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ትብብር ማድረግ፣ ከሥራ ባልደረቦች ድጋፍ በማግኘት የትምህርት ቤት ሥራዎችን እና ግብረመልሶችን በማዘጋጀትና በመስጠት በትምህርት ሒደት ወደፊት እንዲገፉ ማድረግ ነው። የትምህርት ተሞክሮዎቹ እሳቤ ትምህርትን ማስቀጠል፣ የሚኖሩትን እርምጃዎች መከታተል እና ማመቻቸት፣ እና ተማሪዎች ራሳቸው በቁርጠኛነት በእውቀት ማደግን ታሳቢ ያደረገ ነው። የቢሮ ሠዓት መርሐግብሮች ከመምህራን ጋር ለመገናኘት፣ ተጨማሪ ትምህርት ለመሥራት፣ እና እንደአስፈላጊነቱ ድጋፍ ለማግኘት አስፈላጊ ሠአቶች ናቸው።


ማርክ-ውጤት መስጠት እና ሪፖርት ማድረጊያ ሥርአት

የሦስተኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ውጤት ሪፖርት የሚደረገው መደበኛውን የውጤት አሰጣጥ ሲስተም በመጠቀም ይሆናል። ኤፕሪል 27 በሚውልበት ሣምንት ሪፖርት ካርዶች ወደ ቤት ይላካሉ። ባለፉት በርካታ ሣምንታት፣ ስለ 4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ውጤት እና ሪፖርት አሰጣጥ MCPS የተለያዩ አማራጮችን ሲዳስስ ቆይቷል። ይህ አሠራር የሌሎች የህዝብ ትምህርት ቤት ዲስትሪክቶችንም አቀራረብ መመርመር-ማጥናት እና ኮሌጆችንና ዩንቨርስቲዎችን መገናኘት፣ እና ከተላያዩ ባለድርሻ አካላት ግብረመልሶችን ማፈላለግን ያካትታል። ይሄ በጥንቃቄ ማቀድን እና ትብብርን የሚጠይቅ ውስብስብ ውሳኔ ነው። መደበኛው የውጤት አሰጣጥ ሲስተም ማለትም በፐርሰንቴጅ እና በፊደል ማርክ አሰጣጥ በዚህ ወቅት ኦንላይን ትምህርት በመከታተል-በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ፍላጎት እንደማያሟላ ተገንዝበናል። የእኛ የውጤት-ማርክ አሰጣጥ ሲስተም አዎንታዊ ተጽእኖ ያለው እና ተማሪዎቻችን በትምህርት ያሉበትን አቋም ለመመዘን የሚረዳ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን።

እንደማንኛውም የውጤት-ማርክ አሠጣጥ ፖሊሲ፣ እንከን የሌለው የማርክ-ውጤት መስጫ ሲስተም የለም። እንዲያውም በዚህ ቤተሰብን በሚያስጨንቅ ሁኔታ ውስጥ እንዲያውም የሚጎላ ይሆናል። ነገር ግን፣ ወረርሽኙ በቤተሰቦች ላይ ባስከተለው ጭንቀት ምክንያት እንደማይቀጡ ግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪዎች እየተማሩ መሆናቸውን የሚከተሉት ስልቶች-ስትራቴጂዎች ለማወቅ እንደሚያስችሉን እናምናለን።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
በ4ኛው የማርክ-ውጤት መስጫ ክፍለጊዜ፣ በመካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች/In middle and high schools፣ መደበኛው የፊደል ውጤት አሰጣጥ ሲስተም ተግባራዊ አይደረግም። ለቀሪው የትምህርት ዓመት፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች MCPS የሚታወቀውን አይነት “Pass/Incomplete” ወይም “Credit/No Credit” የማርክ-ውጤት እና ሪፖርት አሰጣጥ ሥርዓት እያዘጋጀ ነው። ይህ አይነት የማርክ-ውጤት አሰጣጥ ተማሪዎች በከሪኩለሙ እንዲሳተፉ እና ትርጉም-ፋይዳ ያለው ግብረመልስ በመስጠት፣ እና እርምጃቸውን በመለካት ለሁሉም ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ መሆኑን እንደሚያረጋግጥላቸው እናምናለን። ወደዚህ ሲስተም በተግባቦት ለመሸጋገር እና መምህራን እና ተማሪዎች የውጤታማነት መመዘኛውን መረዳታቸውን-መገንዘባቸውን ለማረጋገጥ በዚህ ወቅት ከባለድርሻ አካላት ጋር (መምህራን፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ እና የማህበር መሪዎች) እየሠራን እንገኛለን። ይህ አይነት የውጤት-ማርክ አሰጣጥ ስለሚያስከትለው ነገር በርካታ ጥያቄዎች እንደሚኖሩ እንገነዘባለን፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ይሰጣቸዋል። ነገር ግን መደበኛው የውጤት-ማርክ አሰጣጥ ተሞክሮ የሁሉንም ተማሪዎች ፍላጎት ስለማያሟላ ዓለም አቀፍ በየትም ያለውን አይነት አቀራረብ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ሲስተም እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ የመጨረሻው ሴሚስተር ውጤት እንዴት በትራንስክሪፕት ላይ ተካቶ ሪፖርት እንደሚደረግ ጭምር በመጪዎቹ ሣምንቶች የበለጠ መረጃ-ኢንፎርሜሽን ይሰጣል።

የኤለመንተሪ ተማሪዎች
ለ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በፊደል ማርክ-ውጤት አይሰጥም። ትኩረት የሚደረገው ተማሪዎች በመማር ላይ እንዲሠማሩ-እንዲሳተፉ ማድረግ እና በተቻለ መጠን ከበርካታ ተማሪዎች ጋር መገናኘት እና በትምህርቱ እንዲሳተፉ በማድረግ ላይ ይሆናል። ተማሪዎች የትምህርት እርምጃ ማሳየታቸውን እና የትምህርት ዓላማን እያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ በእኛ በኩል፦

  • በርካታ የመማር-ማስተማር ተሞክሮዎች ላይ ተማሪዎች እንዲሳተፉ እድል መስጠት-ማመቻቸት
  • ተለይተው የታወቁ ማሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ዙርያ ከተማሪዎች እና ከወላጆቻቸው/ሞግዚቶቻቸው ጋር ክትትል ማድረግ
  • ተማሪዎች በአካደሚያዊ እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ
  • ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት በሚመለሱበት ወቅት ለቀጣዩ የክፍል ደረጃ በየትኛዎቹ ችሎታዎቻቸው ዙርያ መሥራት እንደሚኖርባቸው ለመምህራን መረጃ-ኢንፎርሜሽን መስጠት።

የተማሪ ክትትል-ተሳትፎ እና ሃላፊነት

ምንም እንኳ በተለመደው አይነት መደበኛ ትምህርት የመከታተል ቁጥጥር ባይወሰድም፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች የተማሪን ተሳትፎ እና ትምህርት የመከታተል ሁኔታዎችን ይቆጣጠራሉ። ይሄንን በብዙ መንገድ ክትትል ይደረጋል፣ ጭምር፦

  • የቤት ሥራ ማጠናቀቅ
  • ተማሪ የቀጥታ ስርጭት ትምህርት መከታተል ወይም ቨርቹወል የቢሮ ሠዓቶችን መከታተል
  • ከተማሪዎች/ወላጆች/ሞግዚቶች ጋር የኢ-ሜይል ወይም የስልክ ጥሪዎችን ማድረግ
  • ተማሪዎች የሚመልሷቸው የወረቀት/የእርሳስ የቤት ሥራዎች

በርቀት ትምህርት የተማሪ መሠማራት-መሥራት-መሳተፍ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት መግለጽ እንፈልጋለን። የእርስዎ ልጅ (ren) በኦንላይን ትምህርት ላይ የመሣተፍ ችግር ካለበ(ባ)ት፣ እባክዎ ካውንስለርን ወይም የትምህርት ቤት አስተዳዳሪ በተቻለ ፍጥነት ያነጋግሩ። በተጨማሪ ጥያቄ ወይም አሳሳቢ ሁኔታ ካለ እዚህ ማቅረብ ይችላሉ።


ስለ 2020 ተመራቂ ተማሪዎች እና ምረቃ የስቴት መስፈርቶች

ኤፕሪል 14፣ የስቴት የትምህርት ቦርድ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየሮች የፈተና-ቴስት መመዘኛዎችን ስለማስቀረት ድምፅ ሰጥቷል-ወስኗል። የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሠአቶች መስፈርትም እንዲቀር ወስኗል። የ 2020 ተመራቂዎችን በሚመለከት የ MCPS የሥራ ባልደረቦች አማራጭ የምረቃ ፕሮግራሞችን ለመወያየት ስብሰባ እያደረጉ ናቸው። በመጪዎቹ ሣምንታት የበለጠ ዝርዝር መረጃ-ኢንፎርሜሽን ይገለጻል።


ለምግብ አገልግሎት ፕሮግራም አዳዲስ ጣቢያዎች ተጨምረዋል

ከ ሰኞ፣ ኤፕሪል 20 ጀምሮ MCPS ለምግብ አገልግሎት ስርጭት ሁለት አዲስ ጣቢያዎችን ይጨምራል። አዲሶቹ ጣቢያዎች የሚገኙት በ "John Poole Middle School in Poolesville እና Meadow Hall Elementary School in Rockville" ሲሆን የጠቅላላ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 50 ያደርሳል። ስለ ጊዜዎቹ፣ ቀኖች፣ እና ቦታዎችን በተመለከተ በዚህ ድረገጽ ላይ ዝርዝር Coronavirus webpage ማግኘት ይችላሉ።


Alert MCPS

ስለ ትምህርት ቤቶች የአስቸኳይ ጊዜ መዘጋት እና አርፍዶ መክፈት ለማህበረሰብ አስፈላጊ እና ጠቃሚ መልእክቶችን ለማስተላለፍ MCPS ስለ "Alert MCPS system" አጠቃቀም ሲስተምን አስፋፍቷል። እነዚህ ማስታወቂያዎች የሚተላለፉት በኢ-ሜይል እና በቴክስት መልክቶች ይሆናል። የ MCPS ቤተሰቦችን በሙሉ ወቅታዊ መረጃዎችን፣ ሪሶርሶችን እና ማስታወቂያዎችን ማግኘትዎን ለማረጋገጥ ስለሚረዳ እዚህ ሲስተም ላይ እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።


ፊትን መሸፈን

ማሳሰቢያ፦ በአብዛኛዎቹ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ወቅት ፊት መሸፈን እንደሚያስፈልግ አዲሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ህግ ይደነግጋል። ምግብ እና Chromebooks የሚወስዱ ግለሰቦች መሸፈኛ ልብስ ወይም አፍንጫቸውን እና አፋቸውን የሚሸፍን ሌላ ቁሳቁስ፣ እንደ ፊት መሸፈኛ፣ እቤት የተሠራ የፊት መሸፈኛ፣ ስካርቭ፣ መሃረብ የመሣሰሉ ነገሮችን እንዲጠቀሙ አበክረን እናበረታታለን። የፊት መሸፈኛዎች እንዴት እንደሚዘጋጁ የ CDC መመሪያዎች እዚህ ይገኛሉ።


Zoom Reminder-ማሳሰቢያ

MCPS በአካል እና በ ኦንላይን ጤናማ የትምህርት አካባቢን የመስጠት ቁርጠኝነት አለው። የተማሪን ገመና እንዳይገለጥ ለማጠናከር እና ተማሪዎች ቨርቹወል ትምህርት ላይ እያሉ-virtual classroom ውጫዊ የማደናቀፍ ጣልቃገብነትን ለመቀነስ-ለመከላከል የሚከተሉትን ጨምሮ MCPS በርካታ ስልቶችን ዘርግቷል፦

  •  የ MCPS አካውንት ያላቸው ተማሪዎች እና መምህራንን ብቻ የሚያስገባ ጥብቅ የሆነ ሲስተም
  • በመምህራን አማካይነት ኦንላይን ትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ለመገምገም የሚያስችል "waiting room feature"
  • የተማሪን ካሜራዎች እና ማይክሮፎኖችን እንዳይሠሩ የሚዘጉ ቅንብሮች-Settings

የተማሪን ገመና ስለመጠበቅ MCPS ምን ያህል ቁርጠኝነ እንዳለው እዚህ የበለጠ ያንብቡ።


George B. Thomas Learning Academy ኦንላይን ትምህርት ድጋፍ ይሰጣል።

ከቅዳሜ፣ ኤፕሪል 25 ጀምሮ፣ የ George B. Thomas, Sr. Learning Academy (Saturday School) በኦንላይን ትምርህት የሚሰጥበት ፕላትፎርም “The Learning Academy Online” ይጀምራል። የዚህ አዲስ ፕላትፎርም ግቡ፣ በዚህ ወቅት በ MCPS ከሪኩለም የርቀት ትምህርት ላይ የተመዘገቡ ቤተሰቦችን እና ተማሪዎችን ለመርዳት እና በተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው መካከል መልካም ግንኙነትን መገንባት እንዲቀጥል ለማገዝ ነው። የበለጠ መረጃ-ኢንፎርሜሽን በዚህ ድረገጽ ላይ ይገኛል፦ Saturday School website