Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: April 17, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어አማርኛ

የተወደዳችሁ ወላጅች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

ዛሬ (ኤፕሪል 17)፣ ገቨርነር ላሪ ሆገን/Governor Larry Hogan እና የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐር ኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን/Superintendent of Schools Karen Salmon የሜሪላንድ የህዝብ ትምህርት ቤቶች እስከ ሜይ 15 ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ አሳውቀዋል። ተማሪዎቻችን እና ሠራተኞቻችን ለመማር እና አብረው ለመሥራት በትምህርት ቤት በአካል አብረው ለመሆን ባለመቻላቸው ሀዘንና ስጋት ቢሰማንም፣ ይህ ውሳኔ የተማሪዎቻችንን እና የማህበረሰባችንን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን እናምናለን።

የትምህርት ቤቶች መዘጋት እንዲራዘም መገለጹ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች—ከ ኦንላይን ትምህርት ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ካለንደር እና የምረቃ ፕሮግራሞች ድረስ በርካታ ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ እናውቃለን። በዚህ ሳምንት መጨረሻ፣ እነዚህን በርካታ ጥያቄዎች እና አሳሳቢ ጉዳዮችን የሚመለከቱ መልእክቶችን ለማህበረሰቡ እናስተላልፋለን። እነዚህን የመገናኛ ብዙሃን አውታረ-መረቦቻችንን እንድትከታተሉ እናበረታታለን፦coronavirus webpage frequently and sign up to receive important alerts through theAlert Montgomery system

እባካችሁ እርስበርስ እየተደጋገፋችሁ ጤንነታችሁን ጠብቁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools 
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ