Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: April 9, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어አማርኛ

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

ሁለተኛውን ሣምንት ኦንላይን ትምህርት ያጠናቀቅን ሲሆን፣ ሠራተኞች እና ተማሪዎች እንዴት እንደገና እየደተገናኙ መሆናቸውን እና መምህራን እንዴት እያስተማሩ መሆናቸውን ስንመለከት እና ስንሰማ በጣም የሚያስደንቅ ነው። ከ creative rap songs/የፈጠራ ለስላሣ/ጠንካራ ምት ዜማዎች አንስቶ በሒሳብ ትምህርት እስከ መሠማራት ድረስ፣ ለተማሪዎቻችን ትርጉም ያለው የትምህርት ተሞክሮ ለመፍጠር እንደማህበረሰብ አብረን በትብብር እየሰራን እንገኛለን።

ከዚህ ሣምንት ክንውኖቻችን ጥቂት ጎልተው የሚታዩትን እነሆ፦

  • ተማሪዎች ከ 17,000 በላይ የቀጥታ ስርጭት ትምህርት ክፍለጊዜዎችን ከመምህራን ጋር ተሳትፈዋል።
  • በመጀመሪያው ዙር የማከፋፈል ወቅት ለመቀበል እድል ላላገኙ ተማሪዎች ከ 9,000 Chromebooks እና MiFi wireless hotspots ተከፋፍሏል።
  • በዚህ ሣምንት ከ 213,000 በላይ ምግቦች ለቤተሰቦች ታድሏል።

እባክዎ ትንሽ ጊዜ ወስደው ከትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት ሼብራ ኢቫንስ/Board of Education president Shebra Evans የተላለፈውን ይህንን አጭር የቪድኦ መልእክት በዚህ ሊንክ ላይ https://youtu.be/JJdfClV2qGE ይመልከቱ። የስፕሪንግ እረፍት እየጀመርን ሣለ፣ ከዚህ በታች ያሉት ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች ናቸው። ከኤፕሪል 9-13 ለተማሪዎች ኦንላይን ትምህርት የማይኖር መሆኑን እናሳስባለን። በዚህ የእረፍት ወቅት ጥሩ ጊዜ እንደሚኖራችሁ እና በአዲስ ሃይል-በአዲስ ጉልበት ከጠቅላላ ተማሪዎቻችን ጋር ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 14 እንደገና እንደምንገናኝ በተስፋ እንጠብቃለን።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ


ለ3ኛ ሣምንት ኦንላይን ትምህርት ምን እንደሚጠበቅ

ተማሪዎች እና መምህራን በዋና ዋና ትምህርቶች ላይ ማድረግ ያለባቸውን ትክረት ይቀጥላሉ፣ እንዲሁም ኤፕሪል 17 የሚያበቃውን ሦስተኛውን የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በስኬት ለማጠናቀቅ መሠራት ያለባቸው ተግባሮች-assignments እና እቅዶች ላይ ትኩረት ሰጥተው ይሠራሉ። መምህራን ከትምህርት ቤት ቡድኖቻቸው ጋር የሚሠሩ ሥራዎችን/assignments ማቀድ እና ከተማሪዎቻቸ ጋር መገናኘት ይቀጥላሉ። ተማሪዎች/ወላጆች/ሞግዚቶች myMCPS Classroom፣ Google Classroom፣ email messages፣ ወይም ሌሎች ተማሪዎች የተለማመዷቸውን የመገናኛ ብዙሃን መሳሪያዎች በየቀኑ ማየት አለባቸው። መምህራን መልእክቶችን፣ የሚያስተምሯቸውን ትምህርቶች፣ ተማሪዎች መስራት ያለባቸውን ሥራዎች-assignments እና ሌሎች ዋና ዋና መረጃዎችን ለመላክ እነዚህ የሚያጓጉ መድረኮች-platforms ዋነኛ መገናኛዎቻችን ናቸው። በተጨማሪ፣ በጠቅላላ ትምህርት ቤቶች በየግል ድረ-ገጾቻቸው ላይ ሣምንታዊ መርሃግብሮቻቸውን ይገልጻሉ። የተለየ ትምህርት ቤትን የሚመለከት ጥያቄ ካላችሁ ጥያቄያችሁን እዚህ  እንድታቀርቡ እንጠይቃለን። በኤለመንተሪ ደረጃ ተጨማሪ የህትመት ጥራዞችን እንድናቀርብ የተጠየቅን ስለሆነ፣ ከስፕሪንግ እረፍት በምንመለስበት ጊዜ የስርጭት ጊዜ ሠሌዳ እናሳውቃለን። እነዚህ የማስተማርያ-መማሪያ ፓኬቶች በኦንላይን የተለቀቁ ስለሆነ እዚህ ማግኘት ይቻላል። 

ስለ ሦስተኛ እና አራተኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ውጤት አሰጣጥ መረጃ-ኢንፎርሜሽን ኤፕሪል 13 በሚውልበት ሣምንት ለቤተሰቦች ይገለጻል። የኤለመንተሪ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ኤፕሪል 21 ውጤት ይሰጣሉ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከማርች 30 በፊት የተሰጣቸውን ሥራ አጠናቀው እንዲመልሱ እድል ተሰጥቷቸው ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሦስተኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ውጤታቸውን ለማሻሻል እድል እንዲኖራቸው መምህራን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ ሁለት ተጨማሪ ሥራዎችን-assignments መስጠት ይችላሉ።

የሦስተኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ውጤት ሪፖርት የሚደረገው መደበኛውን የውጤት አሰጣጥ ሲስተም በመጠቀም ይሆናል። ኤፕሪል 27 በሚውልበት ሣምንት ሪፖርት ካርዶች ወደ ቤት ይላካሉ።

ለ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የተማሪዎች ማርክ-ውጤት አስጣጥ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ለመወሰን ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት እና ከሌሎች አጎራባች ዲስትሪክቶች ጋር በመተባበር እየሠራ ነው።


ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት

በዚህ ሣምንት፣ በስፕሪንግ እረፍት ምክንያት፣ MCPS ከኤፕሪል 6-8 ቁርስ፣ ምሣ እና እራት ለልጆች በነጻ ሰጥቷል። ከሐሙስ፣ ኤፕሪል 9 እስከ ሰኞ፣ ኤፕሪል 13 የምግብ አገልግሎት አይኖርም። MCPS ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 14 የምግብ አገልግሎት ይጀመራል። ምግብ የሚሰጥባቸውን ቦታዎች የተሟላ ዝርዝር ለማግኘት እባክዎ ይህንን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የምግብ አገልግሎት ድረገጽ ይመልከቱ/MCPS Meals Service webpage

ሚኒስትሪዎችን የሚያገለግሉ ሴቶች "Women Who Care Ministries" ለሣምንት መጨረሻ የሚሆኑ ምግቦችን ዓርብ፣ ኤፕሪል 10፣ ከ 11 a.m.- 6 p.m. በዚህ አድራሻ፦ Montgomery Village site located at 19642 Club House Road, Suite 620, in Montgomery VIllage ለቤተሰቦች ይሰጣሉ። ተጨማሪ መረጃዎች እዚህ ይገኛሉ።

Manna Food Center-መና የምግብ ማእከል ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ለሣምንት መጨረሻ የሚሆኑ ምግቦችን በከረጢት ያድላል። ጊዜው እና ቦታዎቹ ዓርብ፣ ኤፕሪል 10 በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ድረገጽ - MCPS website ላይ ይገለጻል።


Chromebook ማከፋፈል

ኤፕሪል 13 በሚውልበት ሣምንት Chromebooks እና mobile MiFi hotspots የመስጠት ተጨማሪ እድሎች ይኖራሉ። ኤፕሪል 8 ለሚደረገው ማከፋፈል ለእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት ጥያቄ የማቅረብ እድል ያላገኙ ከሆነ፣ እባክዎ በሚቀጥለው ዙር ለሚከፋፈለው እድል ለማግኘት ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ።

ስለ ኮሮናቫይረስ-ኮቪድ 19/Comcast’s COVID 19 ከ” Comcast በተደረገው ምላሽ፣ የ “Comcast’s Xfinity Outdoor WiFi hotspots” ለሚፈልጉ ሁሉ በነፃ አገልግሎት ይሰጣል። ይኼውም የ Xfinity ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያልሆኑትን ጭምር ማለት ነው። የ Xfinity Outdoor WiFi hotspots አገልግሎት ማፑን ለማወቅ-ለማየት እባክዎ ይህንን ድረ-ገጽ ይጎብኙ www.xfinity.com/wifi - hotspot ዝርዝሩ ላይ ከገቡ በኋላ “xfinitywifi” የሚለውን በይነመረብ ስም ይምረጡ እና አውታረመረቡን ዳሰሳ ማድረግ ይችላሉ። እባክዎ እነዚህ hotspots የ “Xfinity የመኖሪያ አካባቢ Wifi ኔትዎርክ አለመሆናቸውን ግንዛቤ ይውሰዱ።


Mindful Moments-ልብ የምንላቸው-የምናስተውላቸው ጉዳዮች

MCPS ልብ የምንላቸው-የምናስተውላቸው ወቅቶች በሚል ርእስ ተከታታይ ቪድ ኦችን አዘጋጅቷል። በተከታታይ የሚቀርቡት ልብ የምንላቸው-የምናስተውላቸው ወቅቶች-Mindful Moment Series ግቡ ፍርሃት እና ጭንቀት በከበበን ጊዜ እንዴት ለመወጣት እንደምንችል ቀላል እና ውጤታማ የሆኑ ዘዴዎችን ለመግለጽ ነው። በማንኛውም ጊዜ ለማግኘት እና ለመጠቀም የተዘጋጁትን እነዚህን ቪድኦዎች እዚህ ማግኘት ይቻላል።

ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ለጎልማሶች እና ለቤተሰቦች የተነደፉ አይነት ስትራቴጂዎች-ስልቶች አሉ። እያንዳንዱ ቪድኦ ስለማስተዋል ተሞክሮ በሚመራ-በምትመራ የ MCPS ሠራተኛ አማካይነት ይቀርባል። አንዳንዱ የአካል እንቅስቃሴን ይጨምራል፣ አንዳንዱ ስለ አተነፋፈስ ዘዴ፣ ሊሎች ደግሞ የአእምሮ ጅምናስቲክን የሚያካትቱ ሲሆን—ሁሉም ስለ ማስተዋል ዘዴዎችን በማስተማር ድብርት፣ ውጥረት-ጭንቀት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ መከፋት፣ ቁጣ፣ ፍርሃት-ስጋት እና እፎይታ ማጣት የሚያስከትሏቸውን ተጽእኖዎች ፋታ-እፎይታ ለማግኘት ፍቱን ተሞክሮዎች ናቸው።


Zoom አጠቃቀም ላይ የተማሪዎችን ደህንነት መጠበቅ-መከላከል

በአካል ሆነ ወይም በኦንላይን ደህንነቱ የተጠበቀ ጤናማ የትምህርት ምህዳር ለመስጠት MCPS ቁርጠኛ ነው። የተማሪን ገመና እንዳይገለጥ ለማጠናከር እና ተማሪዎች ቨርቹወል ትምህርት ላይ እያሉ-virtual classroom ውጫዊ የማደናቀፍ ጣልቃገብነትን ለመቀነስ-ለመከላከል የሚከተሉትን ጨምሮ MCPS በርካታ ስልቶችን ዘርግቷል፦

  •  የ MCPS አካውንት ያላቸው ተማሪዎች እና መምህራንን ብቻ የሚያስገባ ጥብቅ የሆነ ሲስተም
  • በመምህራን አማካይነት ኦንላይን ትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ለመገምገም የሚያስችል "waiting room feature"
  • የተማሪን ካሜራዎች እና ማይክሮፎኖችን እንዳይሠሩ የሚዘጉ ቅንብሮች-Settings

ስለ ተማሪ ገመና መጠበቅ MCPS ምን ያህል ቁርጠኛ መሆኑን የበለጠ እዚህ ያንብቡ።


ጥላቻ እና አድልዎን መዋጋት

የትምህርት ሲስተም-ተቋም እንደመሆናችን፣ እኛ ያለን ግብ በትምህርት ቤቶቻችን እና በጽ/ቤቶቻችን እያንዳንዱ ሰው ዋጋ ያለው-ያላት መሆኑን፣ አብሮነት እንዲሰማው-እንዲሰማት እና ጉጉት እንዲኖረው-እንዲኖራት የሚያስችል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ ምቹ ሥፍራዎችን መፍጠር ነው። አብዛኛው የህብረተሰባችን ክፍል በዚህ ግብ እንደሚያምን እናውቃለን። ነገር ግን፣ በኤዥያን አሜሪካኖች ላይ ስለ ኮሮናቫይረስ ጥላቻ የተሞላባቸው ዘለፋዎች እንደሚሠነዘሩባቸው ከአንዳንድ የማህበረሰብ አባሎች በተከታታይ እንሰማለን። እነዚህ የጥላቻ ድርጊቶች እንደማህበረሰብ ማንነታችንን አያንፀባርቁም-አይገልጹም። በዚህ አይነት የዘረኝነት ድርጊት የሚሣተፉ ተማሪዎች እና ሠራተኞች በጣም ከባድ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል። በ MCPS በጭራሽ ለጥላቻ ቦታ አይኖርም። እነዚህን ክስተቶች በትኩረት ተመልክተን ተገቢውን የአፃፋ-ምላሽ እንሰጣለን።