Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 30, 2020

mcps logo

English | español |  中文 |   tiếng Việt | 한국어 አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ የሥራ ባልደረቦች እና የማህበረሰብ አባላት፦

ዛሬ፣ ሰኞ ማርች 30፣ COVID-19 ረቂቅ ተዋሲ-ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ከገቨርነር ላሪ ሆጋን/ Governor Larry Hogan እቤት-ውስጥ-ቆዩ የሚል ትእዛዝ መሰጠቱ ይታወቃል። ትእዛዙ የሜሪላንድ ነዋሪዎችን እጅግ አስፈላጊ በሆኑ ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር መዘዋወርን የሚከለክል ቢሆንም - ከገቨርነሩ የተሰጠውን ትእዛዝ ይመልከቱ (see the Executive Order)፣ የማህበረሰብ አባላት ወደ ትምህርት ቤቶቻችን እየመጡ ምግቦችን እና የትምህርት ቁሳቁሶችን መውሰድ መቀጠል እንዳለባቸው ይፈቅዳል።

ምግብ የመስጠት አገልግሎት በዚህ ሣምንት በታቀደው መሠረት በርካታ ጣቢያዎች ላይ multiple sites ይቀጥላል። በተጨማሪም፣ MCPS ለተማሪዎቻችን እና ለሠራተኞቻችን students እና staff የማህበራዊ-ስነልቦናዊ-ስሜታዊ፣ እና አካላዊ ደህንነት ድጋፎችንና አገልግሎቶች መስጠት ይቀጥላል።
ዛሬ እንደዚሁ የቀጣይ ትምህርት ሽግግር እቅድ (ከቤት ሆኖ መማር/የርቀት ትምህርት) የመጀመሪያው ቀን ነበር። ተማሪዎች እና ወላጆች በዚህ ሣምንት ምን መጠበቅ እንዳለባቸው የሚገልጽ መረጃ here እዚህ ይገኛል።

ማሳሰቢያ፦ እጅግ አስከፊ በሆነ ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ ውስጥ ስለምንገኝ እባካችሁ COVID-19 የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲረዳ ከገቨርነሩ የተሰጠውን ትእዛዝ እና ከማህበራዊ የአካል ንኪኪ ራሳችሁን አግልሉ-ራቁ best practices የሚለውን መመሪያ ተግባራዊ አድርጉ።
በአክብሮት የቀረበ

 Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

Important Online Resources: