Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 29, 2020

mcps logo

English | español |  中文 |  français |  tiếng Việt | 한국어 አማርኛ


ለተወደዳችሁ የ "Prekindergarten፣ Head Start፣ Pre-K Plus፣ እና Special Education Prekindergarten" ተማሪዎች ወላጆች፦

የዚህ መልእክት አላማ ስለ ቀዳሚ የልጆች ፕሮግራሞች የርቀት ትምህርት/"distance learning for early childhood programs" የሚጠበቁ ነገሮችን መረጃ-ኢንፎርሜሽን ለመስጠት ነው። የትምህርት ቤት መዘጋት ተራዝሞ ባለበት ወቅት የቅድመ ምዋእለ ህጻናት/Prekindergarten አስተማሪዎች ከህጻናት እና ከቤተሰብ ጋር እንደየ እድሜአቸው ደረጃ የርቀት ትምህርት ላይ ይሰማራሉ። በተጨማሪም፣ በመደበኛው የቢሮ ሠዓቶች አስተማሪዎች ከህጻናት ልጆች እና ከቤተሰቦች ጋር ዳግም-ግንኙነት ይዘረጋሉ።

የቅድመ ምዋእለ ህጻናት/prekindergarten ተማሪዎችን እንደየ እድሜአቸው ለማስተናገድ፣ በርቀት ትምህርቱ እቤት ውስጥ የሚሠሩ የወረቀት ሥራዎችንም ያካትታል። ቁሳቁሶችን የማከፋፈሉ ሂደት ይዘጋጃል። እነዚህን ተግባሮች ቀጥታ በሚተላለፍ የማስተማር ስርጭት እና ሪኮርድ በተደረጉ ኦንላይን ትምህርቶች በቢሮ የሥራ ሠአቶች ወቅት መምህራን ድጋፍ ይሰጣሉ። በአስተማሪ የሚመሩ ኦንላይን የትምህርት ተግባሮች ከ30 ደቂቃዎች በላይ አይራዘሙም፣ የቅድሚያ ትኩረቱ ከፍ ባለ ድምፅ ምንባብ እና የሒሳብ ሥራን እና ቀዳሚ የማንበብና የመጻፍ/early literacy እንቅስቃሴዎች ላይ ነው።

የርቀት ትምህርት ሂደትን ለማመቻቸት፣ የቅድመ ምዋእለ ህፃናት (prekindergarten) ወላጆች/ሞግዚቶች "Chrome Books" በሚከፋፈልበት ሂደት ማግኘት ይችላሉ። ምናልባት በመማሪያ ክፍሎቻቸው "Chrome Books" ተጠቅመው ስለማያውቁ፣ ለወላጆች usernames እና logins በመስጠት የቅድመ ምዋእለህጻናት ልጆች ያሏቸው ወላጆችን እናግዛቸዋለን። አክቲቪቲዎችን ለመሥራት የተዘጋጁ የርቀት ትምህርት መስጫ የህትመት ፓኬቶች እና ካለንደሮች ጭምር ይሰጣሉ።

Important Online Resources: