የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እስከ ኤፕሪል 24 ዝግ ሆነው ይቆያሉ፦ ማርች 26 የላፕቶፕ/Laptop ስርጭት ይጀመራል
የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና ማህበረሰብ፦
ዛሬ፣ማርች 25 ገቨርነር ላሪይ ሆጋን እና የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐር ኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን (Governor Larry Hogan and State Superintendent of Schools Karen Salmon) የሜሪላንድ ፐብሊክ ስኩልስ እስከ ኤፕሪል 24/2020 ዝግ እንደሚሆኑ አሳውቀዋል። ይህ የማንፈልገው አይነት ወይም ያልተጠበቀ ዜና ቢሆንም፣ ሆኖም ተደርጎም የማይታወቅ የጤና ቀውስ እየተጋፈጥን ስለሆነ መወሰድ ያለበት ውሳኔ ነው። ምንም እንኳ የትምህርት ቤት ህንጻዎቻችን ዝግ ቢሆኑም እንኳ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (Montgomery County Public Schools) የተማሪዎቻችንን የመማር፣ አካላዊ፣ ማህበራዊና-ስሜታዊ እንዲሁም ስነልቦናዊ ፍላጎቶችን ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን እንዲያውቁት እንፈልጋለን። ይህ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ህንፃ ውስጥ ሆነው ከተለማመዱት አሠራር ጋር አንድ አይነት እንደማይሆን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን፣ የትምህርት ቤቶቻችን ህንጻዎች ቢዘጉም ትምህርት እንዲቀጥል እናደርጋለን።
ለተራዘመ ጊዜ እንደሚዘጋ መገለጹ በርካታ ጥያቄዎችን እንደሚፈጥር እናውቃለን—ከተማሪ የመማር ተሞክሮ እስከ ትምህርት ካለንደር ያሉትን። ዛሬ ምሽት፣ እና በሚቀጥሉት በርካታ ቀናት፣ እነዚህን ጥያቄዎች እና አሳሳቢ ነገሮችን ለመመለስ ለተማሪዎች፣ ለሠራተኞች እና ለወላጆች መልእክቶችን እንልካለን።
ህንፃዎቻችን ቢዘጉም እንኳ፣ የተማሪዎቻችንን ትምህርት እናስቀጥላለን። የዚህ እቅድ አንዱ አካል በእርግጠኝነት የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ክሮምቡክ እና ላፕቶፕ እንዲሁም ኢንተርኔት "Chromebook laptops and the internet" እቤታቸው ማግኘት መቻላቸውን ማረጋገጥ ነው። ነገ ሐሙስ፣ ማርች 26 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ላፕቶፖችን/laptops ለተማሪዎች ማከፋፈል ይጀምራል። ስለ ስርጭቱ ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች ይገኛል።
በስቴት ሱፐርኢንተንደንት አማካይነት የትምህርት ቤት መዘጋት እንዲራዘም የተላለፈው ውሳኔ ለቤተሰቦቻችን ከባድ እንደሚሆን እናውቃለን። ትምህርት ቤት የካውንቲያችን እና የማህበረሰባችን ልብ ነው። ነገር ግን፣ የእያንዳንዱን ሰው ደህንነት እና የኮሮና ቫይረስ/ተዋህሲ COVID-19 ወረርሽኝ ለመግታት የተወሰደ ትክክለኛ ውሳኔ ነው።
እባክዎ እርስበርስ በመደጋገፍ በጤንነት ይቆዩ። በዚህ ሁላችንም በአንድነት ነን።
ከአክብሮት ጋር
Jack R. Smith Ph.D.
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ ዶ/ር
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር) የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ
ሐሙስ ማርች 26 ጀምሮ ለተማሪዎች
ላፕቶፕ/Laptop ማደል ይጀመራል
ትምህርት ቤቶች ለተራዘመ ጊዜ ሊዘጉ እንደሚችሉ ታሳቢ በማድረግ ዝግጅት በማድረግ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከቤታቸው ትምህርት ለመከታተል እንዲችሉ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ላፕቶፖችን/Laptops ይሰጣል። የላፕቶፕ/Laptop ስርጭቱ ሐሙስ፣ ማርች 26 ይጀመራል። ዲቫይሶቹ ውስን ስለሆኑ የሚሰጡት እቤታቸው ኮምፒውተር ወይም ላፕቶፕ ለሌላቸው የሚሰጡ ናቸው።
ላፕቶፕ/laptop ለመቀበል፣ ተማሪዎች (ወይም ወላጅ/ሞግዚት) የተማሪው(ዋ)ን መታወቂያ (ወይም የተማሪው(ዋ)ን የመታወቂያ ቁጥር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የማከፋፈያ ቦታዎቹ በትምህርት ቤት ደረጃ ይዘጋጃሉ። የተሟላ መመሪያ እንዲሁም የሚከፋፈሉባቸው ቀኖች፣ ጊዜ እና ቦታዎች ከዚህ በታች በ--ተዘርዝረዋል በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የኮሮናቫይረስ የመረጃ ድረ-ገጽ/MCPS Coronavirus Information website። ተማሪዎች እና ወላጆች የስልክ ቁጥር 240-740-7023 በመደወል መረጃ ለማግኘት ይችላሉ።
ጠቃሚ ማስታወሻ፦እቤታቸው ኢንተርኔት ለሌላቸው ቤተሰቦች፣ Comcast በኢንተርኔት ኢሰንሻልስ ፕሮግራሙ/Internet Essentials program አማካይነት ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት ይሰጣል። ስለዚህ ፕሮግራም የበለጠ መረጃ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል https://internetessentials.com/። MCPS እንደዚሁ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተወሰነ ቁጥር "mobile Wi-Fi hotspot" ዲቫይሶች አሉት። እነዚህ ዲቫይሶች ወደፊት ቆይተው ይከፋፈላሉ።
የማከፋፈያ ቀኖች እና ጊዜዎች
- ሐሙስ፣ ማርች 26፣ 8 a.m.-11:15 a.m.: ጠቅላላ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች
- ሐሙስ፣ ማርች 26፣ 12:45 p.m.-4 p.m.: የሚከተሉት የኤለመንተሪ ት/ቤቶች
አርኮላ/Arcola |
ግለንአላን/Glenallan |
ኬምፕ ሚል/Kemp Mill |
ቤል ፕሬ/Bel Pre |
ጆርጅያን ፎረስት/Georgian Forest |
ስትራትሞር/Strathmore |
ካሼል/Cashell |
ጁዲዝ ረስንክ/Judith Resnik |
ሰኩያህ/Sequoyah |
ካንድልውድ/Candlewood |
ፍለወር ሂል/Flower Hill |
ሚል ክሪክ ተወን/Mill Creek Towne |
ሉሲ ቪ. ባርንስለይ/Lucy V. Barnsley |
ፍለወር ቫሊ/Flower Valley |
ሜሪቬል/Maryvale |
መዶው ሆል/Meadow Hall |
ሮክ ክሪክ ቫሊ/Rock Creek Valley |
ቤልስ ሚል/Bells Mill |
ሰቨን ሎክስ/Seven Locks |
ቤቨርሊ ፋርምስ/Beverly Farms |
ፖቶማክ/Potomac |
ዌይሳይድ/Wayside |
ሃይላንድ/Highland |
ኦክላንድ ተሬስ/Oakland Terrace |
ሮክ ቪው/Rock View |
ግለን ሄቨን/Glen Haven |
ፍሎራ ኤም. ሲንገር/Flora M. Singer |
ውድሊን/Woodlin |
ቤል/Beall |
ኮሌጅ ጋርደንስ/College Gardens |
ሪቼ ፓርክ/Ritchie Park |
ትዊንብሩክ/Twinbrook |
ባያርድ ረስቲን/Bayard Rustin |
ክሎቨርሊ/Cloverly |
ስቶንጌት/Stonegate |
በርተንስቪል/Burtonsville |
ፌርላንድ/Fairland |
ግሪንካስል/Greencastle |
ጋልዌይ/Galway |
ዊሊያም ታይለር ፔጅ/William Tyler Page |
ባኖክበርን/Bannockburn |
ብራድለይ ሂልስ/Bradley Hills |
በርኒንግ ትሪ/Burning Tree |
ካርደርሮክ ስፕሪንግስ/Carderock Springs |
ውድ ኤከርስ/Wood Acres |
|
|
|
- ዓርብ፣ ማርች 27፣ 8 a.m.-11:15 a.m.: የሚከተሉት የኤለመንተሪ ት/ቤቶች
ካፒቴ. ጄምስ ዳሌይ/Capt. James Daly |
ፎክስ ቻፕል/Fox Chapel |
ክላርክስበርግ/Clarksburg |
ዊሊያም ቢ. ጊብስ/William B. Gibbs |
ሊትል በነት/Little Bennett |
ሲዳር ግሮቭ/Cedar Grove |
ስኖውደን ፋርም/Snowden Farm |
ዊልሰን ዊምስ/Wilson Wims |
ቤልሞንት/Belmont |
ግሪንውድ/Greenwood |
ኦልነይ/Olney |
ብሩክ ግሮቭ/Brooke Grove |
ሼርውድ/Sherwood |
ስቴድዊክ/Stedwick |
ዋትኪንስ ሚል/Watkins Mill |
ዌትስቶን/Whetstone |
ሳውዝ ሌክ/South Lake |
ብራዎን ስቴሽን/Brown Station |
ራቼል ካርሰን/Rachel Carson |
ፊልድስ ሮድ/Fields Road |
ጆንስ ሌን/Jones Lane |
ዘርጉድ ማርሽል/Thurgood Marshall |
ኤስ. ክሪስታ ማክሉፍ/S. Christa McAuliffe |
ሳሊ ኬ. ራይድ/Sally K. Ride |
ሌክ ሴኔካ/Lake Seneca |
ዋተርስ ላንዲንግ/Waters Landing |
አሽበርተን/Ashburton |
ከንሲንግተን ፓርክውድ/Kensington Parkwood |
ዋይንጌት/Wyngate |
ፋርምላንድ/Farmland |
ጋረት ፓርክ/Garrett Park |
ለክስማኖር/Luxmanor |
ጎሸን/Goshen |
ሮዝሞንት/Rosemont |
ሱሚት ሆል/Summit Hall |
ዋሽንግተን ግሮቭ/Washington Grove |
ጌትርስበርግ/Gaithersburg |
ለይቶንስቪል/Laytonsville |
ስትሮውበሪ ኖልስ/Strawberry Knoll |
ግሬት ሴኔካ ግሪክ/Great Seneca Creek |
ሮናልድ ማክኔር/Ronald McNair |
ስፓርክ ኤም. ማትሱናጋ/Spark M. Matsunaga |
ዳርንስታወን/Darnestown |
ዳይሞንድ/Diamond |
ክሎፐር ሚል/Clopper Mill |
ጀርመንታወን/Germantown |
|
|
- ዓርብ፣ ማርች 27፣ 12:45 p.m.-4 p.m.: የሚከተሉት ኤለመንተሪ ት/ቤቶች
ሞንትጎመሪ ኖልስ/Montgomery Knolls |
ኒው ሃምፕሻየር ኢስቴትስ/New Hampshire Estates |
ኦክ ቪው/Oak View |
ፓይን ክረስት/Pine Crest |
ታኮማ ፓርክ/Takoma Park |
ፓይኒ ብራንች/Piney Branch |
ሃርሞኒ ሂልስ/Harmony Hills |
ቼቪ ቼዝ/Chevy Chase |
ኖርዝ ቼቪ ቼዝ/North Chevy Chase |
ሮክ ክሪክ ፎረስት/Rock Creek Forest |
ሮዝሜሪ ሂልስ/Rosemary Hills |
ቤተዝዳ/Bethesda |
ሶምረስት/Somerset |
ዌስትብሩክ/Westbrook |
ኢስት ሲልቨር ስፕሪንግ/East Silver Spring |
ፎረስት ኖልስ/Forest Knolls |
ሃይላንድ ቪው/Highland View |
ሮሊንግ ተሬስ/Rolling Terrace |
ስላይጎ ክሪክ/Sligo Creek |
ብሩክሄቨን/Brookhaven |
ሳርጀንት ሽራይቨር/Sargent Shriver |
ቬይረስ ሚል/Viers Mill |
ዌለር ሮድ/Weller Road |
ዊህተን ውድስ/Wheaton Woods |
ኮልድ ስፕሪንግ/Cold Spring |
ስቶን ሚል/Stone Mill |
ደፊይት/Dufief |
ፎልስሚድ/Fallsmead |
ሌክውድ/Lakewood |
ትራቪላህ/Travilah |
ክሊርስፕሪንግ/Clearspring |
ዳማስከስ/Damascus |
ሎይስ ፒ. ሮክዌል/Lois P. Rockwell |
ውድፊልድ/Woodfield |
ሞኖከሲይ/Monocacy |
ፑልስቪል/Poolesville |
በርንት ሚልስ/Burnt Mills |
ካኖን ሮድ/Cannon Road |
ክረስትሄቨን/Cresthaven |
ዶ/ር ቻርልስ ድሪው = Dr. Charles Drew |
ሮሶኮ ኒክስ/Roscoe Nix |
ጃክሰን ሮድ/Jackson Road |
ብሮድ ኤክረስ-ለሌክ/Broad Acres/Leleck |
ዌስትኦቨር/Westover |
ቤተሰብ ላፕቶፖችን/Laptops ከየት ነው መውሰድ ያለባቸው?
- የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ፦ ተማሪዎቹ ከሚማሩበት ት/ቤት መውሰድ አለባቸው።
- የመካከለኛ ደረጃ-ሚድል ስኩሎች፦ ለመኖሪያ ቤታቸው ከሚቀርበው የኤለመንተሪ ት/ቤት መውሰድ ይችላሉ (የትምህርት ቤት ሥራ አመላካች/School assignment locator ይጠቀሙ ለአንቺ/ለአንተ ማህበረሰብ የተመደበውን ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት ካላወቅህ(ሽ)።
- የኤለመንተሪ ት/ቤት ተማሪዎች፦
- የተለዩ ፕሮግራሞች ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ፦ ተማሪው(ዋ) በማግኔት ወይም የተመረጠ ፕሮግራም፣ የሪጅናል ስፔሻል ኢጁኬሽን ፕሮግራም ስኩል ኮሚኒቲ ቤዝድ ወይም ለርኒንግ ፎር ኢንዲፔንደንስ የመሣሰሉት/magnet or Choice program, a regional special education program (such as School Community Based or Learning For Independence) ወይም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ቦታዎች በማናቸውም የሚገኙ ፕሮግራሞች፣ ከየትኛውም ቤታችሁ አቅራቢያ ከሚገኘው የኤለመንተሪ ት/ቤት ላፕቶፕ=laptop መቀበል ትችላላችሁ።
- ካርል ሳንድበርግ የትምህርት ማእከል/Carl Sandburg Learning Center
- ሮክ ተሬስ ት/ቤት - Rock Terrace School
- ስቴፈን ኖልስ ትምህርት ቤት/Stephen Knolls School
- ሎንግቪው ትምህርት ቤት/Longview School
- RICA
- ብሌር ጂ. ኢዊንግ ሴንተር/(ፕለም ኦርቻርድ፣ አቨሪ ሮድ እና ክሎቨርሊፍ የሚገኙበት ቦታዎች) Blair G. Ewing Center (Plum Orchard, Avery Road and Cloverleaf sites)
- ማክዶናልድ ኖልስ ኤርሊ ቻይልድሁድ ሴንተር/MacDonald Knolls Early Childhood Center
- በኢሞሪግሮቭ የሚገኘው አፕካውንቲ የህፃናት ማዕከል (Upcounty Early Childhood Center at Emory Grove)
- ወዴት መሄድ እንዳለብዎት እርግጠኛ ካልሆኑ፣ School assignment locator በአቅራቢያዎ የሚገኝ የኤለመንተሪ ት/ቤት ለማግኘት School assignment locator ይጠቀሙ።
- ላፕቶፕ/laptop መቀበል ከሚፈልግ/ከምትፈልግ ተማሪ ጋር አዋቂ አብሮ እንዲሆን አበክረን እናበረታታለን።
- ላፕቶፕ/laptop በሚከፋፈልበት ቀን ለመውሰድ ካልቻሉ፣ MCPS በመጪዎቹ ቀናት ላፕቶፕ/laptop የሚወስዱበትን ተጨማሪ እድሎችን ኢንፎርሜሽን ይሰጣል።
ስለሚከፋፈልበት ቀን ለወላጆች/ለተማሪዎች መመሪያ
- በመኪና የሚመጡ ከሆነ፣ እባክዎ የተማሪው(ዋ)ን መታወቂያ ወይም የመታወቂያ ቁጥሩን ሠራተኛ ከመኪና መስኮት ወይም ከ ስድስት ጫማ ርቀት ለማንበብ በሚችል አይነት ትልቅ አድርገው በወረቀት ጽፈው ይዘው ይምጡ። የሥራ ባልደረባ የእርስዎን ተማሪ መታወቂያ ቁጥር በመመዝገብ ላፕቶፕ/laptop ይሰጣል-ትሰጣለች።
- ወደ ማከፋፈያ ስፍራው በእግር የሚሄዱ ከሆነ፣ እባክዎ የተማሪዎ(ዋ)ን መታወቂያ ወይም የመታወቂያ ቁጥሩን አዘጋጅተው ይሂዱ። የሥራ ባልደረባ የእርስዎን ተማሪ መታወቂያ ቁጥር በመመዝገብ ላፕቶፕ/laptop ይሰጣል-ትሰጣለች።
- ላፕቶፕ/laptop ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት በማህበራዊ ግንኙነት አካላዊ ግንኙነትን ስለማስወገወቅትድ መመሪያዎችን ያስታውሱ (በሰዎች መካከል የስድስት ጫማ እርቀት ይጠብቁ)። እባክዎ የትራፊክ ሁኔታ ለመቆጣጠር ከ MCPS ሠራተኞች የሚሰጡትን መመሪያዎች ይከትሉ።
- ላፕቶፖች/Laptops የተሰጣቸው ተማሪዎች ስለ ስለ ላፕቶፖች/Laptops ያለባቸውን ሃላፊነት መግለጫ ከ (አባሪ ዶኩመንት ይመልከቱ)።
|