Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 13, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어አማርኛ

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

በትላንትናው ቀን እንደገለጽንላችሁ፣ የኮሮና ቫይረስን COVID-19 (coronavirus) ወረርሽኝ ለመቀነስ-ለመከላከል ከሰኞ ማርች 16 ጀምሮ እስከ ዓርብ ማርች 27/2020 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሙሉ ይዘጋሉ። ይህ የትምህርት ቤቶች መዘጋት በማህበረሰባችን ለብዙዎች የማይመቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን የምንገዘብ ስለሆነ ጥያቄዎቻችሁን እና ስጋቶቻችሁን ለመመለስ ከበርካታ የካውንቲ ኤጀንሲዎች እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብረን መሥራታችንን እንቀጥላለን።

እንደዚህ አይነት የት/ቤት መዘጋትን ታሳቢ በማድረግ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ለብዙ ሣምንት በትጋት እየሠሩ ሰንብተዋል። እባክዎ ይህ በፍጥነት እየተከሰተ ያለው ሁኔታ በብዙ ነገሮች ላይ ተጽእኖ እንደሚያስከትል ይወቁ፦ የስፕሪንግ እረፍትን ጨምሮ፣ መደበኛ የፈተና አሰጣጥ፣ አድቫንስድ የምደባ ፈተናዎች፣ እና የስፖርት ሁነቶች ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። በእነዚህ አስቸጋሪ/ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሠራተኞቻችን ሥራቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን መረጃዎች እንደደረሱን ዝርዝሮችን እና ውሳኔዎችን በፍጥነት እናሳውቃለን።  ስለ ትዕግስትዎ በቅድሚያ እናመሰግናለን።

የሚከተለው በበርካታ ቁልፍ ጉዳዮች ዙርያ የዲስትሪክቱ አዲስ እና ወቅታዊ መረጃ ነው፦

የትምህርት ቁሳቁሶች/ማቴሪያሎች እና ሪሶርሶች ተደራሽነት
የትምህርት ተግባሮች/አክቲቪቲዎች እና ቁሳቁሶች-ማቴሪያሎች በ myMCPS Classroom አማካይነት በአውታረመረብ-ኦንላይን ላይ ይገኛል። የህትመት ማቴሪያሎች ለትምህርት ቤቶች ተሠራጭተዋል እና ማክሰኞ፣ ማርች 17 ከምግብ ቦታዎች ለመውሰድ ይቻላል። እነዚህ ተግባሮች የታሰቡት ቀድሞ የተማሩትን ለመከለስ እና ለመለማመድ ነው። አክቲቪቲዎቹ ዲዛይን የተደረጉት ትምህርት ቤቶቻችን ዝግ ሆነው እስከቆዩበት ድረስ ነው።

የእርስዎ ልጅ በትምህርት እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲጠመድ-እንድትጠመድ ሪሶርሶችን ለመስጠት በቁርጠኝነት ተዘጋጅተናል።

ቁሳቁሶችን-ማቴሪያሎችን ለማግኘት እባክዎ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይከተሉ፦

  • ይህንን ድረ-ገጽ ይጎብኙ፦ https://www.montgomeryschoolsmd.org/curriculum/contingency። 
  • ተገቢውን የክፍል ደረጃ ምልክት ይጫኑ።
  • የእርስዎ ልጅ ኮርሱን ለመሣተፍ Join Here የሚለውን ምልክት መጫን ይችላል/ትችላለች።
  • የእርስዎ ልጅ የ MCPS Google account በመጠቀም ሎግኢን ለማድረግ ይችላል/ትችላለች። የራሳቸውን ሎግኢን እና ፓስዎርድ (login and password) ለማያውቁ የኤለመንተሪ ተማሪዎች፣ ሰኞ ማርች 16/2020 ለሁሉም የኤለመንተሪ ቤተሰቦች ConnectEd መልእክት ይላካል። If your child still has difficulty logging in, please refer to the Frequently Asked Questions (FAQs) at http://bit.ly/mcpsmd-course-faq
  • እያንዳንዱ myMCPS Classroom ኮርስ እንኳን ደህና መጡ ደብዳቤ እና መመሪያዎችን ያካትታል።

እነዚህ አክቲቪቲዎች-ተግባሮች የተነደፉት ልጅዎ ብቻው(ዋ)ን ለመሥራት እንዲችል/እንድትችል ተደርጎ ቢሆንም እባክዎ ከልጅዎ ጋር ለመሥራት ነፃነት ይሰማዎት። በተጨማሪ፣ እንዲያነቡ፣ play board games እንዲጫወቱ፣ ማስታወሻዎችን እንዲጽፉ፣ እና ማናቸውንም ለልጅዎ ጠቃሚ/ተገቢ ነው በሚሉት አክቲቪቲዎች ላይ እንዲሳተፉ ቤተሰቦችን እናበረታታለን። ልጆች በ MCPS ማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች ላይ እንዲሳተፉ ተጨማሪ ፍንጮችን እና ሃሳቦችን እንሰጣለን (Twitter እና Facebook)።

የምግብ ሥርጭት
ለተማሪዎች በ 20 ቦታዎች ላይ “Grab-N-Go” ምግብ የምናሠራጭ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን። የቦታዎቹን ዝርዝር እዚህ ማግኘት ይችላሉ። ነጻ ምግብ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 11 a.m. to 1 p.m. የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎች ምግብ ለማግኘት መታወቂያ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን ከ 18 ዓመት እድሜ በታች መሆን አለባቸው። የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት ወደ ማንኛውም ቦታ መሄድ ይችላሉ።

መረጃ-ኢንፎርሜሽን እና ሪሶርሶች
እነዚህ ለማህበረሰባችን አስቸጋሪ ወቅቶች ናቸው። በካውንቲያችን፣ በስቴት እና በአገር አቀፍ ደረጃ ከባድ የጤና ቀውስን በጋራ እየተጋፈጥን ነው። የራስዎን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን የመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስዱ እናበረታታለን። እባካችሁ እርስበርስ ተደጋገፉ እና ለሚያስፈልጋቸውም የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉ። ለትምህርት ቤተሰቦቻችን የሚረዱ ጥቂት የትምህርት ቤት ሲስተም እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን ዝርዝር የሚገልጽ ዶኩመንት አዘጋጅተናል። ዶኩመንቱን እዚህ መመልከት ይችላሉ። ተጨማሪ ሪሶርሶች እና መረጃዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የኮሮና ቫይረስ ድረ-ገጽ ላይ MCPS coronavirus webpage በቀጣዮቹ ሁለት ሣምንት ይገለጻል-ፖስት ይደረጋል።

የማካካሻ ቀኖች
ስለ ስፕሪንግ እረፍት እና የማካካሻ ቀኖች በአሁኑ ወቅት ምንም ውሳኔ አልተደረገም። ካላንደራችንን እና የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የሰጠውን ሃሳብ እየገመገምን ስለሆነ በተቻለ ፍጥነት ለቤተሰቦች ተጨማሪ መረጃ- እናስተላልፋለን።

ስለ ህፃናት እንክብካቤ
ትምህርት ቤቶች ተዘግተው በሚቆዩበት ሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ የልጆች እንክብካቤ ሰጭዎች በያዙበት ሥፍራ እያገለገሉ ያሉትን ቤተሰቦች ለመርዳት ከፈለጉ ክፍት ሆነው መቀጠል ይችላሉ። በመጀመሪያ የትምህርት ቤት ህንፃዎች መጽዳት ስላለባቸው፣ እንክብካቤ ሰጪዎች አገልግሎታቸውን እሮብ፣ ማርች 18 ይጀምራሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ለልጆች እንክብካቤ ከሚሰጡ እና የማህበረሰብ ፋሲሊቲዎች ጋር ስለ ጊዜ ምደባ እና የሥራ ሂደት በጋራ እየሠሩ ናቸው። የእንክብካቤ ሰጭዎች ዝርዝር በማህበረሰብ ፋሲሊት አጠቃቀም ድረገጽ Community Use of Public Facilities በመጪዎቹ ቀናት ይገለጻል። ስለሚቀጥሉት ሁለት ሣምንቶች እንዴት እንደሚሠሩ እባክዎ የእርስዎን ፕሮቫይደር ያነጋግሩ።

ወቅታዊ መረጃዎች እና የጥያቄዎች መልሶች በየጊዜው ስለሚገለጹ እባክዎ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን ድረ-ገጽ/MCPS website ዘወትር መጎብኘትዎን ይቀጥሉ። ማንኛውም አይነት የተለየ ጥያቄ ወይም ስጋት ካለዎት ASK MCPS line መስመርን በስልክ ቁጥር 240-740-3000 ማግኘት ይችላሉ።