Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 11, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어አማርኛ

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-

በዋሽንግተን አካባቢ የ COVID-19 (ኮሮና ቫይረስ) አስከፊ ተጽእኖ እያደገ ሲሄድ፣ MCPS ለሁሉም ቤተሰቦች፣ ሠራተኞች እና ለተማሪዎች፣ ስለኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ እና ምንጮችን፣ ማህበረሰባችንን እና የትምህርት ቤቶቻችንን ሥራዎች እንዴት ሊነካ እንደሚችል ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት ቁርጠኝነታችን ይቀጥላል።

ትምህርት ቤቶቻችን ክፍት እንደሆኑ የሚቀጥሉ ሲሆን የማስተማር ተግባርም በመደበኛ ሁኔታ ይቀጥላል። ለማስታወስ ያህል፣ ህዝባዊ የጤና ቀውስ በሚከሰትበት ወቅት ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት ውሳኔ የሚሰጠው በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንት/Montgomery County Department of Health and Human Services አማካይነት ነው። ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የሚወሰን ከሆነ፣ ለእኛ ከተገለጸልን በኋላ በፍጥነት ጠቅላላ ህብረተሰቡ እንዲያውቀው እናደርጋለን።

የተማሪዎቻችንን እና የሠራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ MCPS የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይቀጥላል። ከማርች 9 የመረጃ ልውውጥ በኋላ የተገኙት የሚከተሉት ጥቂት አዲስ መረጃዎች ናቸው

ስለ መስክ ጉዞዎች እና አትሌቲክስ የበለጠ ማእቀብ ማድረግ

ከሰኞ፣ ማርች 16/2020 ጀምሮ ከስቴት ውጪ የሚደረጉ የመስክ ጉዞዎች በሙሉ እና የአትሌቲክስ ክንውኖች ቀጣይ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ታግደዋል። ይህ መመሪያ ኤፕሪል 20/2020 ከማለፉ አስቀድሞ ወቅታዊ ይደረጋል። በሜሪላንድ የሚካሄዱ በጊዜ ሠሌዳ የተያዙ ጉዞዎች እና የአትሌቲክስ እንቅስቃሴዎች በሙሉ በተያዘላቸው እቅድ መሠረት ይቀጥላሉ።

የስፕሪንግ እረፍት Spring Break

ስለ ስፕሪንግ የእረፍት ጊዜ እንዲቀየር ወይም እንዲራዘም ለ MCPS ጥያቄዎች እየቀረቡ ናችው። በዚህ ወቅት፣ MCPS የስፕሪንግ እረፍት ጊዜን የመቀየር እቅድ የለውም። የስፕሪንግ እረፍት የተያዘው ከ ኤፕሪል 6 - 13 ድረስ ነው። ስለ እነዚህ ቀኖች ማናቸውም ለውጦች የሚደረጉ ከሆነ፣ ለህብረተሰባችን እናሳውቃለን።

ስለ ተማሪ የትምህርት ሁኔታ

የእኛ ግባችን ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽነት ያላቸው ስልቶችን ሁሉ በመጠቀም የተማሪዎች ትምህርት የመከታተል ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረው ማረጋገጥ ነው። ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ቢዘጋ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ለተማሪዎች በርካታ የተለያዩ የማስተማሪያ ማቴሪያሎችን እና ሪሶርሶችን አዘጋጅተዋል። እነዚህ ቁሳቁሶች/ማቴሪያሎች በህትመት ቅርጸት እና በ "myMCPS Canvas platform and the MCPS website" አውታረመረቦች ይሰጣሉ። በ-- ማርች 9/2020 የማህበረሰብ የተላለፈ መልእክት ላይ እንደገለጽነው፣ እነዚህ ቁሳቁሶች/ማቴሪያሎች እና ሪሶርሶች ሊገኙ የሚችሉት ትምህርት ቤቶች የሚዘጉ ከሆነ ብቻ ነው። በዚህ ወቅት፣ በአካባቢ እና በስቴት የጤና ባለሙያዎች ሌላ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ እስካልሆነ ድረስ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ እና መደበኛ የማስተማር ሥራም ይቀጥላል።

ስለ ተማሪ መቅረት

በትምህርት ቤቶቻችን እና በማህበረሰባችን መካከል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋት እያደገ መምጣቱን እንገነዘባለን። የጤና ኃላፊዎች ስለትምህርት ቤቶቻችን የሚኖረው ስጋት ዝቅተኛ ነው የሚለውን እምነታቸውን ማካፈል እንደቀጠሉ ሳለ፣ አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን እቤታቸው ማቆየትን ጨምሮ አሁኑኑ ተጨማሪ እርምጃች እንዲወሰዱ መፈለጋቸውን እንገነዘባለን። ጤነኛ የሆኑ ተማሪዎች እና ሠራተኞች በሙሉ መደበኛ ትምህርት እንደተለመደው መከታተል ይችላሉ/አለባቸውም፣ ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል ወይም ከጤንነት ጋር በተገናኘ ምክንያት ልጆዎን እቤት ማቆየት ከፈለጉ፣ ልጅዎ የቀረባቸው-የቀረባቸው ቀኖች ይቅርታ ይደረግለ(ላ)ታል። ወላጆች ልጆቻቸው ወደ ትምህርት ቤት መመለሳቸውን በሦስት ቀን ውስጥ እንዲገልጹ እንጠይቃለን። የእርስዎ ልጅ (ልጆች) ወደ ትምህርት ቤት ሲመለስ/ስትመለስ/ሲመለሱ የማካካሻ ሥራ እንዲሠሩ ይፈቀዳል።

ስለ COVID-19 (ኮሮና ቫይረስ) ከልጆችዎ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለብዎት

በርካታ ቁጥር ያላቸው ተአማኒ ብሔራዊ ድርጅቶች ለወላጆች፣ ለእንክብካቤ ሰጪዎች እና ለመምህራን ስለ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታ ከልጆቻቸው ጋር የሚነጋገሩበትን መመሪያ አዘጋጅተዋል። አንዳንዶቹ ሪሶርሶች በእኛ--የኮሮና ቫይረስ ድረ-ገጽ/coronavirus webpage ሊገኙ ይችላሉ። በተጨማሪ ከዚህ በታች በተገለጹት አገናኝ መረቦች ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

ስለ COVID-19 ኮሮና ቫይረስ ከልጆች ጋር መነጋገር/Talking to Children About COVID-19 (Coronavirus): የወላጅ መገልገያ/A Parent Resource (ከልጆች ጋር ለመነጋገር የበለጠ የሚረዳ መረጃ/More information to help conversations with children)

ለልጆች ብቻ፦ ስለ ኮሮና ቫይረስ አስቂኙ/ኮሚኩ ተመራማሪ/A Comic Exploring the New Coronavirus

ወቅታዊ መረጃዎች እና ሪሶርሶች

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ምክንያት ማንኛውም መረጃ/ኢንፎርሜሽን ከካውንቲው የጤና ኃላፊዎች እና ከ MCPS በቀጥታ ይተላለፋል። ወሳኝነት ያላቸው መረጃዎች/ኢንፎርሜሽኖች በጠቅላላ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ጋር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ በተለያዩ አይነት የመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ይተላለፋሉ፦ BlackBoard ConnectEd፣ ConnectEd phone calls፣ የ MCPS website-ድረገጽ እና የኮሮና ቫይረስ ድረገጽ/coronavirus webpage እንዲሁም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን/MCPS social media pages (Twitter እና Facebook) የሞንትጎመሪ ካውንቲን የኮሮና ቫይረስ ድረ-ገጽ/MCPS coronavirus webpage እንዲመለከቱ እናበረታታዎታለን። ለኮሮና ቫይረስ ተጋልጫለሁ ብለው የሚያምኑ ከሆነ ስለ ጤንነት ማንን ማግኘት እንዳለብዎት የበሽታ መከላከል ማዕከልን (CDC) ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲያነቡ እናደፋፍራለን።

ስለ ጤንነትዎ ምርጥ ተሞክሮዎች

የዚህን ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል CDC እና የአካባቢ የጤና ኃላፊዎች የሚከተሉትን ጠቃሚ ተሞክሮዎች እርምጃዎችን ገልጸዋል፦

  • ህመምተኛ ከሆኑ ሰዎች ጋር ግንኙነት አስወግድ(ጂ)።
  • ከታመምክ-ከታመምሽ እባክህ(ሽ) በቤትህ(ሽ) ቆይ።
  • ከታመምክ-ከታመምሽ አትጓዝ-አትጓዢ።
  • እጆችዎን በተደጋጋሚ በሳሙናና በውሀ ይታጠቡ።
  • ሳሙና እና ውኃ ካልተገኘ አልኮልነት ያለው የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳንታይዘር/alcohol-based sanitizer ተጠቀም(ሚ)።
  • ሲያስልህ(ሽ) ወይም ሲያስነጥስህ(ሽ) በለስላሣ የንፅህና ወረቀት ወይም በእጅጌ አፍህ(ሽ)ን እና አፍንጫህ(ሽ)ን ሸፍን(ኚ)።

ስጋት ተደቅኖብናል ወይም ለኮሮና ቫይረስ ተጋልጠናል ብለው የሚያምኑ ግለሰቦች የግል የጤና ተንከባካቢያቸውን እንዲያገኙ እናበረታታለን። በቅርብ ጊዜ በ CDC ዝርዝር ውስጥ ወዳሉት አገሮች ተጉዘው ካልሆነ፣ ራስዎን ማግለል አያስፈልግዎትም። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና የተላላፊ በሽታ መከላከያ/Montgomery County Department of Disease Control and Epidemiology በስልክ ቁጥር 240-777-1755 ወይም የሜሪላንድ የጤና እና ተላላፊ በሽታ መከላከያ ቢሮ/Maryland Department of Health Infectious Disease Bureau በስልክ ቁጥር 410-767-6700 ማነጋገር ይችላሉ። በእርስዎ ዶክተር ለመታየት ካልቻሉ፣ የድንገተኛ ጤና እንክብካቤ ፋሲሊቲ ወይም የአስቸኳይ ህክምና ክፍልን እንዲጎበኙ እናበረታታለን። ለተጨማሪ መመሪያ ይህንን ድረ-ገጽ https://www.montgomerycountymd.gov/HHS/RightNav/Coronavirus.html ይጎብኙ።

በዚህ አስጊ ወቅት የእኛ ጥረት እና ቅድሚያ ትኩረታችን የተማሪዎች ደህንነት-ጤንነት እና ስለ ማንኛውም ወሳኝ መረጃዎች/ኢንፎርሜሽን ለማህበረሰባችን የማሳወቅ ቁርጠኝነት አለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools