Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 9, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንት (DHHS) እና የአስቸኳይ ሁኔታ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጋር ስለ COVID-19 (ኮሮና ቫይረስ/coronavirus) ቁጥጥር እና ወቅታዊ መረጃ ስለመስጠት በጋራ መሥራቱን ይቀጥላል። ብዙ ወላጆች እና በርካታ የማህበረሰብ አባላት ስለ COVID-19 እና በማህበረሰባችን ላይ እና በትምህርት ቤት ሥራ ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንደሚፈጥር መረጃ እንደሚፈልጉ እናውቃለን። ይህንን ለማህበረሰባችን እጅግ ወቅታዊ መረጃ/ኢንፎርሜሽን የያዘ ማርች 5/2020 በተጻፈ ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው፣ የመጀመሪያዎቹ 3 COVID-19 የተገኙት በሜሪላንድ ስቴት ሲሆን ህመተኞቹ ነዋሪነታቸው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ነው። እባክዎ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የካውንቲውን ጋዜጣዊ መግለጫ ያንብቡ። ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ሁኔታዎች ማርች 8 በሜሪላንድ ተከስቷል ። አዲስ ከተከሰቱት ሁለት ህመምተኞች አንዱ(ዷ) ነዋሪነቱ(ቷ) በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ነው። የካውንቲው የጤና ኃላፊዎች ለዲስትሪክቱ እስካሁን እምነታቸውን የሚገልጹት ለትምህርት ቤቶቻችን ያለው ስጋት ዝቅተኛ መሆኑን እና ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው ስራቸውን እንዲቀጥሉና መደበኛ የማስተማር ስራዎችም መቀጠል እንዳለባቸው ነው። በካውንቲው ውስጥ ሁኔታዎች የሚቀየሩ ከሆነ፣ የትኞቹ ትምህርት ቤቶች መዘጋት እንደሚኖርባቸው DHHS ይወስናል። በድጋሚ፣ በሜሪላንድ ህግ መሠረት፣ በህብረተሰብ የጤና ቀውስ ምክንያት ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት የሚወሰነው በጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንት/Department of Health and Human Services አማካይነት መሆኑን ደግመን በአጽንኦት ለመግለጽ እንወዳለን።
ስለ ተማሪ የመማር ሁኔታ
ትምህርት ቤቶች የሚዘጉ ከሆነ ብቻ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሠራተኞች እና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ለሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ማቴሪያሎችን እና ሪሶርሶችን የማዘጋጀት ሥራውን ይቀጥላል። ግባችን ለሁሉም ተማሪዎች የተዘጋጁ እና ተደራሽ የሆኑ ስልቶችን/ዘዴዎችን በመጠቀም ተማሪዎች መማራቸውን ማረጋገጥ ነው። በዚህ ወቅት፣ ከ DHHS መመሪያ ጋር በማጣጣም፣ ጤናማ ተማሪዎች እና ሠራተኞች በጠቅላላ መደበኛ የትምህርት ቤት ክትትል እንደተለመደው መቀጠል አለባቸው።

ወከባ፣ ማስፈራራት፣ እና ትንኮሳ፣ ማስጨነቅ
ስለ ኮሮና ቫይረስ አንዳንድ የተማሪ ቡድኖች ላይ ዒላማ የተደረገ ማሾፍ፣ ወከባ፣ ማስፈራራት፣ እና ትንኮሳ፣ ማስጨነቅ እንደሚካሄድ ከአንዳንድ የማህበረሰብ አባላት ሰምተናል። ይህ አይነት አድራጎት ተቀባይነት የሌለውና በትእግስት የሚታለፍ አይደለም። ማሾፍ፣ ወከባ፣ ማስፈራራት፣ እና ትንኮሳ፣ ማስጨነቅ ካጋጠማችሁ ወይም ከተመለከታችሁ እባካችሁ ለትምህርት ቤት ሥራ ባልደረባ ይንገሩ ወይም የወከባ፣ ማስፈራራት፣ እና ትንኮሳ፣ ቅጽ ላይ ይሙሉ።

የመረጃ/የኢንፎርሜሽን ምንጮች
በዲስትሪክቱ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በመጥቀስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የሚያሳስቡ በርካታ የሀሰት መግለጫዎች በማህበራዊ ሚድያ እየተሠራጨ መሆኑን ተገንዘበናል። በዚህ አይነት የተለቀቁት የሀሰት መረጃዎች ናቸው። ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተገናኘ ማንኛውም መረጃ/ኢንፎርሜሽን ከካውንቲው የጤና ኃላፊዎች እና ከ MCPS በቀጥታ ይተላለፋል። ወቅታዊ መረጃዎች በጠቅላላ ከ MCPS ቤተሰቦች-ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ የመገናኛ አውታሮች እና መገልገያዎችን BlackBoard ConnectEd፣ ConnectEd phone calls፣ የ MCPS website-ድረ-ገጽ እና ስለ ኮሮና ቫይረስ ድረ-ገጽ/cornavirus webpage እንዲሁም መደበኛ የ MCPS ማህበራዊ ሚድያ ገጾች (Twitter and Facebook) የመሣሰሉትን በመጠቀም ይተላለፋሉ። ስለ ኮሮና ቫይረስ የ MCPS ድረ-ገጽ  = MCPS coronavirus webpage በየጊዜው እንዲጎበኙ እናደፋፍራለን።

በዚህ እጅግ ከባድ እርእስት ማንም ሰው ሆነ ብሎ ማህበረሰባችንን ሲያሳስት/ሲያወናብድ ጥልቅ ቅሬታ ይሰማናል። በሀሰት የተሠራጨ መረጃ በመፍጠር የተገኘ ማንኛውም ኃላፊነት ያለበ(ባ)ት ተማሪ በ MCPS የተማሪ ስነምግባር ደምብ መሠረት ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበ(ባ)ታል።

ስለ ጤንነትዎ ምርጥ ተሞክሮዎች
የዚህን ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል CDC እና የአካባቢ የጤና ኃላፊዎች የሚከተሉትን ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ገልጸዋል፦

  • ህመምተኛ ከሆኑ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያስወግዱ።
  • ከታመሙ-እባክዎ በቤትዎ ይቆዩ።
  • ከታመሙ አይጓዙ።
  • እጆችዎን በተደጋጋሚ በሳሙናና በውኃ ይታጠቡ።
  • ሳሙና እና ውኃ ካልተገኘ አልኮልነት ያለው የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳንታይዘር/alcohol-based sanitizer ይጠቀሙ።
  • በሚያስልዎት ወይም በሚያስነጥስዎት ጊዜ በንፅህና ወረቀት ወይም በእጅጌ አፍዎን እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ።

ስጋት ተደቅኖብናል ወይም ለኮሮና ቫይረስ ተጋልጠናል ብለው የሚያምኑ ግለሰቦች የግል የጤና ተንከባካቢያቸውን እንዲያገኙ እናበረታታለን። በቅርብ ጊዜ በ CDC ዝርዝር ውስጥ ወዳሉት አገሮች ተጉዘው ካልሆነ፣ ራስዎን ማግለል አያስፈልግዎትም። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና የተላላፊ በሽታ መከላከያ/Montgomery County Department of Disease Control and Epidemiology በስልክ ቁጥር 240-777-1755 ወይም የሜሪላንድ የጤና እና ተላላፊ በሽታ መከላከያ ቢሮ/Maryland Department of Health Infectious Disease Bureau በስልክ ቁጥር 410-767-6700 ማነጋገር ይችላሉ። በእርስዎ ዶክተር ለመታየት ካልቻሉ፣ የድንገተኛ ጤና እንክብካቤ ፋሲሊቲ ወይም የአስቸኳይ ህክምና ክፍልን እንዲጎበኙ እናበረታታለን። ለተጨማሪ መመሪያ ይህንን ድረ-ገጽ https://www.montgomerycountymd.gov/HHS/RightNav/Coronavirus.html ይጎብኙ።

ሁኔታውን እየተከታተልን በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን።

 

በአክብሮት

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of School

Raymond L. Crowel, Psy.D.
Director, Montgomery County Department of Health and Human Services