Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: July 18, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


ከ MCPS የተላለፈ አስፈላጊ የቪድኦ መግለጫ


ቪዲዮ ይመልከቱ

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች፡-

ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን "MCPS Fall 2020" ዳግም መተለም፣ መክፈት፣ ማገገም-ማንሠራራት ረቂቅ እቅድ ጁላይ 11 ከገለጽን ወዲህ፣ በሺህዎች ከሚቆጠሩ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ምላሾቻቸውን ሰምተናል። የቀረቡትን ረቂቅ አማራጮች ከተመለከታችሁ በኋላ ሃሳባችሁን፣ ጥያቄዎቻችሁን እና ስጋቶቻችሁን በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ጽፋችኋል፣ ደውላችኋል እና በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ  ገልጻችኋል። በጁላይ 11 መልእክቴ ላይ በገባሁት ቃል መሠረት የሞትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከማህበረሰባችን ለመስማት እና እነዚህን ጉዳዮች እና ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በመጪዎቹ ቀናት እና ሣምንታት ከህብረተሰባችን ጋር አብረን ለመሥራት ጠንካራ እምነት አለን። የአሁኑ ረቂቅ እቅድ አሁን ያለንን ሃሳብ  የሚያመለክት ሲሆን ከግብረመልሶቹ በሚገኙት ምክረሃሳቦች እና በጤና ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ማሥተካከያ፣ ማጣሪያ እና ማሻሻያ ይደረግበታል።

ስለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት የእኛ ግብ MCPS ተማሪዎች በጠቅላላ በአካልም ሆነ ወይም በቨርቹወል  ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እና የትምህርት ተሞክሮዎችን ለመስጠት ነው። እና በሚቀጥሉት ወራት በተቻለ መጠን በርካታ ተማሪዎችን በዘላቂነት በአካል ለማስተማር መልሰን የማምጣት ተስፋ ቢኖረንም፣ ከስቴት እና ከአካባቢ ሃላፊነት ካላቸው አካላት ይሁንታ ፈቃድ ካላገኘን በስተቀር አናደረገውም፣ ማድረግም አንችልም። ከካውንቲ ሃላፊዎቻችን "county’s Chief Health Officer, Dr. Travis Gayles, County Executive March Elrich, the Governor and the State Superintendent of Schools" የመጨረሻ ውሳኔ እስከምናገኝ እየተጠባበቅን በእቅዶቻችን ላይ በትጋት እየሠራን እንቀጥላለን።

እንደምናውቀው፤ ገቨርነር ላሪ ሆጋን እና የስቴት ሱፐርኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን (Governor Larry Hogan and State Superintendent Karen Salmon) ስለ ትምህርት ቤቶች ያሉትን እቅዶች በሚቀጥለው ሳምንት ወቅታዊ መግለጫ ይሰጣሉ። ኦገስት 6 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ MCPS ትምህርት ቤቶች ፊት--ፊት ተገናኝቶ የማስተማር ሞዴል መቼ ሊሆን እንደሚችል ጊዜያዊ ውሳኔ ይሰጣል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሠራተኞች በጠቅላላ ኦገስት 31 ትምህርት ቤት ይጀመራል። ጠቅላላ  ተማሪዎች  የትምህርት ዓመቱን ቨርቹወል የሚጀምሩ ሲሆን  በንቃት እና በትጋት ትምህርት ይሰጣቸዋል። በዚህ የማስጀመሪያ ቨርቹወል ሞዴል ለምን ያህል ጊዜ እንደምንቆይ ስለማናውቅ፣ ከስቴት እና ከአካባቢ የጤና ሃላፊዎች የሚሰጠንን መመሪያ እየጠበቅን በቅርብ እየተባበርን በመሥራት የህብረተሰብ ጤና ሁኔታን እየተቆጣጠርን ለትምህርት ቤቶቻችን ዲስትሪክት እጅግ ተመራጭ የሆነ ውሳኔ ላይ እንደርሳለን።

በሆነ መንገድ ትምህርት ቤት ፊት--ፊት በአካል ሥራ የሚጀመርበት ሞዴል ላይ ዝግጅት ማድረጋችንን እንቀጥላለን። በአካል ትምህርት ቤት መሆን ያለባቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች መኖራቸው ይታወቃልስንክልና ያለባቸው ተማሪዎች፣ የቋንቋ ችሎታን የማዳበር አገልግሎት የሚሰጣቸው ተማሪዎች፣ በሊተረሲ እና በሒሳብ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች፣ ስለአካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ደህንነታቸው በትምህርት ቤት የተዋቀረ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች፣ በድህነት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች፣ እና ዝርዝሩ ይቀጥላል። በአጭሩ፣ ተማሪዎች በጠቅላላ ትምህርት ቤት ይፈልጋሉ-ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን ከስቴት እና ከአካባቢ ሃላፊዎች ፈቃድ እስከምናገኝ ድረስ ፊት--ፊት በአካል ትምህርት መስጠት የማይጀመር መሆኑን ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ።

ባለፈው ሣምንት ከእናንተ ያገኘናቸውን እሳቤዎች እና ጥያቄዎችን በተመለከተ ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ወቅታዊ መግለጫዎች እና አስፈላጊ ማብራሪያዎች ናቸው።፡ በወረርሽኙ ምክንያት በማህበረሰባችን ውስጥ አለመተማመን እና አደናቃፊ ሁኔታዎች ውጥረትና ስጋቶች መፈጠራቸውን እናውቃለን። እባካችሁ እኛ እንደምንሰማችሁና እንደምናዳምጣችሁ እንድታውቁልን እንፈልጋለን። መልእክቶቻችሁን እና ፖስት የምታደርጓቸውን ሃሳቦቻችሁን እየተመለከትን-እያነበብን ይህንን እጅግ ፈታኝ እና ውስብስብ ሁኔታ እንዴት በፍጥነት እና በትብብር እንደምንሻገር መንገዶችን ለመቀየስ እየሠራን እንገኛለን። ፍጹም የሆነ እቅድ ሊኖር አይችልም፣ ከበድ ያለ ምርጫ ማድረግ ብቻ ነው። በዚህ ውስጥ እየሠራን ለማለፍ-ለመሻገር የእናንተን ትብብር እና ትእግስት እንጠይቃለን። ስለ እቅዶቻችን እርግጠኛ እና ትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት Fall Recovery webpage-የፎል ማገገሚያ ድረገጽ እንዲያነቡ እናበረታታለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools 

ጃክ አር. ስሚዝ (/)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ

አትሌቲክስ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በመጀመሪያው ምዕራፍ-Phase 1Return to R.A.I.S.E. እቅድ ይቀጥላል፣ ይህም ማለት እስከ ኦገስት 11/2020 ድረስ እንደወቅቱ ትግበራዎችን በቨርቹወል ተሳትፎ የሚመለከት እና በአካል በመገኘት የሚከናወኑ-ትግበራዎችን የሚከለክል መመሪያ ነው። በዚህ ወቅት በአካል በመገናኘት የሚደረጉ የሠመር ተለምዷዊ ሁኔታዎች እና እንቅስቃሴዎች በጠቅላላ ተሠርዘዋል። ከኦገስት 12 በኋላ ስለሚደረጉ የፎል ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ፕሮግራሞችን በሚመለከት ወቅታዊ መረጃ ጁላይ መጨረሻ ላይ ይገለጻል። ውሳኔዎች የሚደረጉት በስቴት እና በካውንቲ የጤና መመሪያ መሠረት ይሆናል። MCPS በትምህርት ቤቶች መካከል ስለሚደረጉ የአትሌቲክስ ፕሮግራም ትግበራዎች እና ውድድሮች ወቅታዊ መረጃ የኮቪድ-19 አትሌቲክስ መረጃ - COVID-19 Athletics Information section of the MCPS Athletics webpage - የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አትሌቲክስ ድረገጽ ላይ ይገኛል።

ጤና እና ደህንነት

ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች እንድንመለስ ከተፈቀደልን፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስጋት ለመቀነስ በተቻለ መጠን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እናከናውናለን። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ባለፉት ጥቂት ወራት የግል መከላከያ ቁሳቁሶችን (PPE) የእጅ ንጽህና መጠበቂያ-hand sanitizer ሣሙና-soap እና ሌሎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለማዘዝ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቷል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች እና ተማሪዎች እንዲጠቀሙ የፊት መሸፈኛዎችን ይሰጣል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በተቻለ መጠን በርካታ የተለያዩ አይነት የፊት መሸፈኛዎችን እየገዛ ነው። ደጋግሞ ለመጠቀም የሚሆኑ እና አንዴ ከተጠቀሙበት በኋላ የሚወገዱ አይነት የፊት መሸፈኛዎች ይኖራሉ። በርካታ ቁጥር የፊት መሸፈኛዎችን እየገዛን ቢሆንም እንኳ 166,000 ተማሪዎች እና 24,000 የሥራ ባልደረቦች ለሲስተሙ በጠቅላላ ተጠቅመው ወዲያው  መወገድ ያለበት አይነት የፊት መሸፈኛዎችን በየቀኑ የመግዛት አቅም እንደማይኖረን እባክዎ ይገንዘቡ። ተማሪዎች እና ሠራተኞች ደጋግሞ የሚያገለግል የፊት መሸፈኛዎችን እንደአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ የተለያየ የአጠቃቀም ስልቶች ላይ እንደገፋለን። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሠራተኞች እና ለተማሪዎች ዓመቱን በሙሉ የተወሰኑ አይነት የፊት መሸፈኛዎችን ብቻ ነው የምንሰጠው ተብሏል የሚል አይነት ወሬ ሰምተው ከሆነ፣  እርሱ ሀሰት ነው የፊት መሸፈኛዎች በየቀኑ እንደሚያስፈልጉ እና ይህንን መልእክት ተግባራዊ ለማድረግ የእርስዎንም ልጅ ለዚህ ለውጥ እንዲያዘጋጁ የእርስዎን ድጋፍ እንደምፈልግ ግልጽ ላደርግልዎት እፈልጋለሁ። ተማሪዎች እና ሠራተኞች በጠቅላላ ደህና መሆናቸውን እና  በዚህ አዲስ ሁኔታ ውስጥ ተማሪዎች እንዴት መሥራት እንዳለባቸው መማር የሚችሉበት እድል ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን።

የእጅ ንጽህና መጠበቂያን-hand sanitizer በሚመለከት፣ በተቻለን መጠን የተለያዩ አይነቶችን እየገዛን ነው። የማይነኩ አይነት ማስወገጃዎችን-touchless dispensers በአሁኑ ወቅት ለመግዛት አስቸጋሪ በመሆኑ እና በአገሪቱ በጠቅላላ በርካታ የቢዝነስ ድርጅቶች እና የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶችም ተመሣሣይ የእጥረት ችግር እያጋጠማቸው ቢሆንም፣ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ-hand sanitizer ለመስጠት በርካታ አማራጮች አሉ። ለትምህርት ቤቶች እና ለቢሮዎች በሙሉ ለማዳረስ የተቻለንን ያህል የተለያዩ አይነት ማስወገጃዎችን-range of dispensers እንገዛለን። የእጅ ንጽሕና መጠበቂያ-Hand sanitizer በጠቅላላ ህንጻዎቻችን ውስጥ ይኖራል።

የትምህርት ቤት ህንጻዎችን ስለማጽዳት

 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የህንፃዎች አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች ቁጥራቸው ተጨምሮ ዘወትር በመገኘት የፋሲሊቲዎችን ሃላፊነት ይኖራቸዋል። ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች በጠቅላላ ዘወትር ንጽህና እንዲኖራቸው ጽዳት ይደረግላቸዋል። በተመሣሣይ ሁኔታ፣ መምህራን እና ተማሪዎችም ቀኑን ሙሉ የየራሳቸውን አካባቢ በንጽህና የመጠበቅ እና እቃዎቻቸውን የማጽዳት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። መምህራን ቀኑን ሙሉ አካባቢያቸውን እና ቁሳቁሶችን ለማጽዳት መጠቀም የሚችሉት ቆሻሻና ብክለትን ለመከላከል የሚረዱ መጥረጊያዎች-disinfecting wipes እና ሌሎች የጽዳት ቁሳቁሶች ይህንን ጥረት ተግባራዊ ለማድረግ ከሚያስችል መመሪያ ጋር በተጨማሪ ታዟል። የእያንዳንዳችንን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ በጋራ መሥራት አለብን።

የሠራተኞች እና የቤተሰብ ፍላጎት-ምርጫ

MCPS ሠራተኞች የራሳቸው ሁኔታ ካስገደዳቸውና  ከፈለጉ  ከርቀት የመሥራት መወሰን ይችላሉ። የሆነ ሆኖ፣ እንደሁኔታው-flexibility የመወሰኑ ሁኔታ ከተማሪዎቻችን እና ከሲስተሙ ፍላጎት ጋር ተመዛዝኖ መደረግ እንዳለበት መገንዘብ ያስፈልጋል። አንዳንድ ሠራተኞች ካለባቸው ግዴታ አንፃር እንዲሁም ለቤተሰብ አባላት እንክብካቤ የመስጠትና የመጠበቅ ሃላፊነት ስለሚኖርባቸው ለጥቂት ጊዜ በአካል ወደ ማስተማሪያ ክፍል ለመምጣት እንደማይችሉ እንገነዘባለን። እንዲሁም በርካታ የሥራ ባልደረቦቻችን በወረርሽኙ ወቅት  በህንጻዎች ውስጥ ለመሥራት የሚከለክላቸው ልዩ ሁኔታዎች እንደሚኖርባቸው እንገነዘባለን። የእያንዳንዱ ፍላጎት ይሄ አይደለም። ወደ ህንጻዎች በምንመለስበት ጊዜ፣ የእናንተን ተማሪዎች እና ሠራተኞች ደህንነት ለመጠበቅ ተገቢ የጤና አጠባበቅ እና የደህንነት እርምጃዎች በሙሉ ተግባራዊ መደረጋቸውን እናረጋግጣለን።

ጁላይ 11 መልእክታችን ላይ እንደገለጽነው ወላጆች ልጃቸው-ልጆቻቸው በቅይጥ-ቨርቹወል ትምህርት ሞዴል ወይም በቨርቹወል የትምህርት ሞዴል ብቻ መሣተፍ እንደሚፈልጉ አማራጭ ይኖራቸዋል። የእነዚህ ዝርዝሮች  እየተጠናቀቁ ስለሆነ እንደጨረስን የሚገለጽ ይሆናል።

የመማሪያ ክፍል አዘገጃጀት-አደረጃጀት

አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ መርህ ላይ ተመርኩዘን በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ በአማካይ ከ 12 እስከ 15 ተማሪዎችን ለማስቀመጥ እንደምንችል እናምናለን። እባክዎ ይሄ የመጀመሪያ ስሌት መሆኑን ይወቁ። አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መመርያን በማክበር በቂ የመቀመጫ ቦታ አደረጃጀት እንዲኖር ለማመቻቸት ይህ ቁጥር ከክፍል ወደ ክፍል ሊለያይ ይችላል።

ቪዲዮ ይመልከቱ