Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: July 11, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች፦

ገቨርነር ሌሪ ሆገን/Larry Hogan እና የስቴቱ የትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ የሆኑት ካረን ሳልሞን/ Karen Salmon ሁሉም የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች ህንፃዎች ለቀሪዉ 2019-2020 የትምህርት አመት ዝግ ሁኖ እንደሚቆይ ካስታወቁበት ሜይ 6 ጀምሮ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ 2020-2021 የትምህርት አመት ጅማሮን አስመልክቶ በንቃት እቅድና ዝግጅት እያደረገ ነዉ። መገምት እንደምትችሉት፣ ይህ ሥራ ፈታኝ እና በሚያስደንቅ ሁኔታ ውስብስብ ነበር። ት/ቤቶችን እንደገና ለማስጀመር በርከት ባሉ አማራጮች ላይ ተወያይተናል እንዲሁም ገምግመናል፣ እናም እውነቱ የእኛ የትምህርት ሲስተም ያጋጠመውን የማስተማሩን፣ የሥራ ሂደትን እና የሎጀስቲክስ ውጣ ውረዶችን በሙሉ ለማሟላት የሚያስችል አንድ ብቸኛ አማራጭ የለም። ከሁሉም በላይ፣ እኛ ያቀረብናቸው አማራጮች በሙሉ በፍትሃዊነት እና በሚዛናዊነት፣ እንዲሁም በከፍተኛ ጥራት/ምጡቅነት፣ መነጽር መታየት ያለባቸው ሲሆን የ 166,000 ተማሪዎችን እና የ24,000 የሥራ ባልደረቦችን ጤንነት እና ሠላም በሚያረጋግጥ ሁኔታ መሆን አለበት።  ለተማሪዎቻችን እንደገና መሠናዶ በማድረግ እና እያንዳንዱን የትምህርት ቤት ተሞክሮዎች ዳግም በማሰብ ፊት ለፊት ተጋፍጠናል። እናምእኛ ተስፋ ያደረግነው ወይም ጭራሽ የገመትነዉ ባይሆንም እንኳ፣ ባልተጠበቀ መንገድ—አዲስ የጤና መመሪያዎችን/ፕሮቶኮሎችን፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅን እና ሌሎች በርካታ ነገሮችን ጨምሮ የ 2020-2021 የትምህርት ዓመትን እንጀምራለን ።

እኛ ግባችን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በሙሉ በአካልም ሆነ በርቀት/በቨርቹወል ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ተሞክሮዎችን መስጠት ነው። ቨርቹወል/የርቀት ትምህርትን በማጎልበት እና ወጥነት ባለዉ መልኩ ፊት-ለፊት በአካል ለማስተማር በተቻለ መጠን በርካታ ተማሪዎች እንዲመጡ በማድረግ ዕቅድ ላይ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን። ለተወሰኑ ወይም ለሁሉም ተማሪዎች የት/ቤት ህንፃዎችን እንደገና ለመክፈት የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠዉ በገቨርነር ሆገን እና በዶ/ር ሳልሞን አማካይነት መሆኑን ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ። እንዲሁም በካውንቲያችን እና በስቴቱ አሁን ያለዉን የጤና ሁኔታዎች ግምት ዉስጥ በማስገባት የ MCPS ት/ቤቶችን እንደገና መክፈቱ ምናልባት ምን ሊመስል እንደሚችል ተጨማሪ ድጋፍ እና መመሪያ ከሚሰጡን ከአከባቢያችን ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እንሰራለን።

ዛሬ የምጽፍላችሁ፣ ለፎል የእኛን አንዳንድ የመነሻ እሳቤዎች እና እቅዶቻችንን ለእናንተ ለማጋራት ነዉ። የMCPS Fall 2020፦ ዳግም መተለም፣ ዳግመኛ መክፈት፣ ማገገም/ወደ መደበኛ ሁኔታ የመመለስ መመሪያ ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንትእና ከካውንቲያችን የጤና አጋሮችባገኘነው መረጃ እና መመሪያ መሠረት በዚህ ወቅት የምናስባቸውን ጥቂት የማገገሚያ ሞዴሎችን አጠቃላይ እይታ ግንዛቤ ይሰጣል። ድጋሚ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ ይሄ ረቂቅ መመሪያ መሆኑን እና ከእናንተ—ከአጋሮቻችን፣ ከሠራተኞች እና ከተማሪዎች ምክረሃሳቦችንና ግብረመልሶችን ካገኘን በኋላ በእነዚህ አስተያየቶች ላይ ማሻሻያዎችን፣ ማስተካከያዎችን ማድረግ እንቀጥላለን። እነዚህን ረቂቅ አማራጮች በምታዩበት ጊዜ በርካታ ጥያቄዎች እና አሳሳቢ ነገሮች ሊኖራችሁ እንደሚችል እናውቃለን እናም በመጪዎቹ ሣምንታት እናንተን የሚያሳስቧችሁን ነገሮች እና ለጥያቄዎቻችሁ ምላሽ ለመስጠት እያንዳንዱን እርምጃ ከእናንተ ጋር እንደምንሠራ ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን። በስፕሪንግ ወቅት የትምህርት ቤቶች ሳይታሰብ በድንገት መዘጋት እና ስለ ፎል እርግጠኛ መሆን አለመቻል በቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ መረበሽ/መታወክ እና ውጥረት መፍጠሩን እንገነዘባለን። ቤተሰቦች ከተለየ ሁኔታቸው በመነሣት የገለጹልንን ገጠመኞቻቸውን እና ፍላጎታቸውን በርካታ አተያይ ግምት ውስጥ አስገብተናል።

{MCPS ፎል 2020፦ ዳግም መተለም፣ ዳግመኛ መክፈት፣ ማገገም/ወደ መደበኛ ሁኔታ የመመለስ—ረቂቅ መመሪያ ያንብቡ}

ት/ቤቶችን እንደገና ለመክፈት የእኛ አቀራረብ/ዘዴ የትብብሮሽ ጥረት ነው። ከወላጆች፣ ከሰራተኞች፣ ከማህበረሰቡ አባላት እና ከሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ግብረ መልስ ሰብስበናል። ይህ ግብረ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ/መነሻ ዕቅዳችንን እንዴት እንዳቀረብን አሳውቋል። ከ 55,000 በላይ ወላጆች/ሞግዚቶች የእኛን የፎል መልሶ ማገገሚያ የዳሰሳ ጥናት አጠናቀዋል። አካላዊ ጤንነት እና ደኅንነት ፣ ተማሪዎች እንዴት ትምህርት እንደሚያገኙ አማራጮች መኖር ፣ እና በየሳምንቱ ወጥ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ መኖሩ ለ MCPS ቤተሰቦች በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት አሳይቷል። ስለ ፎል በምናደረገዉ እቅዳችን ላይ ህብረተሰቡን በውይይት ማሳተፋችንን እንቀጥላለን እናም ሀሳብዎን እና አስተያየትዎን እንዲያጋሩ በርከት ያሉ እድሎችን እንሰጥዎታለን። በረቂቅ መመሪያው መጨረሻ ላይ በቀዳሚ/መነሻ ማገናዘቢያችን ላይ የእርስዎን ግባት/አስተያየት ማስገባት የሚችሉበት በግብረመልስ ቅጹ ላይ አገናኝ/ሊንክ አቅርበናል። የእርስዎ ግብረመልስ ወሳኝ ነው።

የትምህርት ቦርድ በጁላይ 14 የሥራ ስብሰባዉ ወቅት በቀዳሚ/መነሻ የማገገሚያ ዕቅዶች ላይ ውይይት ያደርጋል። ይህንን አስፈላጊ ውይይት እንድታዳምጡ እናበረታታለን። ስብሰባው የሚጀምረው በ 12:30 p.m. ሲሆንበ MCPS ድረ-ገጽ እና በ MCPS TV (Comcast 34፣ Verizon 36፣ RCN 89) በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። በህያው/live ለመመልከት ካልቻላችሁ፣ የስብሰባዉ ቀረጻ በ YouTube እና በ MCPS ድርጣቢያ ላይ ይለጠፋል።

ሁላችንም በጋራ አንድ ላይ ነን። የቤተሰቦችን፣ የተማሪዎቻችንን እና የሠራተኞቻችንን ፍላጎት በማሟላት ረገድ በጋራ አጠቃላይ እቅድ ለመገንባት በቀጣይነት ስለሚያደርጉልን ትብብር እና ድጋፍ አመሰግናለሁ።

በፎል የመልሶ ማገገሚያ ዕቅድ ላይ ፣ በ MCPS መገልገያዎች ውስጥ የሕፃናት መንከባከቢያ እና ወቅታዊዉ ዘረኝነት በአእምሮ ጤና ላይ ስለሚያስከትለው ተፅእኖ Waymaking/መንገድ ከፋች ተከታታይ ዉይይት ከዚህ በታች በመጪው ምናባዊ/ቭርቹወል ውይይትን አስመልክቶ ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች አሉ።

ከአክብሮት ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D. 
Superintendent of Schools



MCPS ፎል 2020፦ ዳግም መተለም፣ ዳግመኛ መክፈት፣ ማገገም/ወደ መደበኛ ሁኔታ የመመለስ— ቨርቹወል ዉይይት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሮብ፣ ጁላይ 15 በድስትሪክቱ የማገገሚያ ረቂቅ እቅድ ላይ ለመወያየት ቨርቹዋል ውይይት/virtual conversation ያካሄዳል። የህብረተሰቡ አባላት ስለ መልሶ መክፈት የመጀመሪያ/መነሻ ረኮመንደሽንስ ከ MCPS መሪዎች የበለጠ ይማራሉ እናም ጥያቄዎችን የመጠየቅ እድልም ይኖራቸዋል። ቨርቹወል ዉይይቱ በ 6:30 p.m.የሚጀምር ሲሆን  በ MCPS ድረገጽ፣ በ MCPS TV እና በ YouTube ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ጥያቄዎችን ቀደም ብለዉ ይላኩ www.mcpssubmitfeedback.org ን በመጎብኘት። ሐሙስ ፣ ጁላይ 16 በስፓንሽ እንዲኖር ይደረጋል። በ MCPS ድርጣቢያ እና በ MCPS YouTube ጣቢያ ላይ ይለጠፋል።


በ MCPS ፋሲሊቲዎች የሚካሄድ የህፃናት እንክብካቤ

MCPS ለተማሪዎች ት/ቤቶችን እንደገና ለመክፈት የጤና እና የደህንነት ስራዎች እቅዶች እና ፕሮቶኮሎችን ለማጠናቀቅ እየሰራ እንደመሆኑ፣ እንዲሁም ለልጆች እንክብካቤ ሰጭዎች የትምህርት ቤት መገልገያዎችን/ፋስሊቲዎችን ለመክፈት እየሰራን ነው። MCPS የወቅቱን የመልሶ ማገገሚያ እቅድ ሁኔታ በማስመልከት እና አቅራቢዎችን በእቅዳቸዉ ለማገዝ ቀጣይ እርምጃዎችን ለመጋራት በ MCPS መገልገያ/ፋስሊቲ ውስጥ ከሕፃናት እንክብካቤ ሰጪዎች/አቅራቢዎች ሁሉ ጋር ተገናኝቷል። በ MCPS መገልገያዎች/ፋስሊቲዎች ውስጥ ከህፃናት እንክብካቤ አቅራቢዎች ጋር ብዙ የተለያዩ የኪራይ እና የህንፃ ዝግጅቶች አሉ። የአቅራቢዎች ድጋሚ መክፈት በእነዚህ የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ይለያያል። አንዳንድ አቅራቢዎች በቅርቡ ይከፈቱ ይሆናል ፤ ሌሎች አገልግሎት ሰጭዎች ከ MCPS ለተማሪዎች ትምህርት ቤቶችን እንደገና ከመክፈት ጋር በቅንጅት ይከፈታሉ። ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን አቅራቢዎን ያነጋግሩ። በ MCPS መገልገያዎች ውስጥ ለት/ቤት ዕድሜያቸው ለደረሱ ሕፃናት እንክብካቤ እና ድጋፍ ለመስጠት እንዲሁም ት/ቤቶችን እና ፕሮግራሞችን እንደገና ለማስጀመር ሁኔታዎችን በተመለከተ ውይይቶችን ለማቀናጀት የ MCPS እና የማህበረሰብ ፋስሊቲዎች የህዝብ አጠቃቀም አብረው እየሠሩ ናቸው። 


የዘረኝነት በአእምሮ ጤና ላይ ተጽእኖን አስመልክቶ አበረታች ዉይይቶች

ሁለተኛዉ ክፍል የዘረኝነት በአእምሮ ጤና ላይ ተጽእኖን አስመልክቶ አበረታች ዉይይቶች ሰዎች የአእምሮ ጤና ጉዳዮችን በተመለከተ እንዴት እገዛ እና ድጋፍ እንደሚያገኙ፣ እንዲሁም የአእምሮ ጤና አቅራቢ የማግኘት ሀፍረትን እንዴት ማስወገድ በሚቻልበት መንገድ ላይ ትኩረት አድርጓል። ሁለቱንም ዉይይቶች መመልከት ይችላሉ እዚህ

ሱፐርኢንተንደንት ጃክ ስሚዝ - Superintendent Jack Smith በካውንቲያችን ውስጥ ዘረኝነትን የሚያንፀባርቅ የቤተዝዳ ድብደባን “Bethesda Beat” እና እኩልነት፣ ፍትሃዊነትን እና ምጡቅነትን ለማስፈን እየተካሄደ ስላለው የትምህርት ቤት ሲስተም ያለውን አሠራር በጽሑፍ ገልጸዋል።.
ጽሑፉን እዚህ article here ማንበብ ይችላሉ።


Important Online Resources: