Is this email not displaying correctly? View it in your browser

mcps logo

Welcome back!

Image
Video with Open Captions

ወደ አዲሱ የትምህርት ዓመት እንኳን በሠላም አደረሰዎት!

officer icon

አብዛኛውን እድሜዬን ተማሪ በመሆን፣ ወይም በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ሥርአት ውስጥ እየሠራሁ ቆይቻለሁ። ምንም እንኳ በዓመት የምሠራው 12 ወር ቢሆንም፣ እስካሁን ወደ ትምህርት ሲስተሙ ሥራ የሚጎርፉ ነገሮች አሉ። ለእኔ ትምህርት ቤት የሚከፈትበት የመጀመሪያ ቀን ከፍተኛ ጉጉት ያሳድርብኛል። በአዲስ ጅማሮ ላይ ተስፋ አለ። ወደ አዲስ የትምህርት ዓመት ስሻገር ስራዬን እያከናወንኩ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር፣ አዳዲስ ሰዎች ጋር እንድገናኝ እና እያንዳንዱ ተማሪ አካደሚያዊ ችግርን የመፍታት ፈጠራ እና የማህበራዊ ስሜት ክህሎትን በኮሌጅ እና በሙያ ሥራ ላይ ተግባራዊ ማድረግ “Every student will have the academic, creative problem solving and social emotional skills to be successful in college and career” የተሰኘውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተልእኮ መሣካት ለማረጋገጥ አሻሽዬ የመስራት እድል ይሰጠኛል። 

በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ የ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ይጀመራል፣ እና ከ 164,000 በላይ ከምዋእለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ 207 በሞንትጎመሪ ካውንቲ  ትምህርት ቤቶች በሮች ይጎርፋሉ። ከ 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች እስከ 1,000 አዲስ ተማሪዎች እንደሚገቡ እንጠብቃለን። በጠቅላላ ከ 11,000 በላይ የምዋእለ ህፃናት ተማሪዎች ይኖሩናል።

ለ 23,000 ሠራተኞቻችን ምስጋና ይድረሳቸውና፣ እነዚህን ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸውን ለመቀበል ተዘጋጅተና። የሚያንፀባርቁ ወለሎች፣ የተጠናቀቁ የአውቶቡስ ጉዞ መስመሮች፣ የተቀጠሩ እና ስልጠና የተሰጣቸው ሠራተኞች፣ እና ተማሪዎች በየክፍሎቻቸው ተደልድለዋል፣ የትምህርት ግብአት አቅርቦቶች ሁሉ ተዘጋጅተዋል። ... ዝርዝሩ ማለቂያ የለውም።

officer icon

ከአዲሶቹ ተማሪዎች በተጨማሪ፣ በክላርክስበርግ/Clarksburg አካባቢ ስኖውደን ፋርም ኤለመንተሪ "Snowden Farm Elementary" የተሰኘ አዲስ ትምህርት ቤት እየጨመርን ነው። ትምህርት ቤቱ የተሰየመው በ1845 ዓ.ም ወተትና የወተት ምርቶች ግብርና ልማት በጀመረው Thomas Snowden ስም ነው። ስለ ትምህርት ቤቱ ስያሜ መነሻ/ምንጭ በአጭሩ የሚገልጽ ቪድዎ እዚህ ይገኛል። ስሙ አስደሳች የሆነ ታሪክ እና ከሁላችንም የተሰወረ ኃላፊነትን ወደ እኛ ያመጣል። በማህበረሰቡ ላይ እንድንገነባ እና ኢንቨስት እንድናደርግ ጥሪ ቀርቦልናል።

የቶማስ ስኖውደን/Thomas Snowden ሦስተኛ ትውልድ-የልጅ ልጅ የሆነችው ጁአን ውድሰን/Joann Woodson በቪድዎ ላይ እንደገለጸችው ስኖውደን ፋርም ሁልጊዜም ጎረቤት ነበረ/“The Snowden Farm was always a neighbor ይህ የግብርና ከተማ ስለነበረ እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ ሁሉ ለመርዳት ዝግጁ ነበሩ። ... ነገሮችን ለማሣካት እያንዳንዱ እርስበርስ መደጋገፍ ነበረባቸው።"

ርእሰመምህሯ Yolanda Allen እንደገለጹት የትምህርት ቤቱ ስም ማህበረሰቡን አስፈንድቆታል ይላሉ። "Snowden Farm" ከተሰኘው ስያሜ (ስም) ተማሪዎች ስለ መልሶ መስጠት አስተሳሰብ፣ እርስበርስ ስለመደጋገፍ እና ማህበረሰባዊ አስተሳሰብን ይማራሉ የሚል እምነት አለኝ።"

ከትምህርት ቤት ማህበረሰባችን አሻግረን ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ፣ የእኛን ስቴት እና የእኛን ህዝብ ስንመለከት፣ ጠንካራ፣ንቁ እና አንፀባራቂ ሆኖ ለመቆየት፣ የልጆቻችን ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ እሙን ነው። ማህበረሰባችን በደንብ በተማረ ህብረተሰብ ይታመናል። ከቀለም ትምህርቱ በተጨማሪ፣ መልካም ጎረቤት እንዲሆኑ፣ እገዛ ሲያስፈልግ እንዲረዱ፣እና እርስበርሳቸው መደጋገፍን ለመማር እንዲችሉ ልጆቻችንን መርዳት አለብን።

የማህበረሰብን ጥራት/ትልቅነት በዚህ የትምህርት ሥርአት ሠራተኞች በሚሠሩት እና እርስበርሳቸው በየቀኑ በሚያደርጉት ግንኙነት ተመልክቻለሁ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጠንካራ ህብረተሰብ እና ዜጎች፣ድርጅቶች፣ መንግሥት እና ቢዝነሶች እንዴት ልጆቻችንን እንደሚረዱ ተመልክቻለሁ። ይህ ማህበረሰብ የትምህርት ሥርዓቱን እና ሥራውን በመርዳትና በመደገፍ ጠንካራ ታሪክ አለው። አንተ(ች) ጥሩ ጎረቤት ነህ(ሽ)፣መልሰህ(ሽ) ተሰጣለህ/ትሰጪያለሽ፣እርዳታ በሚያስፈልግ ጊዜ ትረዳለህ/ተረጂያለሽ፣እና የእኛን ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸውን ከፍ ታደርጋቸዋለህ/ታደርጊያቸዋለሽ። ለተማሪዎቻችን ሁልጊዜም አለኝታ ነህ(ሽ)። በውጤቱም፣እኛ ሁላችን ልንኮራበት የሚያስችለን የትምህርት ሥርዓት አለን።

ስለዚህ፣ ስኖውደን ፋርም ኤለመንተሪ ት/ቤት-Snowden Farm Elementary School የሚለውን ስም በምንሰማበት ጊዜ ሁሉ፣ ለእያንዳንዱ ተማሪ ደህንነት እንክብካቤ የማድረግ ኃላፊነት የተጣለብን መሆኑን መረዳት እና እያንዳንዱ ተማሪ ክህሎት፣ እውቀት እና ለማህበረሰብ አስተዋጽኦ ለማድረግና ለመጠቀም በራስ የመተማመን አቅም እንዳለው/እንዳላት ማረጋገጥ ይኖርብናል። የእኛ መፃኢ ጊዜ በዚህ ይወሰናል።

 

ዶ/ር ጃክ አር. ስሚዝ፣ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

ግሩም - ምንባብ፦