Is this email not displaying correctly? View it in your browser

mcps logo

ሁሉም በአንድ ላይ፦ ለተማሪዎቻችን እና ለእያንዳንዳችን የምንችለውን ሁሉ ጥረት እያደረግን ነን

 

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

 

Superintendent Jack R. Smith Ph.D.

 

ይሄ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ክስተት ነው።

በትምህርት ቤቶች በሠራሁባቸው 40 ዓመታት፣ ለእንደዚህ አይነት ሁኔታ ተቀራራቢ ነገር እንኳ ሆኖ አያውቅም።

 

በነገው ቀን፣ ከበፊቱ ፍጹም በተለየ ሁኔታ የትምህርት አሰጣጥ እንጀምራለን። ባለፉት አስርተ ዓመታት በተለያዩ ደረጃዎች እና በበርካታ መንገዶች የዲጅታል መሣሪያዎችን ከመማር ማስተማር ጋር በማዋሐድ ፊት-ለ-ፊት ስንሰራ የኖርን ድርጅት ነን። ነገር ግን፣ በየእለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች እና ወደ መማሪያ ክፍሎች እየመጡ ከአዋቂ ሰዎች ጋር እና እርስበርሳቸው በሚገናኙበት እውነታ ላይ ተመክተን መኖራችን እርግጠኛ ነገር ነው። ቢያንስ እስከ ኤፕሪል 24 ድረስ (ገቨርነር ሆጋን/Governor Hogan ትምህርት ቤቶች እስከዚያ ቀን ተዘግተው እንዲቆዩ ያራዘሙት ቀን) ሁሉ ነገር ተቀይሯል። ስለዚህ፣ ከአንድ ወር በፊት ብዙዎች እንዲህ ይሆናል ብለው አስበውት በማያቁት መንገድ ከተማሪዎች ጋር ለሚቀጥሉት አራት ሣምንታት እንሠራለን።

 

—“This is an extraordinary event in our history” የሚለውን ጥቅስ ስታነቡ—Jack Smith ስለሁኔታው እርግጠኛ ነበር ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ነገር ግን ቃሎቹ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአንድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መምህር ካገኘሁት ከሚከተለው መልክት የተወሰዱ ናቸው። መልእክቱን ለማካፈል ፈቃድ ስጠይቅ፣ መምህሩ ተስማምቷል፣ ነገር ግን ስሙ እንዳይገለጽ ጠይቆኛል።

ሃይ ዶ/ር ስሚዝ፣

 

ሁልጊዜም ለተማሪዎቻችን መልካም እንደሆነ በማሰብ በቅንነት እና ባለን እውቀት ተማምነን በምናደርገው ነገር የምንሳሳትበት መንገድ አይኖርም ለማለት እፈልጋለሁ። እንከን የሌለው እንደማይሆን ሰዎች እንደሚገነዘቡ አምናለሁ፣ ነገር ግን ሁኔታዎችን እያየን ለማሻሻል እስከቻልን ድረስ እና ተፈጥሯዊ/ለማሳካት የሚቻል እስከሆነ ድረስ፣ ሁላችንም ከሁሉ የተሻለ/ምርጥ ለማድረግ እንሞክራለን።

 

ይሄ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ/ያልተለመደ ክስተት በመሆኑ—ሁላችንም በተቻለን መጠን ማድረግ የምንችለውን በማድረግ፣ እና እያንዳንዳችን ማከናወን በቻልነው ነገር ፈራጅ ሳንሆን በፀጋ የምንቀበልበት ጊዜ ያስፈልገናል። አንተ እና አንተ የምትንከባከባቸው በሙሉ በሠላም እና በጤና እንደምትቆዩ ተስፋ አደርጋለሁ።

 

እነዚህ ቃሎች እንዴት ወደፊት መሄድ እንዳለብን ለመረዳት መንገድ ይከፍቱልናል፣ ቴዎዶር ሮዘቬልት እንደተናገረው ማድረግ የምንችለውን ማድረግ፣ ባለህ(ሽ) ነገር፣ የትም ቦታ ሆነህ(ሽ) / Theodore Roosevelt said, “to do what you can, with what you have, where you are.” የዚህ መምህር መልእክት እኔ ምን እንደማደርግ፣ ሌሎች ምን እንደሚያደርጉ፣ እና በጋራ ምን እንደምናደርግ በቅንነት በማሰብ፣ ፈራጅ ያለመሆንን ፀጋ፣ ምቹ ስለመሆን እና ስለ ትክክለኛነ ጠለቅ አድርጌ ማሰብ እንዳለብኝ አስገንዝቦኛል። ይሄ እኔ ማድረግ የምችለው ነው ወይም አይደለም፣ ምርጫው የኔ ፈንታ ነው።

 

ከጥቂት ቀናት በፊት፣ 15 ሰዎች ከተሳተፉበት ረዥም፣ ከባድ የስልክ ኮንፈረንስ ስብሰባ በኋላ፣ አምስት ሰዎች በኮንፈረንስ ክፍል ውስጥ 15 ወይም 20 ጫማ ተራርቀን ነበርን፣ ከባልደረቦቼ አንዱ በአካል እዚያ ስለነበርነው ሰዎች “We must keep in mind that this is a once-in-a-hundred-years event” በማለት ተችቷል። ከ “Spanish Flu pandemic of 1918” ጋር ለማያያዝ ነው። ለምን በመቶኛ ዓመቴ ይሆናል ነበር የእኔ መልስ / “Why did it have to happen during my 100 years!” እንደመቀለድ አይነት ነበር ያልኩት፣ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ሁላችንም የምንኖርበት ያልተጠበቀ እና ሁከት የበዛበት አዲስ ዓለም በመሆኑ ምክንያት ለራሴ በጣም እያዘንኩ ነበረ። ወደ ቢሮዬ ስመለስ ነበር የዚህን መምህር መልእክት ያገኘሁት። መልእክቱ አስተሳሰቤን እንደገና ለመቃኘት ረድቶኛል፣ እናም ለተማሪዎቻችን ምርጥ የሆኑ ነገሮችን በቅንነት እያደረግን ወደፊት እንድንራመድ አበረታቶኛል/ማደፋፈሪያ ሆኖኛል።

የሚያበረታታ፣ ጥበብ እና ተስፋ የተሞላበት መልእክት ያካፈለኝን ባልደረባዬን ላመሰግን እወዳለሁ። እያንዳንዱን የማህበረሰባችንን አባላት፣ ለተማሪዎቻችን ስለምታደርጉት ነገር አመሰግናችኋለሁ። በዚህ ሁላችንም በጋራ አንድ ላይ ነን፣ እና በጋራ ለተማሪዎቻችን ምርጥ የትምህርት ተሞክሮ እንሰጣቸዋለን፣ ከዚህ በፊት በመማሪያ ክፍል ውስጥ ሆነው ከተለማመዱት የተለየ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።

 

ጥንቃቈ አይለያችሁ እና በሠላም ቆዩ።

 


ሁላችንም በአንድ ላይ ነን

Important Online Resources: