‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ 
All In blog by MCPS Superintendent Dr. Jack R. Smith
alt_text

ሁላችንም፦ በምግባረ ሠናይ፣ በመተሳሰብ እና በጨዋነትና በእርጋታ

በርካታ የኢ-ሜይል መልእክቶች ደርሰውኛል። በአብዛኛዎቹ ቀናት በመቶዎች የሚቆጠሩ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የዚያን ሁለት ወይም ሦስት እጥፍ የሚሆኑ ናቸው። አንዳንዶቹ የሥራና የአገልግሎት እቅድና ዝግጅትን በሚመለከት ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ስለ መረጃዎች፣ እና ሌሎቹ ደግሞ ግላዊ ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ናቸው። በእኔ የኢ-ሜይል ፋይል በርካታ መልእክቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ ነገር ግን አንዳንዶቹ ከእኔ ተጣብቀው ይቀሩና ስለሁኔታዎች ያለኝን አመለካከት ወይም የግንኙነትን አድማስ ያስቀይሩኛል። በእርግጥም እነዚህ መልእክቶች ትርጉም-ፋይዳ አላቸው።

ከሁለት ሣምንት በፊት፣ትምህርት ቤቶቻችን በተዘጉ ሁለተኛ ሣምንት ላይ በእኔ --ኢሜይል Superintendent’s Blog ከአንድ መምህር ያገኘሁትን ጽሑፍ አጋርቻችሁ ነበር። ወደ አዲሱ እውነታ ከገባን ስድስተኛ ሣምንታችን ሲሆን፣ እስካሁን በዚህ(ች) መምህር መልእክት ላይ እያተኮርኩ ነው። ከመልእክቱ ውስጥ ከእኔ ጋር ተጣብቀው የቀሩት ሀረጎች፦

መልካም እና ቅንነትን በማሰብ ... በማንም ላይ ፈራጅ ሳንሆን ፀጋዎቻችንን ማካፈል ... እንደሁኔታው ማገናዘብ እና ከእውነት ያልራቅን ሀቀኛ መሆን “assuming the best of intentions … extending grace without judgment … being flexible and realistic”

እነዚህ ሀረጎች፤ አሁን በምንገኝበት ሁኔታ ለእርስበርሳችን ምን አይነት ምላሽ እንደምንሰጣጥ በኋላ ወደ ትምህርት ቤቶቻችን ህንፃዎች ስንመለስ፣ ዳግም በአካል ተገናኝተን እርስበርስ ስንነጋገር እና ጎን ለጎን ሆነን በምንሠራበት ጊዜ እርስበርሳችን ለሚኖረን ግንኙነት መሠረት እንደሚሆኑን ለማሰብ ረድተውኛል።

አሁን ያለንበትን አዲስ ገጠመኝ ውስጥ በጽናት ስናልፍ፣ አንዳንድ የ MCPS ቤተሰቦቻችን በአስቸጋሪ-አዳጋች-ከባድ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ መሆናቸውን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው። አንዳንዶቹ የሚወዷቸውን ቤተሰብ አጥተዋል፣ አንዳንዶቹ ሥራቸውን አጥተዋል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ከፊት ለፊት ሆነው ይህንን ወረርሽኝ እየተዋጉት/እየተጋፈጡት ይገኛሉ፣ እና ሁላችንም በየቀኑ ከአዳዲስ ለውጦች ጋር ራሳችንን ለማስለመድ እየጣርን እንገኛለን። ይህ በሽታ በማህበረሰባችን ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ/ጉዳት በጣም የከፋ እንዳይሆን ሁላችንም የበኩላችንን እንድናደርግ እየተጠይቅን ነው።

በቅርቡ፣ አንዲት ወላጅ እናት በዚህ ወቅት ልጆቿ ምን አይነት ትምህርታዊ ተሞክሮ ሊኖራቸው እንደሚችል ስለልጆቿ ምን ተስፋ እንደምታደርግ ከዚህ የሚከተለውን በኢ-ሜይል መልእክት አካፍላለች ። ልጆቿ ያደርጋሉ ብላ ተስፋ የምታደርገው ከአስተማሪዎቻቸው ጋር የመገናኘት እና የመነጋገር እድሎችን፣ ከእነርሱ የመስማት፣ ዝምብሎ የክለሳ ሥራዎችን ብቻ ሣይሆን ትርጉም-ፋይዳ ያላቸው የቪድኦ ትምህርቶችን እንደሚከታተሉ፣ በኢ-ሜይል እና በቢሮ ሠዓቶች ጥያቄዎችን ማቅረብ-መጠየቅ እንደሚችሉ፣ እና ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለመሻገር ሁሉም በጥሞና፣ በመተሣሠብ፣ እና ሁሉንም ነገር በእርጋታ፣ በጋራ-በትብብር እንደሚሠሩ በአጽንኦት ትገልጻለች።/ “opportunities to connect and talk to teachers, hear from them, attend interesting and engaging video lessons that are not just worksheet reviews, ask questions through email and office hours, and all work together to get through this with kindness, compassion, and a gentle approach to everything.”

ሁሉንም ነገር በቅንነትና በቸርነት፣ በርህራሄ፣ እና በእርጋታ መመልከት/“with kindness, compassion, and a gentle approach to everything”

በዚህ ወቅት እነዚህ አገላለጾች-ሀረጎች በሙሉ በአእምሮዬ ላይ ተጣብቀዋል፦ ስለሁሉም ነገር በመልካምነት እና በቅንነት በማሰብ ... በማንም ላይ ፈራጅ ሳንሆን ፀጋዎቻችንን ማካፈል ... እንደሁኔታው ማገናዘብ እና ከእውነት ያልራቅን ሀቀኞች መሆን። “ በየቀኑ እያንዳንዱን ሰው ለማግኘት-ለመድረስ እና ወደፊት ለመራመድ ምንኛ አስደናቂ መንገድ ነው።

በዚህ ሁላችንም በአንድነት በጋራ ነን።

እባክዎ ጥቂት ደቂቃዎችን ይውሰዱና ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ተስፋ ሰጪ፣ አበረታች እና እውነተኛ ምክሮችን ያዳምጡ።

We Got This MCPS

Message from President Shebra Evans

ከትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት ሸብራ ኢቫንስ የተላለፈ መልእክት፦ Message from Board of Education President Shebra Evans

Message from Board of Education Member Brenda Wolff

ከትምህርት ቦርድ ምክትል ፕሬዚደንት ብረንዳ ዎልፍ የተሰጠ መልእክት፦ Message from Board of Education Vice President Brenda Wolff

Message from Board of Education Member Patricia O'Neill

ከትምህርት ቦርድ አባል ፓትሪሻ ኦ ኔይል የተላለፈ መልእክት፦ Message from Board of Education Member Patricia O’Neill

 
Montgomery County Public Schools

View as a Web Page

Montgomery County Public Schools
850 Hungerford Drive, Rockville, MD, 20850
Call: 240-740-3000 | Spanish Hotline: 240-740-2845