Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: February 5, 2019

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የ MCPS የመንፈቀ-ዓመት የደህንነት መልእክት

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ:

 

አሁን የትምህርት ዓመት መንፈቀ-ዓመት ደርሰናል፣ ተማሪዎቻችን ሠላማዊና አመቺ የሆነ የትምህርት አካባቢ እንዳላቸው ለማረጋገጥ በተከታታይ ያደረግነውን እርምጃ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ። ከዚህ በፊት እንደተገለጸው፣ ሁሉም ተማሪዎች የወደፊት ተስፋ እንዲሰንቁ ማስቻል የትምህርት ስርዓታችን ዋናው አላማ እንደመሆኑ መጠን፣ ተማሪዎች ትምህርት ቤቶቻችን ሠላማዊና ደህንነታቸው የተጠበቀ አመቺነት ካልተሰማቸው በስተቀር ይሄ ሊሣካ እንደማይችል እናውቃለን።

 የተማሪዎች እና የሠራተኞች ደህንነት ጉዳይ የአንድ-ጊዜ ብቻ "ተነሳሽነት" ሳይሆን፣ ይልቁንም በየጊዜው የሚደረግ አሰሳ፣ ማጥራት፣ እና ለማሻሻል በቀጣይነት የሚከናወን ትጋት ነው። ስለ MCPS ሠላምና ደህንነት በርካታ መረጃዎችን በድረገጻችን ላይ <እዚህ> ለማግኘት ይችላሉ። የ MCPS ተማሪዎችን ሠላምና ደህንነት ለመጠበቅ የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማወቅ በዚህ ገፅ ላይ ምልክት/ሕዳግ እንዲያደርጉበት እና በየጊዜው እንዲያነቡት እንጋብዛለን።

በጠቅላላ ከ $8 ሚሊዮን በላይ የፈጁት እነዚህ ሁሉ የማሻሻያ ለውጦች የትምህርት ቤት ሠላምና ደህንነት ለማጠናከር እና ለድንገተኛ/አስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት ወሳኝ ናቸው። የተማሪ ስኬታማነት የመጨረሻ ተልእኮአችንና ግባችን ቢሆንም፣ የተማሪ እና የሠራተኛ ሠላም-ደህንነት ቅድሚያ ትኩረታችን መሆን አለበት። ይህንን ኃላፊነት በጥብቅ የምንመለከተው ጉዳይ እንደመሆኑ የትምህርት ቤትን ሠላም/ደህንነት ለመጠበቅ በርካታ ነገሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውን እንድታውቁ እፈልጋለሁ።

የ MCPS ማህበረሰብ ሠላምና-ደህንነትን ለማስፈን ስለምታደርጉልን ድጋፍ ሁሉ አመሰግናለሁ።

Montgomery County Public Schools


ከዚህ በታች ያሉት ጥቂት ፍንጮች ናቸው፦:

Ed Clarke, Director, Department of School Safety and Security - እንኳን ደህና መጡ አቀባበል

MCPS በዲሴምበር፣ Mr. Edward (“Ed”)ን ተቀብሏል፤ Mr. Edward (“Ed”) A. Clarke የትምህርት ቤቶች ሠላምና ደህንነት ዳይሬክተር በመሆን ወደ MCPS ቡድን እንኳን ደህና መጡ በማለት ተቀብለናል። Mr. Clarke በሜሪላንድ የትምህርት ቤቶችን ሠላምና ደህንነት ማዕከል በመምራት ከአራት ዓመት በላይ አሳልፈዋል፣ በዚህም ወቅት "Maryland Safe to Learn Act of 2018" የተሰኘ የሜሪላንድ ሠላማዊ የመማር ህገ-ደንብ ሥርአቶችን ማጎልበት እና ባጀት ማሳደግ በማዘጋጀት የረዱበት ጊዜ ነው። Mr. Clarke ቀደም ሲል በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የሠላምና ደህንነት ዳይሬክተር/MCPS Director of Safety and Security በመሆን ያገለገሉ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ መምሪያ ጡረታ የወጡ ካፒቴን ናቸው። በሚቀጥሉት ወራት፣ Mr. Clarke እና Dr. Christina Conolly, director of psychological services፣ በመሆን ስለ ትምህርት ቤት ሠላም እና ደህንነትን በሚመለከት በጠቅላላ በካውንቲው ውስጥ ከወላጆች፣ተማሪዎች እና ሠራተኞች ጋር የማህበረሰብ ውይይቶችን ያካሄዳሉ። ስለ Mr. Clarke እና Dr. Conolly የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

የትምህርት ቤት ደህንነት መሠረተ-አውታር፦:

  • MCPS የመግቢያ መቆጣጠሪያ ሲስተሞችን ለማዘመን እና በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን የመተካት አቋም ወስዷል።
  • ለትምህርት ቤቶች የጎብኚዎች ማኔጅመንት ሲስተምን (VMS) አሻሽለናል። VMS የጎብኚዎችን መታወቂያዎች እና ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ማንነት ያጣራል።
  • በ 173 ትምህርት ቤቶች የመግቢያ በር ላይ ሰኩሪቲ የሚያጣራ መሣሪያ-vestibules አለን። ከእነዚህ vestibules ስምንቱ በቅርብ ጊዜ የተተከሉ ሲሆኑ በመጨረሻ ደረጃ ግንባታ ላይ ናቸው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
  • በጠቅላላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በህንፃዎች በውስጥ እና በውጭ በሙሉ የተገጠሙ CCTV cameras/ካሜራዎች አሏቸው። በአንደኛ ደረጃ (ኤለመንተሪ) ት/ቤቶች ካሜራዎች ተገዝተው ተገጥመዋል፣ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የካሜራዎችን መሠረተ-አውታር አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ላይ አጠናክረናል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
  • በዲጂታል ሁለት-አቅጣጫ ሬድዎች/digital two-way radios አማካይነት የግንኙነት (ኮሙኒኬሽን) መሠረተ-አውታሮችን ለማዳበር እየሠራንበት ነው። አንዴ መሠረተ-አውታሩ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ በት/ቤቶች መካከል፣ በት/ቤቶች እና በደህንነት አመራር መካከል የሬድዩዮ ግንኙነትን ለማዳበር ወደሚያስችላቸው የዲጅታል ሬድዮ መገናኛ ሊያሳድጉት ያስችላቸዋል።

የት/ቤት ሠላም-ደህንነት እቅዶች እና ፕሮቶኮሎች-ሥነሥርአቶች፦:

  • ለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት ዝግጅት ሲደረግ በእያንዳንዱ ት/ቤት አዲስ፣ የግል ደህንነት እቅዶችን ለመሥራት እና የእቅዱን ተአማኒነት/ትክክለኛነት ለመቆጣጠር ከማህበረሰብ የደህንነት ኤክስፐርቶች (ባለሙያዎች) ጋር እየሠራን ነው። ይህኛው የደህንነት እቅድ የሚያተኩረው የመማሪያ ክፍል ቦታ መቀየር፣ እና ለእያንዳንዱ ት/ቤት ከክፍል ውጪ ባሉ ቦታዎች ምን አይነት የተግባር ዕቅዶች እና የቴክኖሎጂ ግብአቶች ይበልጥ ጠቃሚ እንደሆኑ በመለየት ላይ ያተኩራል።
  • በት/ቤቶች ያለውን የደህንነት/ሰኩሪቲ-ጥበቃ ሥርአቶችን እና ለአንድ ትምህርት ቤት ምን ያክል የሪሶርስ ኦፊሰር እንደሚያስፈልግ ለመገምገም ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የህግ አስከባሪ አጋሮቻችን ጋር የሚሠራ ግብረኃይል አቋቁመናል። እናም ወቅታዊ የተኩስ ጥቃት የመሠንዘር መከላከል ምርጥ ተሞክሮዎችን መሠረት በማድረግ ለሚቀጥለው ዓመት በድንገተኛ/አስቸኳይ ፕሮቶኮል ሁኔታዎች ላይ ለውጥ እናደረጋለን። .
  • ወደፊት በአካባቢያችን ተግባራዊ የሚሆን "ማስፍራራት/ዛቻዎችን አሰሳ የማድረግ ፖሊሲ" ለማዳበር ከስቴት አቀፍ ባልደረቦቻችን ጋር በትብብር እየሠራን እንገኛለን።

ዳራ (የቀድሞ ታሪክ) ማጣራት፦:

  • ተመላሽ ሠራተኞች እና አዲስ ተቀጣሪዎች ላይ የቀድሞ ታሪክ/ዳራ የማጣራት ሥርዓትን በይበልጥ ለማሻሻል፣ ህፃናትን ከጥቃት የመከላከል አገልግሎቶችን ዳራ ማጣራትን ጭምር እንቀጥላለን።
  • የሁሉንም ሠራተኞች ዳግመኛ የጣት አሻራ የመውሰድ ሂደት ጀምረናል። ይህ ሂደት በሥራ ቅጥር አንድ ጊዜ ብቻ የሚደረግ መሆኑ ቀርቶ በመደበኛነት የሚከናወን ተግባር ይሆናል።

ህግ

>በኤፕሪል 2018፣ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ ገቨርነሩ የፈረሙበት Maryland Safe to Learn Act በሜሪላንድ የትምህርት ቤት ሠላም/ደህንነት ማዕከል እና በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፖርትመንት አማካይነት የትምህርት ቤትን ሠላም/ደህንነት የመቆጣጠርን ኃላፊነት በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የተሻሻለ የሠላም/ደህንነት ጥበቃ እቅዶችን፣ ከመደበኛ እና አዳዲስ እየተከሰቱ ያሉትን ዛቻ/ማስፈራራት የሚዳስሱ አዳዲስ ፖሊሲዎችን፣ እና ለድንገተኛና አስቸኳይ ሁኔታዎችን ለመከላከል ጠንካራ ሥርአቶች/ፕሮቶኮሎች እና ስልጠናዎች እንዲዳብሩ ህጉ ይደነግጋል። ይህንን ህግ በጣም የምንደግፈው ሲሆን በመላው ስቴት ደረጃ ከባልደረቦቻችን ጋር ይህንን አዲስ ህግ ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራንበት እንገኛለን። የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

የ MCPS ሪፖርት

ስለ ትምህርት ቤት ሠላም እና ደህንነት የ MCPS ሪፖርት የማንበብ እድል ካላገኙ፣ እንዲመለከቱት አደፋፍርዎታለሁ። ሪፖርቱን ለማግኘት ይችላሉ እዚህ ። ሪፖርቱ በዲስትሪክታችን ስለ ሠላም እና ደህንነት የአጭር - ጊዜ የተግባር እቅድ እና የረዥም - ጊዜ ስልታዊ እቅድ (ስትራተጂ) ይዘረዝራል።

ስለ ት/ቤቶች ሠላም የሜሪላንድ ክፍት-ቀጥታ መስመር

አጠራጣሪ ነገር ከሰሙ ወይም ከተመለከቱ፣አንድ ነገር ይናገሩ/If you see or hear something, say something በጠቅላላ ተማሪዎች እና ሠራተኞች መደወል እንዳለባቸው ማወቃቸውን ለማረጋገጥ MCPS ዘመቻ እያደረገ ቆይቷል 833-MD-B-Safe (833-632-7233) MCPS ተማሪዎች፣ ሠራተኞች ወይም ትምህርት ቤቶች ላይ ግልጽ የሆነ ወይም የሚያጠራጥር ስጋት/አስፈሪ ሁኔታዎችን በፍጥነት ምርመራ/ክትትል ለማድረግ እና በሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል በስው ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ እና የአካባቢ የህግ አስከባሪ አጋርነት Montgomery County Police and Local Law Enforcement Partnership

የትምህርት ቤት ሠላም/ደህንነት ዲፓርትመንት (DSSS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ፣ ሸሪፍ ጽ/ቤት፣ እና ከማዘጋጃ ቤት የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት እና አጋርነትን አዳብሯል። የትምህርት ቤቶችን ሠላም/ደህንነት የሚመለከቱ ጉዳዮች እና ስጋቶች ላይ በመወያየት የትምህርት ቤቶችን ሠላም/ደህንነት በጋራ ትብብር ለማሻሻል የ DSSS አባላት በቅርቡ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና አዛዦች ቡድን ጋር ስብሰባ አካሄደዋል። በተጨማሪ፣ በት/ቤት ሠላም/ደህንነት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት ለማድረግ DSSS ከተለያዩ የዲስትሪክት ኮማንደሮች ጋር ይገናኛል/ይሰበሰባሉ። የትምህርት ቤት ሠላም/ደህንነት ማስከበርን በሚመለከት የ DSSS አባላት ከማዘጋጃ ቤት የህግ አስከባሪ ተባባሪዎች/አጋሮች ጋር ተመሣሣይ ስብሰባዎችን ያካሄዳሉ።

የእኛ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች በጠቅላላ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሪሶርስ ኦፊሰር ፕሮግራም (High School Resource Officer Program) ላይ ይሣተፋሉ። SRO ፕሮግራምን በሚመለከት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ጋር ውይይቶች በየጊዜው በመደበኛነት ይካሄዳሉ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) በጠቅላላ School Resource Officer (SRO) ሽፋን በሣምንት አምስት ቀን እንዲሆን አስፋፍተናል።

የሜሪላንድ የትምህርት ቤት ሠላም/ደህንነት ማዕከል—ግላዊ ዕቅድ

DSSS ከሜሪላንድ የትምህርት ቤት ሠላም/ደህንነት ማዕከል ጋር በበርካታ ሁኔታዎች ላይ በመተባበር አብሮ እየሠራ ይገኛል። ወደፊት ስለ ሠላም/ደህንነት መሻሻል አስፈላጊ የሚሆኑ ነገሮችን ለይቶ ለመወሰን DSSS የህንፃዎችን ጥናት ፎርም ይጠቀማል። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት በየራሱ ቀኑን ሙሉ ምርጥ የደህንነት ጥበቃ ልምዶችን የሚተገብርበት እቅድ ይኖረዋል። በመጨረሻም፣ ሜይ 2018 ስለተንቀሳቃሽ ክፍሎች መመሪያዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ሁሉም ርእሰመምህራን አግኝተዋል፣ ተንቀሳቃሽ ክፍሎች ላሏቸው ት/ቤቶችም ACS እንዲዳረስ DSSS ሲሠራበት ቆይቷል።

ስለ ትምህርት ቤት ሠላም-ደህንነት የማህበረሰብ ስብሰባዎች

DSSS እና የህዝባዊ ኢንፎርሜሽን ጽ/ቤት (DSSS and the Public Information Office) የትምህርት ቤት ሠላም/ደህንነት ጉዳዮችን፣ የተማሪ የአእምሮ ጤንነት ጉዳይ፣ እና lock down with options አሠራር መመሪያዎችን በሚመለከት ውይይት ለማድረግ አምስት የት/ቤት ማህበረሰብ ስብሰባዎችን ለማካሄድ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ PTAs ካውንስል ጋር እየሠራ ነው። የማህበረሰብ ስብሰባዎች ፌብሩዋሪ ላይ ተጀምረው እስከ ማርች 2019 ይቀጥላል። ቀኖቹን እና ቦታዎችን ለማወቅ፣ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

Montgomery County Public Schools