Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 6, 2019

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ውስጥ የአንዳንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች የጦር መሣሪያ ጥቃት እና እረብሻን በመቃወም ለ ማርች 14 "student walkout" ለማካሄድ እያደራጁ ናቸው። MCPS ተማሪዎቻችንን እናከብራለን እና ለእነርሱ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዲያቀነቅኑ የተማሪዎቻችንን መብቶች እናከብራለን። ስለዚህ ድጋፍ Regulation JFA-RA ላይ በዝርዝር ተገልጿል።ስለ ተማሪ መብቶች እና ኃላፊነቶች/Student Rights and Responsibilities. ተማሪዎች ስለሚያምኑበት ነገር በግልጽ መናገራቸውን እና የተማሪዎችን ማቀንቀን የምንደግፍ እና የምንኮራባቸው ቢሆንም፥  በትምህርት ቤት ሠዓት ት/ቤት እያሉ በሲቪክ ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተማሪዎች ድጋፍ ባለው አይነት እና ሠላማዊ-ጤናማ የትምህርት አካባቢ ላይ እንዲያደርጉት እንፈልጋለን። ከ MCPS መመሪያ በመቀበል፥ ስለ ማርች 14 ተማሪዎች አመለካከታቸውን ሠላማዊ በሆነ ስፍራ ካምፓስ ክልል ውስጥ የሚያደርጉበትን እቅድ የት/ቤት አስተዳዳሪዎች ከተማሪዎች መሪዎች ጋር በቅርበት ይሠራሉ። እነዚህ ሠላማዊ ሠልፎች በራሳቸው ፈቃደኝነት የሚያደርጉት እና በተማሪዎች የሚመራ ነው። ማንም ተማሪ ተሳትፎ እንዲያደርግ/እንድታደርግ አይገደድም/አትገደድም ወይም እንዳይሳተፍ/እንዳትሳተፍ አይከለከልም/አትከለከልም።

አንዳንድ ተማሪዎች ከካምፓስ ወጥተው ሠላማዊ ሰልፉ ላይ ለመሣተፍ ሊወስኑ እንደሚችሉ ተረድቻለሁ። ከትምህርት ቤት ግቢ ለቆ መውጣት ለሌሎች ተማሪዎች የማስተማርን ሥራ እንደሚያደናቅፍ እና ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስጋት እንደሚፈጥር ከዚህ በፊት መግለጼ ይታወሣል። ተማሪዎች በት/ቤት ክልል ግቢ ውስጥ ካልሆኑ በስተቀር የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅና ለማረጋገጥ MCPS ሠራተኞች እና መገልገያዎች አይኖሩትም። የእኔ ጥያቄ ከታቀደው ሠዓት ውጭ ከመማሪያ ክፍል ወይም ከትምህርት ቤት ግቢ ያለፈቃድ ለቀው ከወጡ  ከት/ቤት እንደቀሩ የሚቆጠር መሆኑን ከልጆችዎ ጋር እንዲነጋገሩ ነው። ያለፈቃድ መቅረት ስለሚያስከትለው ውጤት/አሉታዊ ተፅኖ መረጃ/ኢንፎርሜሽን የሚገኘው ስለ መብቶችና ግዴታዎች የተማሪ መመሪያ ላይ እና በ በተማሪ የስነ-ምግባር መመሪያ/ኮድ ላይ ነው። የእርስዎ ልጅ ያለፈቃድ የትምህርት ቤት ግቢ ለቆ መውጣቱን/ለቃ መውጣቷን የት/ቤት አስተዳዳሪዎች ካወቁ፣ ወዲያውኑ ለእርስዎ ያሳውቃሉ።

ስለ ትምህርት ቤት ሠላም-ደህንነት መናገር የሚፈልጉ ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ ለመደገፍ  የትምህርት ቤት ሠራተኞች እና መገልገያዎች/resources አሉ።

ተማሪዎች ሃሳባቸውን እና አመለካከታቸውን የመግለጽ እድል እንዲኖራቸው MCPS ለተማሪዎች ድጋፍ የመስጠት ቁርጠኝነት እንዳለው እባክዎ ይገንዘቡ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር
Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ