travel

የተወደዳችሁ የ MCPS ተማሪዎች፣ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፦

ተማሪዎች እና ሠራተኞች በአካል ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ በወረርሽኝ ወቅት ስለመጓጓዣ አጠቃቀም ሁኔታ ምን እንደሚጠበቅ ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል። ሁላችንም በመተባበር ትምህርት ቤቶቻችን እና ጽ/ቤቶቻችን ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች በሙሉ በተቻለ መጠን ጤናማ አካባቢ እንዲሆኑ የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለብን የጋራ ፍላጎታችን ነው።የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል (CDC) እና የሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት (MDH) አስፈላጊ ያልሆኑ ጎዞዎችን ስለማያበረታቱ፣ ነዋሪዎች አስፈላጊ ወይም ድንገተኛ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ጉዞ ከማድረግ እንዲታቀቡና ለቱሪዝም ወይም ለእረፍት የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያዘገዩ ይጠየቃሉ። በተለይም የ CDC መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል።

ጉዞ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመለከፍ እና ለሌሎች ሰዎችም የማስተላለፍ እድልን ይጨምራል። CDC በዚህ ወቅት ጉዞ ማድረግ እንደሌለብዎት ያሳስባል። ራስዎን እና ሌሎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ከመጓዝ ይቆጠቡ እና እቤትዎ ይቆዩ።

ከሜሪላንድ እና አጎራባች አካባቢዎች (Virginia, West Virginia, Pennsylvania, Delaware and Washington, D.C.) ውጭ መጓዝ የሚፈልጉ ተማሪዎች ከወቅታዊ የ MDH መመሪያዎች ጋር የተጣጣመ ከተመለሱ በኋላ በ 72 ሰዓታት ውስጥ የኮቪድ-19 ምርመራ መውሰድ አለባቸው እና የምርመራ ውጤታቸውን ሲጠባበቁ ራሳቸን ኳራንቲን ማድረግ አለባቸው። እባክዎ ምልክት ለሚታይባቸው ተማሪዎች እና ጉዞ ከማድረጋቸው 90 ቀኖች በፊት ኮቪድ-19 ተይዘው ለነበሩ ተማሪዎች የተለዩ ሁኔታዎች እንዳሉ ይገንዘቡ። እባክዎ ይህንን ከስቴት የተሰጠ መመሪያ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ይህ መመሪያ በስፕሪንግ የእረፍት ጊዜ እና በትምህርት ዓመቱ ተማሪዎች በሚያደርጓቸው ማናቸውም ሌሎች ጉዞዎች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የክትባት ሁኔታ ጭምር ግምት ውስጥ ሳይገባ ተግባራዊ ይሆናል። የፌደራል እና የስቴት የጤና አጠባበቅ መመሪያ ሲቀየር፣ እነዚህ ፕሮቶኮሎች ወቅታዊ ክለሳ የሚደረግባቸው መሆኑን እባክዎ ይገንዘቡ። እነዚህ ለውጦች በሚደረጉበት ጊዜ ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት ቁርጠኞች ነን።

አንዳንድ ቤተሰቦች በስፕሪንግ እረፍት ጊዜ ከአካባቢ ርቀው የመጓዝ እቅድ እንዳላቸው እና ይሄ የደህንነት መመሪያ እቅዳቸውን ሊያደናቅፍ እንደሚችል እንገነዘባለን። የሆነ ሆኖ፥ እንዲህ አይነቱን ጥንቃቄ መውሰድ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በትምህርት ቤቶቻችን እንዳይስፋፋ ለመቀነስ እና ለመገደብ እንደሚረዳ እናምናለን። ስለ መልካም ትብብርዎ እያደነቅን ከካውንቲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ኤልሪክ/County Executive Marc Elrich በቀረበው ጥሪ መሠረት የስፕሪንግ እረፍት ጊዜዎን በቤትዎ እንዲያሳልፉ እናበረታታለን።

ከአክብሮት ሠላምታ ጋር

Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools