English    |    español    |    中文    |    français    |    tiếng Việt    |    한국어    |    አማርኛ  

የወላጅ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፎል ማገገሚያ እቅድ የዳሰሳ ጥናት

መጪውን የትምህርት ዓመት እየተጠባበቅን እና ትምህርት ቤት ምን መምሰል እንዳለበት እና ተማሪዎቻችን እንዴት ትምህርትን እንደሚከታተሉ አስፈላጊ ውሳኔዎችን መስጠት እንዳለብን ሳንዘነጋ፣ ይህንን ተግባራችንን በጥንቃቄ እና በትብብር እየሠራንበት መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን። የተማሪዎቻችን እና የሠራተኞቻችን ጤንነት እና ደህንነት፣ የማያወላዳ፣ የዳበረ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ለተማሪዎቻችን በሙሉ መስጠት የቅድሚያ ትኩረታችን ነው።

በዚህ ሂደት ላይ የእርስዎ አስተዋጽኦ በጣም አስፈላጊ ነው። MCPS ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ ፎል ላይ በማገገሚያ እቅዱ ላይ መካተት ያለባቸውን የማህበረሰብን አስተያየቶች ለማሰባሰብ የተነደፈ የዳሰሳ ጥናት ጀምሯል ። ይህንን የዳሰሳ ጥናት በሚሞሉበት ጊዜ፣ በርካታ ሁኔታዎችን እንደምንመለከት ይኼውም፦ የርቀት ትምህርት መቀጠልን ጨምሮ፣ ፊት-ለ-ፊት በአካል ማስተማር እና አንዳንድ የርቀት ትምህርቶችን በማቀናጀት ጥምር ሞዴል፣ እና አካላዊ መራራቅን እና የተሻሻለ የንጽህና-ሃይጅን መስፈርቶችን በማሟላት በአካል ትምህርት መስጠት የመሣሠሉት አማራጮች ሁሉ ታሳቢ እንደሚደረጉ እባክዎ ግምት ውስጥ ያስገቡ።

የወላጅ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፎል ማገገሚያ እቅድ የዳሰሳ ጥናት