የ 2020 – 2021 የትምህርት ዓመት ካለንደር

ወቅታዊ መረጃ - ዲሴምበር 4/2019

የትምህርት ቦርድ ዲሴምበር 3/2019 ባደረገው ስብሰባ የትምህርት ዓመት 2020-2021 የትምህርት ቤት ካላንደር አጽድቋል። የትምህርት ዓመት የሚጀመረው ሰኞ፣ ኦገስት 31/2020 ሲሆን የዓመቱ ትምህርት የሚጠናቀቅበት ቀን ረቡዕ፣ ጁን 16/2021 ይሆናል። ካላንደሩ የሚያካትተው 182 የትምህርት ቀኖች፣ የስፕሪንግ እረፍት 10 ቀኖችን፣ በእያንዳንዱ ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ አንዳንድ ሙሉ ቀን እቅድ ለማዘጋጀትና ለፕሮፌሽናል ዴቨሎፕመንት፣ እና በሴፕቴምበር ላይ አንድ ኦፐሬሽናል ክሎዠር ቀን ይኖራል።


በስቴት ህግ መሠረት መዘጋት አለበት።

ፎል 2020፣ የሌበር ዴይ የሚውለው ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 7/2020 ነው

በሚከተሉት ቀኖች ትምህርት ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ የስቴት ህግ ይደነግጋል፦

 • ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 3/2020 የምርጫ ቀን-Election Day
 • ሐሙስ፣ ኖቬምበር 26 እና በማግስቱ ዓርብ፣ ኖቬምበር 27/2020 ታንክስጊቪንግ-Thanksgiving and the day after።
 • ሐሙስ፣ ዲሴምበር 24/2019፣ እስከ ዓርብ፣ ጃኑዋሪ 1/2020፦ ከክሪስትመስ ዋዜማ እስከ አዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን
 • ሰኞ፣ ጃኑወሪ 18/2021፦ የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ቀን
 • የምረቃ ስነስርአት በሚካሄድበት ቀን፣ ረቡእ፣ ጃኑዋሪ 20 ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ ይደነግጋል
 • ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 15/2021፦ የፕሬዚደንት ቀን-Presidents' Day
 • ዓርብ፣ ኤፕሪል 2/2021፦ ከኢስተር ቀዳሚው ዓርብ-Friday before Easter
 • ሰኞ፣ ኤፕሪል 5/2021፦ ከኢስተር ቀጥሎ ያለ ሰኞ-Monday after Easter
 • ሰኞ፣ ሜይ 31/2021 የጀግኖች መታሰቢያ ቀን- Memorial Day

ትምህርት ቤቶች ስለሚዘጉበት ሁኔታ የፖሊሲ መመሪያ፦

 • በሆኑ ቀኖች ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ለመወሰን፣ የትምህርት ቦርድ በዩ.ኤስ ህገመንግስት፣ ከፌደራል እና ከስቴት ህግ፣ እንዲሁም ከትምህርት ቦርድ ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆን አለበት። ቦርዱ ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት የትምህርት ፍላጎቶችን ለማርካት እና አስፈላጊ የትምህርት ስርአትን በማዳበር ረገድ ከሃይማኖት ውጪ የሆነ ማረጋገጫ እንዲኖረው ያስፈልጋል። በመጀመሪያ የተሻሻለው ህግ ላይ፣ ኃይማኖትን ለማስፋፋት ትምህርት ቤቶች መዘጋት እንደሌለባቸው ይደነግጋል።
 • የቦርድ ፖሊሲ IDA፣ የትምህርት ቤት ካለንደር/Board Policy IDA, School Year Calendar፣ እንደሚከተለው ይደነግጋል፦ “The Board may determine that schools should be closed at other times in furtherance of other educational interests or operational needs.” ሌሎች ትምህርታዊ ፍላጎቶችን ወይም ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማከናወን በሌሎች ጊዜያት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ቦርዱ ለመወሰን ይችላል። ፖሊሲውን "Policy IDA" እዚህ መመልከት ይቻላል።
 • የትምህርት ሲስተም/ሥርዓት መዘጋት እና የሙያ ማዳበር/Professional Development ቀኖች የሚታቀዱት ሰፊ የሆኑ ትምህርታዊ እና የስራ ክንውን አላማዎችን በማካተት፣ እንዲሁም፦ የሠራተኞችን እና የተማሪዎችን ሞራል በቀናነት ለማበረታታ፣ የተማሪዎችን እና የሠራተኞችን ክትትልና ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ ለማጎልበት፣ ጤናማ የትምህርት ቤት ድባብ ለመፍጠር፣ ስኬታማ የሆነ እና ትርጉም ያለው የማስተማር ሂደት እንዳይደናቀፍ ለመከላከል፣ ለመምህራን እና ለሌሎች ሠራተኞች እቅድ የማዘጋጀት እና የማስተማሪያ በቂ ጊዜ ለመስጠት፣ እንዲሁም ሌሎች ከማስተማር ካለንደር እና የትምህርት ዓመት ጋር ሁኔታዎችን ማጣጣምን ያካተተ ነው።
 • በኃይማኖታዊ ክብረበአል ምክንያት ተማሪ ከቀረ(ች) በሜሪላንድ ህግ መሠረት የተፈቀደ ነው።

ኖቬምበር 21/2019:

የአሠራር ሂደት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ፦ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጽ/ቤቶች እና ዲፓርትመንቶች በርካታ የትምህርት ባለሙያዎች ያሉት ግብረኃይል የትምህርት ካለንደር ማዕቀፍ/instructional calendar framework ያዘጋጃሉ። ይህ ግብረኃይል የተቻለውን ያህል ሁኔታዎችን ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት ቢያንስ ትምህርት ለመስጠት የሚያስፈልገውን የማስተማሪያ ቀኖች እና የክሬዲት ሠዓቶችን የሚያካትት (ቢያንስ 180-ቀኖች)፣ ለመጥፎ የአየር ሁኔታ እና ሌሎችም ድንገተኛ/አስቸኳይ ሁኔታዎች የመጠባበቂያ ቀኖችን፣ ለምዘና/ፈተና መስጫ የተያዙ መርሃግብሮች፣ በስቴት ህግ መሠረት ስለትምህርት ቤት መዘጋት ጋር በማጣጣም ይሠራሉ።

ስለ ካለንደር እና ረቂቅ መርኃግብር ላይ የመጀመሪያ አስተያየቶችን ግብረመልስ ለማግኘትና ግብአቶችን ለማሰባሰብ ሠራተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ስብሰባ ያደርጋሉ። እነዚህ ጅምር ላይ የሚደረጉት ውይይቶች የሚያካትቱት፦ የሠራተኞች ማህበራትን እና ተወካዮቻቸውን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአስተዳዳሪዎች ማህበር እና ርእሰመምህራን የጋራ ትብብር ኮሚቴ፣ የትምህርት ዓመት የፈጠራ ተግባር አስፈጻሚ ቡድን፣ አቀንቃኝ ቡድኖችን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የወላጅና መምህር የትብብር ካውንስል፣ እና የተማሪዎች አማካሪ ካውንስል ሁሉ ያሉበት ነው።

ሠራተኞች ከትምህርት ቦርድ ውይይት በመቀጠል ከማህበረሰብ አስተያየት እንዲሰጥበት የሚተላለፍ ረቂቅ ያዘጋጃሉ። የትምህርት ዓመቱን ካለንደር በሚመለከት በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጁ ሁኔታዎችን የያዘ ሠነድ አስተያየት እንዲሰጥበት እና ግብረመልስ ለማግኘት ለማህበረሰብ ይፋ ይደረጋል። ከዚያም ስለትምህርት ዓመቱ ካለንደር ውይይትና ስለተቀመጡት አቅጣጫዎች ማህበረሰባችን በቂ ግንዛቤ እንዳገኘ ለማረጋገጥ እና ጠንካራ ግንኙነት/ኮሙኒኬሽን እና ማህበረሰብን የመድረስ ጥረት ይደረጋል። የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂዎች የሚያካትቱት፦

 • በድረ-ገጽ ካለንደር ግራፊክስ አማራጭ ግብረመልስ መስጠት።
 • በኢ-ሜይል/E-mail እና Connect-ED አስተያየት እንዲሠጥባቸው ማሠራጨት
 • በድረ-ገጽ ላይ የሚካሄድ ዳሰሳ.
 • ማህበራዊ ሚዲያ;
 • ከውስጥ እና ከውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን ማድረግ፣ እና
 • ተማሪዎችን መድረስ

MCPS እነዚህን ማህበረሰብን በመድረስ የተገኙትን ግብአቶች፣ አስተያየቶችና ግብረመልሶችን ውጤቶችን በማጠናቀር የማጠቃለያ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለትምህርት ቦርድ ሪፖርት ያቀርባል።