የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)

2018-2019 የትምህርት ዓመት

ለማህበረሰብ የቀረበ አመታዊ ሪፖርት

የተከበራችሁ ማህበረሰብ፦

በሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስም፣ የ2019 ዓመታዊ ሪፖርት ለማህበረሰቡ ሳቀርብ ደስታ ይሰማኛል።

የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተልእኮ በትምህርት፣ ችግርን የመፍታት ፈጠራ፣ እና የማህበራዊ ስሜት ሙያ በኮሌጅ እና በሥራ ስኬታማ ለመሆን እና ለወደፊታቸዉ ብልጽግና የሚያስችል እውቀት ለእያንዳንዱ/ዷ ተማሪ ማስጨበጥ ነው። የአካዳሚክ ስኬታማነት በዘር፣ በጎሣ፣ በጾታ፣ በማህበራዊ ኢኮኖሚ አቋም፣ በቋንቋ ብቃት ወይም ስንክልና ምክንያት የማይተነበይ መሆኑን በማረጋገጥ ተማሪዎቻችንን ለማስተማር እንሠራለን። በትምህርት፣ በመሻሻል እርምጃ፣ ስኬታማነት እና እድሎችን አስመልክቶ ስለ ፍትኃዊነት እና ልቀትን በተመለከተ፣ All Means All /ሁሉም ማለት ሁሉንም ማለት ነዉ በሚለው ጽንሰ ሃሳብ እናምናለን።

ተልእኮአችንን ለማሣካት፣ ለተማሪዎቻችን ጠንካራ/የላቀ አካዴሚክ ትምህርት፣ ለብዝሃነት/ለተለያዩ የመማር እድሎች ተደራሽነት እና እድሎችን፣ ከፍተኛ የትምህርት ሪሶርሶችን/መገልገያዎችን፣ ሠላማዊ የትምህርት አካባቢዎችን፣ እና ሌሎች በርካታ ነገሮችን እንሰጣቸዋለን/እናቀርብላቸዋለን። የ2019 ዓመታዊ የማህበረሰብ ሪፖርት በ 2018–2019 የትምህርት ዓመት የተከናወነ ይህን ወሳኝ ሥራ በፍጥነት ለመዳሰስ ያገለግላል።

ተማሪዎች ከፍተኛ የትምህርት አፈፃፀም እና ስኬት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ እና እምቅ ችሎታቸዉን ለማሟላት፣ ለመማር እንዲዘጋጁ የሚያደርጋቸው በ Be Well 365 program/ፕሮግራም ውስጥ የተካተተ፣ የአካላዊ፣ ማህበራዊ፣ እና ስነልቡናዊ ድጋፎች ያስፈልጋቸዋል። MCPS፣ በሁሉም የኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶች የሙሉ ጊዜ የምክር አገልግሎት/ካውንስሊንግ ሠራተኞችን በመጨመር፣ ለትምህርት ቤቶች የስነልቦና/ሳይኮሎጂ አገልግሎቶችን አሻሽሎ በመመደብ፣ እና በጠቅላላ በካውንቲው ውስጥ ለአእምሮ ጤንነት ፕሮግራሞች ተደራሽነትን በማስፋት ዙርያ ኢንቨስት የማድረጉን ተግባር ይቀጥላል። እኛ ዓላማችን ተማሪ እንዲማር ነው፣ ስለሆነም በአካል፣ በአእምሮ እና በመንፈስ ጤንነት ሲኖራቸው ተማሪዎች የተሻለ የአካዳሚ ሥራ መሥራት እንደሚችሉ እናውቃለን።

በዚህ የማህበረሰብ ዘገባ የተካተቱት፡-

 • ከ 2018 – 2019 የትምህርት አመት ትኩረቶች/ፍንጭ ሰጪዎች
 • የMCPS የህዝብ ስብጥር/demographics እይታ በጨረፍታ
 • ስለተማሪ ሥራ አፈጻጸም፣ ምረቃ፣ አገልግሎቶች እና ስለ እኛ የሥራ ግብረኃይል መረጃ/ዳታ
 • All Means All/ሁሉም ማለት ሁሉንም ማለት ነዉ የተሰኘው አቀራረብ ተማሪዎችን ለማገልገል እና እድሎችን ለማግኘት የልዩነት-ክፍተት ለመዝጋት ነው
 • ስለ ስራ ማስኬጃና የካፒታል በጀቶቻችን መረጃ

ከፍተኛ ጥራት ባለው ትምህርት ራዕያችንን፣እና በየቀኑ ለተማሪዎቻችን ተደራሽነት እና ዕድልን የሚፈጥር የተግባር ተልእኮአችንን እዉን ለማድረግ ላገዙን ከ24,000 በላይ መምህራን፣ ኣስተዳዳሪዎች እና ሰራተኞች ምስጋና ይግባችሁ። ለአጋሮቻችን፣ ለወላጆች፣ እና ለማህበረሰቡ በጠቅላላ ስላደረጋችሁት ድጋፍ፣ስለ አስተዋጽኦዋችሁ እና ስለተሳትፎአችሁ አመሰግናለሁ።

በዚህ ሪፖርት ላይ እንደተዘረዘረው በተከናወኑ ነገሮች መሠረት ላይ እየገነባን ለሁሉም ተማሪዎች የተቻለውን ያክል ከፍተኛ/ምርጥ ህዝባዊ ትምህርት መስጠታችንን በማረጋገጥ ጥረታችንን እንቀጥላለን።

ከአክብሮት ጋር፣

Shebra L. Evans, ሼብራ ኤል. ኤቫንስ
ፕሬዚደንት
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ

ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር) Jack R. Smith, Ph.D.,
የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ Superintendent of Schools

ተልዕኮ/ዓላማ

እያንዳንዱ/ዷ ተማሪ በኮሌጅም ሆነ በስራ ስኬታማ እንዲሆን/እንድትሆን የኣካደሚ፣ የፈጠራ ችሎታን የተካነ የችግር ኣፈታት፣ እና የማህበራዊ ስሜት ክህሎቶች ይኖሩታል/ይኖሯታል።

ራዕይ

ለእያንዳንዱና ለማንኛውም ተማሪ እጅግ የላቀውን ህዝባዊ ትምህርት በማቅረብ መማርን እናበረታታለን።

መሰረታዊ/ዋና አላማ

ሁሉም ተማሪዎች ለወደፊት ኑሮአቸው ጠንካራ/የዳበረ ህይወት እንዲኖራቸው/እንዲበለፅጉ ማዘጋጀት።

ዋና ጠቀሜታ/እሴት

ትምህርት፣ ግንኙነት፣ አክብሮት፣ ልቀት፣ ፍትህ።

የ MCPS 2018-2019 የትምህርት ሥርዓት/ምዝገባ

ስለ እኛ ማንነት

ወደ ትምህርት የገቡትን እና ት/ቤቶችን ይመልከቱ

የእኛ የትምህርት ቤት ሥርዓት

በ 2018-2019 ወደ MCPS የገቡ

 በ 2018-2019 የ MCPS ተማሪዎች ስብጥር

2018-19 የተማሪዎች ስብጥር

የ 2018-19 የተማሪዎችን ስብጥር ይመልከቱ

2018-19 የተማሪዎች ስብጥር

በ 2018-2019 የ MCPS ተማሪዎች ስብጥር

የካርድ ገጽታ ሽፋን/Card image cap

አገልግሎቶች

የ 2018-19 አገልግሎቶችን ይመልከቱ

2018-19 አገልግሎቶች

የ 2018-2019 የ MCPS አገልግሎቶች

የካርድ ገጽታ ሽፋን/Card image cap

የእኛ የሥራ ግብረኃይል

የሥራ ግብረኃይልን በዓይነት ይመልከቱ

የእኛ የሥራ ግብረኃይል 2018-19

2018-2019 የ MCPS የሥራ ግብረኃይል

2018-2019 የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ሪፖርት ካርድ

2018-2019 MSDE ሪፖርት ካርድ

የእኛን ሪፖርት ካርድ ይመልከቱ

MCPS በ 2017 በአዲስ ሱፐርኢንተንደንት ጃክ አር. ስሚዝ/superintendent, Jack R. Smith አመራር አዲስ ስልታዊ የትኩረት መርሃግብሮችን መተግበር ጀምሯል። እነዚህ ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫዎች ለበጀት ዓመት 2018 የ MCPS ስልታዊ እቅድ እንዲሆኑ ተገንብተዋል።

በተጨማሪ ይወቁ

ለተማሪ ስኬታማነት MCPS All Means All/ሁሉም ማለት ሁሉንም ማለት ነዉ ለሚለዉ አቀራረብ ቁርጠኛ ነዉ። በርካታ ተማሪዎቻችን በከፍተኛ ደረጃዎች ስኬታማ ቢሆኑም፣ ያላቸውን እምቅ አቅም ለመጠቀም የሚያስችላቸው ተደራሽነት፣እድሎች እና መገልገያዎችን (resources)የማግኘት ሁሉም እድሉ አልነበራቸውም። በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ፣ እና በሁሉም ት/ቤቶቻችን፣ ለሁሉም ተማሪዎች በእድል እና በስኬት ረገድ ያለውን ክፍተቶች በመዝጋት በተማሪ ውጤቶች ላይ ያለዉን ልዩነቶች/የአለመመጣጠን ለመፍታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቁርጠኝነት ይሰራል። የ MCPS All In/ሁሉንም ማቀፍ፦ የፍትሃዊነት እና የስኬት ማዕቀፍ የሁሉንም ተማሪዎች ስኬት ለማረጋገጥ ዓላማ ፣ መንገድ እና ዕቅድ ይሰጣል/ያቀርባል።

ይበልጥ ለማወቅ ስለ ፍትሃዊነት እና የስኬት ማዕቀፍ ባለ አንድ ገጽ በራሪ ወረቀት/ፍላየር ያንብቡ


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (Montgomery County Public Schools) ተልእኮ እያንዳንዱ ተማሪ የእርሱ ወይም የእርሷ የበፊት ማንነት ሳይገድበው/ሳይገድባት በኮሌጅ፣ በሙያ ሥራ እና በማህበረሰብ ዘንድ ስኬታማ ለመሆን፣ በአካደሚክ ችግርን የመፍታት የፈጠራ ችሎታ እና ማህበራዊና ስሜታዊ ክህሎቶች ማዳበርን ማረጋገጥ ነው። በርካታ ተማሪዎቻችን በከፍተኛ ደረጃዎች ስኬታማ ቢሆኑም፣ ያላቸውን እምቅ አቅም ለመጠቀም የሚያስችላቸው እድሎች፣ድጋፍ እና መገልገያዎችን (resources) የማግኘት ሁሉም እድሉ አልነበራቸውም። በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ፣ እና በሁሉም ት/ቤቶቻችን፣ ለሁሉም ተማሪዎች በእድል እና በስኬት ረገድ ያለውን ክፍተቶች በመዝጋት በተማሪ ውጤቶች ላይ ያለዉን ልዩነቶች/የአለመመጣጠን ለመፍታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቁርጠኝነት ይሰራል።

እድሎችን ማስፋፋት

የመጠቀሚያ መንገድ/መዳረሻ ማግኘት ስኬትን/ክንዋኔን ይቀድማል። ለሁሉም ተማሪዎች ትምህርት ለማበልፀግ በተረጋገጡ በተለያዩ ዘርፎች/ፕሮግራሞች ተደራሽነትን በማስፋት የማስተማር ሠአት ተጨምሮ ትምህርትን ለማቅረብ እና ለማስፋፋት MCPS ቁርጠኛ የሆነው ለዚህ ነው። MCPS በሦስት ቁልፍ ዙርያዎች ላይ እድሎችን አስፍቷል፦

የተስፋፉ የቋንቋ እና ማንበብና መጻፍ ማበልፀጊያ እድሎች

ከመደበኛው የቋንቋ ጥልቀት/ኢመርዥን ፕሮግራሞች በተጨማሪ፣ በአሁኑ ወቅት MCPS ሁለት-አቅጣጫ የቋንቋ ጥልቀት ፕሮግራሞች (immersion programs) በአካባቢ ት/ቤት አሉት። እነዚህ ተማሪዎች 50% ትምህርታቸውን የሚያገኙት በእንግሊዝኛ ሲሆን 50% የሚማሩት በሌላ የትኩረት ቋንቋ ነው። MCPS በተጨማሪም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን ለማዳበር በተጨማሪ የመማሪያ ቦታ እና ሁሉአቀፍ ማጣራት እና ተጨማሪ የአካባቢ ትምህርት ቤቶችን በማዳበር ሁሉም ተማሪዎች፣ በዚፕኮድ ሳይገደቡ በፕሮግራሙ እንዲሳተፉ ለማስቻል ነው።

የተራዘመ የትምህርት ጊዜ

በአብዛኛው ድህነት ባጠቃቸው ቤተሰብ ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ የሚያደርገውን የሠመር ወቅት ትምህርት ማቋረጥን ለመጋፈጥ/ለመዋጋት፣ MCPS አሁን ባሉት የሰመር ትምህርት ፕሮግራሞች (ELO SAIL፣ ELO STEP፣ እና BELL program) ተደራሽነትን እና የመማር ጊዜ አራዝሟል/አስፋፍቷል፣ እና በጁላይ 2019፣ በሁለት የTitle I የኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶች (Roscoe R. Nix እና Arcola) MCPS የትምህርት ዓመቱን በ30 ቀኖች ያራዝማል።

ለትምህርት በቅድሚያ ተጋላጭ መሆን

MCPS የ Pre-K ክፍሎችን እየጨመረ እና ወደ የሙሉ ቀን ትምህርት ትግባሬዎች በጠቅላላ በካውንቲው ውስጥ እያስፋፋ ይገኛል፤ ሳይንስ፣ ምህንድስና፣ ቴክኖሎጂ እና ሒሳብ/Science, Engineering, Technology and Math (STEM) በኤለመንተሪ ዋና ከሪኩለም ላይ በማካተት፤ እና በድህነት የተጠቁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ተማሪዎች ባሉባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ የስነጥበብ ትምርትን በማስፋፋት ላይ ይገኛል።

የታመቀ ችሎታን ማውጣት

ተማሪዎች ትምህርት ቤት አጠናቀዉ ሲወጡ ለወደፊታቸዉ ትርጉም ያለው/አዘል አማራጮች መያዛቸዉን ማረጋገጥ የእኛ ኃላፊነት ነዉ። እነዚህ አማራጮች ክሬዲት-የሚያስገኙላቸው የኮሌጅ ኮርሶች፣ ትርጉም ያለው ሥራ ለመጀመር ተፈላጊ የሆኑ የሙያ እውቀት እና የሙያ ፈቃዶችን መያዝ፣ ወይም ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎቻችን ሁለቱንም ሊሆን ይችላል።

ጥብቅ የሆነ የኮርስ ሥራ እና የኮሌጅ ምዘና መሰናክሎችን መስበር

ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ተማሪዎች ጥረትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ትምህርት ሲጋፈጡት እና ድጋፍ ሲያገኙ በድል ይወጣሉ። በተለይም ውክልና ያላገኙ ተማሪ ቡድኖች ላይ በማተኮር ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ MCPS ከፍ ያለ ምደባ እና ኢንተርናሽናል ባሰሎሪኤት/International Baccalaureate ኮርሶች ተደራሽነትን አስፋፍቷል። በተጨማሪም፣ ሁሉም የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የሚኖራቸውን እቅድ ለመደገፍ ለ(SAT፣ ACT ወይም Career Certificates) ምዘናዎች/ፈተናዎች ተደራሽነት ይኖራቸዋል።

ሙያ/ሥራ እና ማህበረሰብ ዝግጅት

የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሥራ-ዝግጁነት የሚሰጡ ኮርሶችን ጥራት አሻሽሏል እናም አስፋፍቷል። ፕሮግራሞቹ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ከኢንጅነሪንግ እስከ አቪየሽን፣ ፋይናንስ እና የማስተማር ሥራ ይለያያሉ። አንዳንድ ፕሮግራሞች ተማሪዎቹ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚመረቁበት ጊዜ ምንም ወጪ ሳያስከትልባቸው ወይም በቅናሽ ወጪ የሁለት-ዓመት አሶሽየት ዲግሪ ይሰጣሉ፡፡ MCPS 21 ዓመት እድሜ ሳይሞላቸው በፊት የመመረቂያ መስፈርቶችን ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች እና በመደበኛ ትምህርቶች ውስንነት ያለባቸው ወይም ያቋረጡ ተማሪዎችን ለማገልገል Career Readiness Education Academy እያስፋፋ ነው።

ለተማሪዎች ድጋፍ መስጠት

የአናሳ ተማሪዎች ስኮላርስ/Minority Scholars እና ለኮሌጅ ልሂቅነት እና ውጤታማነትን ማሳካት (Achieving Collegiate Excellence and Success) በመሳሰሉት ፕሮግራሞች ላይ ኢንቨስትመንታችን በተለምዶ አነስተኛ ውክልና ካላቸው የሚመጡ ተማሪዎችን ተጨማሪ የማስተማር እገዛ በመስጠት፣ ክትትል በማድረግ እና የባለቤትነት ስሜትን እንዲያዳብሩ ይረዳል።

ዓላማ ላይ የተመረኮዘ የማስተማር ስልቶች

የተዋጣለት የተማሪ ትምህርት ዓላማ ያደረገ እና በእውቀት የሚሰጥ ማስተማርን ይጠይቃል። ይህም ከመደበኛ የፈተና/ቴስት አጠቃላይ ድምር ውጤት ዳታ/መረጃ አሻግሮ ማየትን እና እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ይፈልጋል፦

 • እያንዳንዱ(ዷ) ተማሪ እየተማረ/ች ነው?
 • በቂ ትምህርት/ዕውቀት እየቀሰሙ ናቸው?
 • እንዴት እናውቃለን?
 • እየተማሩ ካልሆነስ፣ ለምን?
 • ስለዚህ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
መረጃው ባትሪ ነዉ

ዳታ/መረጃ ተማሪ እንዴት እየተማረ(ች) እንደሆነ የትምህርት ባለሙያዎች የበለጠ እንዲገነዘቡ ሊጠቅም ይችላል። ይህ የቱ ጋ ግስጋሴ እያደረጉ እንደሆነ እና የትኛው ጋ ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልግ እንደሆነ ለመወሰን የተማሪዎችን ትምህርት ከብዙ መስፈርቶች አኳያ መመልከት ያስፈልጋል። እነዚህ መመዘኛዎች የሚያካትቱት ኩዊዞችን፣ ፈተናዎችን እና የክፍል ደረጃን የሚመጥን ድርሰት መጻፍ፣ እንዲሁም ደረጃ የሚመጥን በስቴት ደረጃ የሚሰጥ የቴስት ዳታ/መረጃን ነው። አዳዲስ፣ ጠንካራ የመረጃ/ዳታ መሣሪያዎችን፣ በመጠቀም የትምህርት ባለሙያዎች የተማሪዎችን ሥራ ለመቆጣጠር እና ድጋፎችን ለመስጠት ወይም የተማሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ተፈታታኝ ትምህርቶችን ለማቅረብ ያስችላቸዋል።

በብቃት የማስተማር ባህል ያላቸው

በተቻለ መጠን ውጤታማ ለመሆን፣ የሰው አዕምሮ መረጃ/ኢንፎርሜሽን ለማዋሃድ/ለማብላላት አቋራጮችን ይወስዳል። ያለመታደል ይሆንና፣ እነዚህ አቋራጮች አንዳንድ ጊዜ ያለአስፈላጊ የሆነ ወደማድላት/ማዘንበል የመፍጠር እና ወደ ጅምላ ፍረጃ ያመራል። ለትምህርት ባለሙያዎች፣ ከተማሪ መጠበቅ ያለበት ከችሎታ ይልቅ በዘር፣ በጎሣ፣ ወይም በፆታ፣ ወደሚለው አስተሳሰብ ያመራል። ይህንን ውስጠታዋቂ/ጥርጥር የሌለው አድልዎ ለመፋለም እና መምህራን ከየትኛውም ወገን ተማሪዎች ጋር የተሻለ ግንኙነት እንዲኖራቸው፣ MCPS የግዴታ መወሰድ ያለበትን ባህልን የመረዳት የብቃት ስልጠና ለሁሉም መምህራን አዘጋጅቷል።

ስለ እኛ ተማሪ ማንፀባረቅ

በማደግ ላይ የሚገኘው የእኛ ብዝሃነት ስብጥር ተማሪዎች አካል እንደእነርሱ ብዝሃነት ስብጥር ከፍተኛ-ምርጥ መምህራን ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ፣ ብዝሃነት ስብጥር ያላቸውን አመልካቾች በእኛ ሲስተም ውስጥ በመምህርነት እንዲሠሩ MCPS ለቅጥር/ምልመላ ትኩረት በመስጠት እየሠራበት ይገኛል። በተጨማሪም በርካታ ስብጥር ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎችን ወደ ሰርቲፋይድ መምህርነት የሚያድጉበትን መንገዶች እየፈጠርን ነው።

ለቤተሰቦቻችን ድጋፍ መስጠት

በበርካታ ቋንቋ ተናጋሪ የወላጅ ማህበረሰብ አስተባባሪዎቻችን እና የተማሪ ፐርሶኔል ሠራተኞቻችን አማካይነት ለቤተሰቦች ድጋፍ ለመስጠት እና ጠቃሚ የሆኑ መገልገያዎችን/resources በመለየት ረገድ MCPS በቁርጠኝነት ይሠራል። እንግሊዝኛ ዋነኛ ቋንቋቸው ላልሆነ ቤተሰቦች ወቅታዊ ትርጉም እና የማስተርጎም አገልግሎት ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ በቋንቋ አገልግሎቶች ሥራ ላይም ኢንቨስት እያደረግን ነው።

MCPS ተልእኮውን ለመወጣት እና ለትምህርት ቤቶቹ ባጀት እንዲያሟላ ለማስቻል የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ/Montgomery County Board of Education ከበርካታ ኃላፊነቶቹ መካከል፣ ፖሊሲዎችን የማዘጋጀት እና የመገምገም ወሣኝ ኃላፊነት አለበት። ይህንን ለማድረግ፣ ቦርዱ በመቶዎች እና በሺዎች ከሚቆጠሩ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ጋር በሠፈር - ክልል ስብሰባዎች/cluster meetings፣ ስለ በጀት ውይይት ሸንጎዎች፣ የት/ቤት ጉብኝቶች እና ሌሎችም በቀጥታ ግንኙነቶችን ያከናውናል። በተጨማሪ ይወቁ

በ2018-2019 የትምህርት ዓመት ወቅት፣ በአጠቃላይ 25 የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ህጎች ተሻሽለዋል፣ተከልሰዋል ወይም ተሽረዋል። አንዳንዶቹ ክለሳና ማሻሻያ የተደረገባቸው ቴክኒካዊ የሆኑ ወይም ጎልተዉ የሚታዩ አይደሉም።

የትምህርት ቦርዱ አንድ አዲስ ፖሊሲ በሥራ ላይ እንዲዉል አድርጓል፣ ሰባት ፖሊሲዎችን አሻሽሏል፣ 14 ደንቦች ላይ ክለሳ አድርጓል፣ ሁለት ፖሊሲዎች እና አንድ ደንብ እንዲሰረዙ አድርጓል።


የቦርድ አባላት

የ MCPS የትምህርት ቦርድ

አዲስ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች
የተሻሻሉ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች
 • BBB ፣ Ethics /ስነምግባር
 • BFA ፣ Policysetting/የፖሊስ ዝግጅት/አደረጃጀት
 • BLB፣ Rules of Procedure in Appeals and Hearings/በይግባኝ እና በችሎቶች ውስጥ የአሠራር/ቅደምተከተል ደንብ
 • FAA ፣ Educational Facilities Planning/የትምህርታዊ ተቋማት እቅድ
 • IGK ፣ Career Readiness/ለሥራ ዝግጁነት
 • JEA፣ Residency, Tuition, and Enrollment/ ነዋሪነት፣ የትምህርት ክፊያ፣ እና ምዝገባ
 • KBA ፣ Policy on Public Information/ስለ ህዝባዊ መረጃ/ኢንፎርሜሽን ፖሊሲ
ክለሳ የተደረገባቸው የ MCPS ደንቦች
 • COB-RA ፣ Incident Reporting/የተከሰተ ነገርን ሪፖርት ስለማድረግ
 • EEB-RA ፣ Operation and Care of MCPS Buses /የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አውቶቡሶችን በጥንቃቄ ማሽከርከር
 • FAA-RA፣ Educational Facilities Planning/የትምህርታዊ ተቋማት እቅድ
 • IGP-RA ፣ Comprehensive Health Education Instructional Program/የአጠቃላይ ጤና ትምህርት ፕሮግራም
 • IOE-RA ፣ Guidelines for the Continuing Education of Pregnant and Parenting Students/ስለ ነፍሰጡር እና ወላጅ የሆኑ ተማሪዎች ትምህርት የመቀጠል መመሪያዎች
 • IOI-RA፣ ለተለዋጭ/አማራጭ ፕሮግራሞች የምደባ ሂደት/Placement Procedures for Alternative Programs
 • JEA-RB ፣ Enrollment of Students/የተማሪዎች ምዝገባ
 • JEA-RE፣ Tuition-based Enrollment/ክፊያን መሰረት ያደረገ ምዝገባ
 • JEE-RA፣ Student Transfers and Administrative Placements/የተማሪ መዛወር እና አስተዳደራዊ ምደባዎች
 • JFA-RA፣ Student Rights and Responsibilities/የተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች
 • JGA-RB፣ Suspension and Expulsion/እገዳ እና ስንብት
 • JPA-RB፣ Safety and Screening Programs: Lead, Hearing, and Vision /ደህንነት እና የምርመራ/ማጣራት ፕሮግራሞች፦ ሊድ፣ መስማት፣ እና እይታ
 • JPG-RA፣ Wellness: Physical and Nutritional Health/ጤናማነት ፦ አካላዊና የአመጋገብ ጤንነት
 • KLA-RA ፣ Responding to Inquiries and Complaints from the Public /ከህዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች ምላሽ ስለመስጠት
የተሻሩ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች
 • FKB ፣ Sustaining and Modernizing Montgomery County Public Schools (MCPS) Facilities / የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መገልገያ ተቋማትን መጠበቅ እና ዘመናዊ ማድረግ
 • KBB ፣ Release of Data /መረጃ/ኢንፎርሜሽን መልቀቅ/ማስተላለፍ
የተሻሩ የ MCPS ደንቦች
 • JED-RA ፣ Residency and Tuition/ነዋሪነት እና የትምህርት ክፊያ

በ 2018-2019 ተሻሽለው በሥራ ላይ የዋሉ ደንቦች/መመሪያዎች

ማሻሻል
ማስተማር እና መማር

 • ተማሪዎች በጠንካራ የኮርስ ስራ፣ ፕሮግራሞች፣ እና የSTEM መስኮችን ጨምሮ ከስርኣተ ትምህርት ጋር በተያያዙ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ እድሎችን መጨመር
 • የተማሪዎችን ውጤቶችና እድሎች ለመጨመር በሁሉም የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች በግኝት-ያተኮሩ ከትምህርት ጊዜ-ውጭ እንቅስቃሴዎች/extracurricular ፕሮግራሞችን ማስፋፋት
 • የቤት ዉስጥ ት/ቤት ሞዴል የልዩ ትምህርት ፕሮግራሞችን ማስፋፋት
 • በጠንካራ ቁሳቁሶች፣ ትኩረት ያለው ድጋፍ፣ እና ለፕሮግራም ዝግጅት ኣቅርቦቶች ኣማካይነት ውጤታማ የሂሳብ ትምህርትን ማረጋገጥ
ስልታዊ ግቦች

ትኩረት ማድረግ
መማር፣ ተጠያቂነት፣ እና ውጤቶች

 • እኩል ዕድል የሚሰጡ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር መጨመር
 • አማራጭ ፕሮግራሞችን ፣ ለምረቃ የመስመር ላይ መንገዶች/መሻገሪያዎች እና ከጥሎ መዉጣት ማገገሚያን እንደገና መንደፍ/ማቀድ
 • ለበለጸገ እና ለተፋጠነ ትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት
 • በ Cybersecurity፣ Public Safety/EMT/Firefighter Academy፣ Agricultural Science and Aviation ሳይበርሰኪዩሪቲ፣የማህበረሰብ ደህንነት/EMT/የእሳት አደጋ መከላከል አካዳሚ፣ በእርሻ ሳይንስ እና በአቪዬሽን የሥራ እድል የሚስፋፋባቸውን መንገዶች መጨመር
 • ለሜሪላንድ Seal of Biliteracy/ከእንግሊዘኛ ዉጪ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋ በብቃት ላጠኑ ተማሪዎች መዳረሻ ማስፋት
 • በሁለት የአንደኛ ደረጃ/ኤለመንተሪ ት/ቤቶች ከጁላይ 2019 ጀምሮ የተራዘመ ዓመት ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ
 • የመልሶ ማገገሚያ ትምህርት ፕሮግራም/መርሐ ግብር መጀመር
 • የፍትሓዊ ተኃድሶ ተነሳሽነትን ማስፋፋት
 • የስነ-ጥበብ ተነሣሽነት ፕሮግራምን በጌትስበርግ እና በጀርመንታዎን አካባቢዎች ላሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማስፋፋት
 • በ Thomas Edison H.S. of Technology ከ Junior Achievement ጋር በሚደረግ ትብብር አማካይነት የፋይናንስ ፓርክ ፕሮግራም ለሁለም የ MCPS ሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተግባራዊ ማድረግ
 • ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የ BELL (Building Educated Leaders for Life/ ምሁራን መሪዎችን ለዘለቄታው መገንባት) ሰመር ፕሮግራምን ማስፋፋት
 • በሁለት ተጨማሪ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሁለትዮሽ የመድብለ ቋንቋ ኢመርሸን ፕሮግራም ማስፋፋት
 • ለሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቋንቋ መርሃግብሮች የሚቀርቡባቸውን መንገዶች መፈለግ/ማሰስ
 • የ Pre-K /መዋዕለህጻናት ፕሮግራም ማስፋፋት
 • በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስን የእንግሊዝኛ ብቃት ላላቸው (LEP) ተማሪዎች አካዳሚያዊ ጉዳዮችን ለመቅረፍ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ መመረቅ የሚያመራ ዕቅድን ማዘጋጀት እና መተግበር።
ስለ ተማሪ ግስጋሴ መረጃ ከ Dashboards መቃኘት

ትኩረት በሠብአዊ እሴት ላይ

 • በዲስትሪክት እና በትምህርት ቤት ደረጃ በ MCPS ዉስጥ ለሥራ ምለመላ፣ ቅጥር እና ሠራተኛ ይዞ የመቆየት ጥረትን መቀጠልና ማስፋት
 • የድጋፍ ባለሙያዎች የመማሪያ ክፍል መምህራን እንዲሆኑ መንገዶችን/መሸጋገሪያዎችን መጨመር እና ማሻሻል
 • በ MCPS ውስጥ በሌሎች የሙያ መስኮች ውስጥ ላሉት ሌሎች የድጋፍ ባለሙያዎች የእድገት እድሎችን ማቅረብ

በሰብኣዊ እሴት ላይ ማተኮር

የ MCPS የሥራ ግብረኃይል፦ የስብጥር ገጽታ/መገለጫ

የ 2016 በጀት ዓመት የ2017 በጀት ዓመት የ2018 በጀት ዓመት የ2019 በጀት ዓመት
መቶኛ/ፐርሰንት መቶኛ/ፐርሰንት መቶኛ/ፐርሰንት መቶኛ/ፐርሰንት
ሴት 73.90% 73.80% 73.80% 73.7%
ወንድ 26.10% 26.20% 26.20% 26.3%
ድምር 100.00% 100.00% 100.00% 100.00%
የ 2016 የበጀት ዓመት የ2017 የበጀት ዓመት የ2018 የበጀት ዓመት የ2019 የበጀት ዓመት
አሜሪካዊ ኢንዲያን ወይም አላስካዊ 0.2% 0.2% 0.2% 0.2%
እሲያዊ 7.9% 8.0% 8.2% 8.5%
ጥቁር ወይም አፍሪካዊ አሜሪካዊ 17.7% 18.0% 18.0% 18.3%
የሰፓኒሽ ተወላጅ 11.3% 12.0% 12.5% 13.2%
የሐዋይ ተወላጅ ወይም ከፓስፊክ ደሴት 0.1% 0.1% 0.1% 0.1%
ሁለት ወይም ከዚያ በላይ 1.3% 1.4% 1.4% 1.4%
ነጭ 61.5% 60.5% 59.6% 58.2%
ድምር 100.00% 100.00% 100.00% 100.00%
የ 2016 የበጀት ዓመት የ2017 የበጀት ዓመት የ2018 የበጀት ዓመት የ2019 የበጀት ዓመት
ከ 20 በታች 0.00% 0.00% 0.00% 0.00%
20 - 29 ዓመት 12.00% 12.60% 12.70% 12.50%
30 - 39 ዓመት 21.40% 21.90% 22.10% 22.10%
40 - 49 ዓመት 24.90% 24.80% 25.00% 25.40%
50 - 59 ዓመት 26.70% 26.40% 26.00% 25.60%
60+ አመት 14.90% 14.40% 14.20% 14.40%
ድምር 100.0% 100.0% 100.0% 100.0%

1. መረጃው ቋሚ ሠራተኞችን ቁጥር በነፍስወከፍ ያንፀባርቃል። ጊዜያዊ እና ተተኪ ሠራተኞች አልተጨመሩም፡፡

2. መረጃው የተሰበሰበው ኦክቶበር 15 ነው።

በሰብኣዊ እሴት ላይ ማተኮር

የ MCPS የሥራ ግብረኃይል፦ የመምህራን በስራ ላይ መቆየት/ዘላቂነት

(የበጀት ዓመትን ተመርኩዞ የአዲስ ቅጥር መረጃ)

የበጀት ኣመት የተቀጠሩ መምህራን ቁጥር የተሰናበቱ ጠቅላላ ቁጥር
የ2008 በጀት ዓመት የ2009 በጀት ዓመት የ2010 በጀት ዓመት የ2011 በጀት ዓመት የ2012 በጀት ዓመት የ2013 በጀት ዓመት የ2014 በጀት ዓመት የ2015 በጀት ዓመት የ2016 በጀት ዓመት የ2017 የበጀት ዓመት የ2018 በጀት ዓመት የ2019 በጀት ዓመት
# % # % # % # % # % # % # % # % # % # % # % # % # %
FY2008 1,236 102 8.30% 63 5.10% 43 3.50% 47 3.80% 38 3.10% 20 1.60% 20 1.60% 43 3.50% 19 1.50% 22 1.80% 16 1.30% 9 0.7% 442 35.8%
FY2009 777     59 7.60% 43 5.50% 37 4.80% 27 3.50% 28 3.60% 27 3.50% 27 3.50% 13 1.70% 16 2.10% 11 1.40% 12 1.5% 300 38.6%
FY2010 639         31 4.90% 42 6.60% 35 5.50% 24 3.80% 22 3.40% 19 3.00% 16 2.50% 15 2.30% 15 2.30% 18 2.8% 237 37.1%
FY2011 492             30 6.10% 23 4.70% 23 4.70% 11 2.20% 39 7.90% 22 4.50% 20 4.10% 14 2.80% 9 1.8% 191 38.8%
FY2012 881                 61 6.90% 44 5.00% 39 4.40% 62 7.00% 32 3.60% 27 3.10% 22 2.50% 21 2.4% 308 35.00%
FY2013 720                     76 10.60% 57 7.90% 71 9.90% 44 6.10% 35 4.90% 38 5.30% 19 2.6% 340 47.2%
FY2014 978                         79 8.10% 79 8.10% 48 4.90% 45 4.60% 35 3.60% 33 3.4% 319 32.6%
FY2015 972                             32 3.30% 62 6.40% 59 6.10% 40 4.10% 53 5.5% 246 25.3%
FY2016 720                                 54 7.50% 60 8.30% 41 5.70% 30 4.2% 185 25.7%
FY2017 1,349                                     148 11.00% 84 6.20% 61 4.5% 293 21.7%
FY2018 1,074                                         112 10.40% 85 7.9% 197 18.3%
FY2019 1,009                                             112 11.1% 112 11.1%
Totals 10,847                                                 3,170 29.2%

ይህ ሠንጠረዥ የሚያሳየው በባጀት ዓመቱ ውስጥ የተቀጠሩትን የመምህራን ብዛት እና (በመስመር ትይዩ ሲያነቡት) በቀጣይ የባጀት ዓመት ከሥራ የለቀቁ/የተሰናበቱትን ብዛት ያመለክታል።

2. ይህ ሠንጠረዥ በጡረታ የተገለሉትን አይጨምርም።

ትኩረት የተደረገዉ
የማህበረሰብ ትብብር እና ተሳትፎ

 • በ KID ሙዚየም ትብብር መቀጠል
 • ከማህበረሰቡ ጋር ሥራ-ተኮር አካባቢዎች/መስኮች ላይ ትብብሮችን መመስረት
 • በተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወደ ኮሌጅ የሚያመራ/ዱካ ፕሮግራም ማስፋፋት
 • በተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የኮሌጅ ልቀት እና ስኬት ግኝት (ACES) ፕሮግራምን ማስፋፋት
 • ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ የመካከለኛ እና የቅድሚያ ኮሌጅ ፕሮግራምን ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ ጋር በአጋርነት ማስፋፋት
በተጨማሪ ይወቁ

በማህበረሰብ ሽርክናዎችና ተሳትፎ ትኩረት ማድረግ

የዋናው ጽ/ቤት አጋሮች

144 አጋር ድርጅቶች/116 ፕሮግራሞች
የድርጅቱ ዓይነት ድምር %
ህብረት  12 8.3
ቢዝነስ/ኮርፖሬሽን ( Business/Corporation) 28 19.4
የትምህርት ተቋም 16 11.1
ምስረታ 5 3.5
የመንግስት አስተዳደር 36 25.0
አትራፊ ያልሆነ ድርጅት 46 31.9
ማህበር 1 0.7
ድምር 144 99.998

የ 2018-2019 ዓመታዊ ሪፖርት የወላጅ አካደሚ መረጃ/ዳታ

አጠቃላይ የአውደጥናቶች ቁጥር፦85
የተሳተፉ ወላጆች/ሞግዚቶች አጠቃላይ ቁጥር፡-1,585
የተመዘገቡ ወላጆች/ሞግዚቶች አጠቃላይ ቁጥር፡-2,212
ከተመዘገቡት ውስጥ የተሳተፉ ወላጆች በመቶኛ/ፐርሰንቴጅ፦71%
የተሳታፊዎች አማካይ ቁጥር፦18.6
የማስተርጎም አገልግሎት የተጠቀሙ ወላጆች/ሞግዚቶች ቁጥር፦96
በሌሎች ቋንቋዎች የተሰጡ አውደጥናቶች ብዛት፦21
እንክብካቤ የተደረገላቸው ህፃናት ብዛት፦264
ግምገማ ያጠናቀቁ ወላጆች/ሞግዚቶች ብዛት፡-1,026

የወላጅ አስተያየት

በእያንዳንዱ አውደጥናት መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎቹ ግምገማ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ። የተሰጡት ግብረመልሶች እና አስተያየቶች የአውደጥናት ርእሶችን እና ሌሎች የፕሮግራም ማሻሻያዎችን ለመወሰን ይጠቅማሉ።

ከዚህ በታች ያሉት ቁጥሮች በጣም እስማማለሁ ወይም እስማማለሁ ብለው የመለሱትን ወላጆች ብዛት ያንፀባርቃል።

ይህንን አውደጥናት በመከታተል ጊዜዬን በቁምነገር ተጠቅሜበታለሁ።99.6%
የተማርኩትን ወስጄ ከልጄ ጋር እቤት ውስጥ እጠቀምበታለሁ፡፡99.2%
አቅራቢው/ዋ ግልፅ ነበር/ረች እና መረጃው/ኢንፎርሜሽኑ ለመረዳት ቀላል ነበር።99.3%

ወላጅ/ሞግዚት ግብረመልስ
ለአማራጭ ክፍል/ሰክሽን የማህበረሰብ ስብጥር ገጽታ ዝርዝር

በወላጅ አውደጥናቶች የተሳተፉ ወላጆች እና ሞግዚቶችን የብዝሃነት ገጽታ ማወቅ እንፈልጋለን። ከዚህ በታች ያሉት ቁጥሮች በግምገማው ቅጽ ላይ በፍላጎታቸው የሚሞሉት ክፍል ላይ የሞሉትን ወላጆች/ሞግዚቶች ጾታ፣ ዘር እና ጎሣ ያመለክታል።

ሴት፦75%
ወንድ፦25%

ዘር/ጎሣ

ህንዳዊ አሜሪካዊ፦<1%
እሲያዊ:28.7%
ጥቁር ወይ አፍሪካ-አሜሪካዊ:-16.9%
ሂስፓኒክ/ላቲኖ፦17.4%
ትውልደ ሃዋይ /ተወላጅ ወይም ሌላ የፓሲፊክ ደሴት ተወላጅ:-<1%
ነጭ:-33.8%
ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ዘሮች፦4.2%

ትኩረት የተደረገዉ
የላቀ የሥራ ክንውን

 • በበጀት፣በፋይናንስ/ገንዘብ እና በሰብአዊ ሪሶርሶች ረገድ የላቀ አፈፃፀም እንዲኖር የስርዓቶች ደረጃ ማሳደግ፣አቅጣጫ ማስያዝ/ማቀናጀት እና ማሻሻል
 • በት/ቤቶች ውስጥ ለንግድ/ቢዝነስ ሥራዎች ማሻሻያ ተነሳሽነትን ተግባራዊ ማድረግ
 • ለት/ቤቶች የማዕከላዊ ጽ/ቤት ድጋፍን መልሶ ማደራጀት/ማዋቀር
በተጨማሪ ይወቁ

በግብረታዊ ልቀት ላይ ማተኮር

አውቶቡስ በሠዓቱ የደረሰበት በመቶኛ/ፐርሰንት

የ16 በጀት ዓመት94%
የ17 በጀት ዓመት94%
የ18 በጀት ዓመት96%
የ19 በጀት ዓመት97%

ለመከላከል የሚቻል የአውቶቡስ አደጋዎች

በ MCPS የአደጋ ገምጋሚ ቦርድ እና በሜሪላንድ ስቴት መመሪያዎች መሠረት ሁሉም የአውቶቢስ አደጋዎች ለመከላከል-የሚቻል/ለመከላከል-የማይቻል በሚል ይለያሉ። ስለ ደህንነት ስልጠና/safety training፣ ግምገማ፣ እና ዓመታዊ የአደጋ ብዛት ቅነሳ ጥረት ዙሪያ በዓመት ለመከላከል የሚቻል አደጋ ከ45 በላይ እንዳይኖር ለመመጠን የመጓጓዣ/ትራንስፖርት መምሪያ ዒላማ አድርጓል/አስቀምጧል።

የ16 በጀት ዓመት42
የ17 በጀት ዓመት43
የ18 በጀት ዓመት39
የ19 በጀት ዓመት54

በአውቶቡስ የተጓጓዙ ተማሪዎች

የ16 በጀት ዓመት99,096
የ17 በጀት ዓመት101,225
የ18 በጀት ዓመት102,067
የ19 በጀት ዓመት104,555

የሞንጎመሪ ካዉንቲ የትምህርት ቦርድ ለ2019 የበጀት ዓመት(በአ) $2.60 ቢሊዮን የሥራ ማስኬጃ ባጀት ጁን 12/2018 አጽድቋል። በጀቱ ከ2018 የበጀት ዓመት የ$77.2 ሚሊዮን ጭማሪ /እድገት አሳይቷል። ይህም ዲስትሪክቱ ያለውን እድገት ለማስተዳደር እና ሁሉም የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከፍተኛ ስኬት እንዲያገኙ ለማረጋገጥ ወሳኝነት ባላቸው ነገሮች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያስችላል።

በበጀት አመት 2019 የሥራ ማስኬጃ ቤት ላይ የሱፐርኢንተንደንት ጃክ አር. ስሚዝን የጁን 12 ማስታወሻ ያንብቡ

ከ$77.2 ሚሊዮን የሥራ ማስኬጃ በጀት ጭማሪ አብዛኛው ገንዘብ ቁጥራቸው እያደገ ለመጣው የተማሪዎች ቁጥር አገልግሎቶችን ለመጠበቅ፤ለሥራ ቅልጥፍና/ጥራት ማረጋገጥ እና ቅድሚያ ትኩረት በሚሰጣቸው ስልታዊ ነገሮች ላይ ኢንቨስት ተደርጓል። በጀቱ ከ 1,800 በላይ የተማሪዎች ምዝገባ እድገትን ለመደገፍ $17.1 ሚሊዮን እና ወደ 202 ተጨማሪ መምህራን እና ሠራተኞች የስራ መደቦችን አካቷል። በተጨማሪም፣ የበጀት ጭማሪዉ አካል በማድረግ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሴፕቴምበር 2018 ላይ የተከፈተውን ቤያርድ ረስቲን አንደኛ ደረጃ ት/ቤትን/ Bayard Rustin Elementary School ጨምሮ፣ተጨማሪ ቦታዎችን አክሏል።

ስለ በጀት ሂደት እና የጊዜ ሰሌዳ በይበልጥ ይወቁ

የ 2019 ፊሲካል አመት በጀት ሪሶርሶች፦የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሥራ ማስኬጃ በጀት

የገንዘብ ምንጮች

ወጪዎች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በሜሪላንድ ስቴት ከፍተኛ/ትልቅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በስቴቱ ውስጥ እና በመላ አገሪቱ በፍጥነት እያደገ የሚገኝ የትምህርት ዲስትሪክት ነው። ከ2008–2009 የትምህርት ዓመት ወዲህ፣ MCPS በ 26,143 ተማሪዎች እድገት አሳይቷል። በጠቅላላ የትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ የሚገቡ ተማሪዎች ብዛት እየጨመረ በሄደ መጠን፣ የእድገቱ ትኩረት ከኤለመንተሪ ትምህርት ቤት ደረጃ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በተለይም ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃ እየዞረ ነው። ይሀ ትርጉም ያዘለ የምዝገባ እድገት ለተጨማሪ የመማርያ ክፍል ቦታ ጭማሪ ከመጠን በላይ የሆነ ጥያቄ እየፈጠረ ነው። ባለፈው አስር ዓመት እያደገ የመጣውን የተማሪዎች ቁጥር ለማስተናገድ MCPS ከ 15,000 በላይ መቀመጫዎችን ጨምሯል፣ ነገር ግን ከዚህ ዓይነት የእድገት ፍጥነት ጋር ለማጣጣም በቂ አይደለም።

የ 2019 በጀት ዓመት ካፒታል ባጀት እና የበጀት ዓመት 2019 - 2024 የካፒታል ማሻሻያዎች ፕሮግራም ፣ ከ $365.5 ሚሊዮን የ 2019 በጀት አመት ወጪ ጋር፣ ለስድስት ዓመታት በጠቅላላዉ $1.83 ቢሊዮን ነዉ። ከዚህ በታች ያለው መረጃ በ 2019 በጀት ዓመት የተጠናቀቁ፣በሂደት ወይም በእቅድ ላይ ያሉ ፕሮጄክቶችን ይወክላል።


አሽበርተን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Ashburton Elementary School

Ashburton Elementary School/አሽበርተን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት9,740 ስኩዌር ፊት ጭማሪ

S. Christa McAuliffe Elementary School

S. Christa McAuliffe Elementary School24,871ስኩዌር ፊት ጭማሪ

ለክስማነር አንደኛ ደረጃ ትምህት ቤት/Luxmanor Elementary School

ለክስማነር አንደኛ ደረጃ ትምህት ቤት/Luxmanor Elementary Schoolየእደሳ/ማጠናከሪያ//ማስፋፋት ፕሮጀክት።

ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Seneca Valley High School

ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት /Seneca Valley High Schoolየእደሳ/ማጠናከሪያ/ማስፋፋት ፕሮጀክት።


አዳዲስ ት/ቤቶች፣ ቅጥያዎች/የተጨመሩ፣ ማጠናከሪያ/እደሳ(sq. ft.)

ትምህርት ቤት ዓይነት Sq. Ft.
Ashburton ES/አሽበርተን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተጨማሪ/ቅጥያ 9,740
S. Christa McAuliffe ES ሳ. ክሪስቲ ማክአሉፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተጨማሪ/ቅጥያ 24,871
Snowden Farm ES/ስኖዎድን ፋርም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ኣዲስ 92,366
ድምር 126,977

በትምህርት ሥርዓቱ

የካፒታል ማሻሸያ ፕላን ገፅ

ለ 2019-2024 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም፤ የትምህርት ቦርድ ለበጀት ዓመት 2020 ካፒታል ባጀት እና ማሻሻያዎችን ጠይቋል

የትምህርት ቦርድ $1.83 ቢሊዮን የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ባጀት አፅድቋል

አዲስ ግንባታና ከፍ ያሉ /ዋነኛ ካፒታል ፕሮጀክቶች

ሴፕቴምበር 2019 ትምህርት ሲጀመር የተጠናቀቁ የ 2018-2019 ትምህርት ዓመት ፕሮጀክቶች

 • 126,977 ስኩ.ጫማ አዲስ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቋል
 • በሰፕቴምበር 2019 ለት/ቤት መክፈቻ የተጠናቀቁ ሶስት የካፒታል ፕሮጄክቶች
  • አንድ አዲስ ት/ቤት– Snowden Farm Elementary School /ስኖዉድን ፋርም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • ሁለት የቅጥያ ፕሮጀክቶች
   • አሽበርተን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Ashburton Elementary School
   • S. Christa McAuliffe Elementary School
 • ለሰባት ካፒታል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ነዉ
  • ሁለት የቅጥያ ፕሮጀክቶች
   • Thomas S. Pyle Middle School/ቶማስ ኤስ. ፓይል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
   • ታኮማ ፓርክ ሚድል ስኩል Takoma Park Middle School
  • አምስት የእደሳ/ማጠናከሪያ/ማስፋፋት ፕሮጀክቶች
   • ለክስማነር አንደኛ ደረጃ ትምህት ቤት/Luxmanor Elementary School
   • Maryvale Elementary School/Carl Sandburg Center/ማሪቬል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት/ካርል ሳንድበርግ ማእከል
   • Potomac Elementary School/ፖቶማክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
   • ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Seneca Valley High School
   • Tilden Middle School/Rock Terrace School/ቲልደን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት/ሮክ ቴረስ ት/ቤት
 • ለ 12 ካፒታል ፕሮጀክቶች እቅድ/ንድፍ በመካሄድ ላይ ነዉ
  • ስድስት የቅጥያ/ጭማሪ ፕሮጀክቶች
   • John F. Kennedy ጆን ኤፍ. ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
   • A. ማሪዮ ሎይደርማን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/ Mario Loiederman Middle School
   • Montgomery Knolls Elementary School/ሞንጎሞሪ ኖልስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
   • ፓይን ክረስት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Pine Crest Elementary School
   • Silver Spring International Middle School ሲልቨር ስፕሪንግ ኢንተርናሽናል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
   • Walt Whitman High School/ዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ት//ቤት
  • ሶስት አዲስ ት/ቤቶች/እንደገና የመክፈት ፕሮጀክቶች
   • Clarksburg Cluster Elementary School #9 /ክላርስበርግ ክላስተር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት#9
   • Gaithersburg Cluster Elementary School #8/ጌትስበርግ ክላስተር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት#8
   • Charles W. Woodward High School (reopening) /ቻርለስ ደብሊዉ. ዉድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት(እንደገና መክፈት)
  • ሶስት የመተካት/ማስፋፋት ፕሮጀክቶች
   • ዱፊፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት DuFief Elementary School
   • ኮሎ.ኢ. ብሩክ ሊ መካለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Col. E. Brooke Lee Middle School
   • ኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Northwood High School
 • ለስድስት ዋና ካፒታል ፕሮጀክቶች እቅድ/ንድፍ በመካሄድ ላይ ነዉ
  • በርንት ሚልስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Burnt Mills Elementary School
  • ኒልስቪል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት Neelsville Middle School
  • Poolesville ሁ/ደ ት/ቤት/Poolesville High School
  • ሳውዝ ሌክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (South Lake Elementary School)
  • ስቶንጌት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Stonegate Elementary School
  • Woodlin Elementary School /ዉድሊን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት