Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: August 27, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

ለ2018 - 2019 የትምህርት ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ!

Welcome Video

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ለ 2018-2019 የትምህርት ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ሠራተኞች በሰመር ወራት ለዚህኛው የትምህርት ዓመት ሲዘጋጁ ቆይተዋል። ሠራተኞችን እየቀጠርን፣ ህንፃዎችን እያሳደስን እና እያፀዳን፣ በስልጠናዎች ላይ እየተሳተፍን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እየገዛን፣ የደህንነት ጥበቃ ሂደቶችን እና አሠራሮችን እየገመገምን፣ እና የትምህርት ዕቅዶችን እያዘጋጀን ቆይተናል። እነዚህን ሁሉ ያደረግንበት ምክንያት ዋናኛ ዓላማችንን በማስፋት ሁሉንም ተማሪዎች ለወደፊት ስኬታማ እንዲሆኑ ለማስቻል/ለማዘጋጀት ነው።

የተዋጣለት/ስኬታማ የትምህርት ክፍል እና ት/ቤት እንዲኖረን፣ የሳይንስ መሠረታዊ ነገሮችን፣ ስነጥበብ እና ቀልባችንን/ልቦናን በማስተማር ተግባር ላይ ማካተት እንዳለብን በአጽኖት አምናለሁ። ሳይንስ:- የምናስተምረውን ምርምር፣ የግኝቶችን መረጃ፣ እና በአእምሮ ማደግና የአንጎልን እውቀት እድገት ያሳውቃል። ስነጥበብ፦ የስሜት ህዋሳቶቻችንን እና አእምሯችንን ያነቃቃል፣ የመማር ፍላጎትን ያነሣሣል። ልብ/ቀልባችን፦ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች ጋር ግንኙነቶችን ለማደበር/ለመገንባት እና ቁርጠኝነታችንን፣ እንክብካቤ፣ ጥልቅ ርህራሄ፣ እና የኃላፊነት ስሜትን ያመለክታል። እነዚህ ሦስቱ ነገሮች በአንድነት ለተማሪ ስኬታማነት በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን አምናለሁ።

የእኛ የትምህርት ሲስተም ለበርካታ ተማሪዎች ከፍተኛ የስኬታማነት ታሪክ አለው፣ ነገር ግን ለሁሉ አይደለም። ይህ መቀየር አለበት። በዚህ ዓመት፣ ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽነት ያለው እድል በመስጠት የተማሪዎችን እምቅ ችሎታ በመፍታት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እና ወደ ከፍተኛው የስኬት ደረጃ እንዲደርሱ ለማድረግ MCPS በልቀት ላይ ያተኮረ ሥራውን ይቀጥላል።

በቅርብ ጊዜ Andy Andrews/አንድይ አንድሪውስ በሚባል ደራሲ የተጻፈ “When confronted with a challenge, the committed heart will search for a solution.” / ጥረትና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ሁኔታ ሲያጋጥም ጠንካራ እምነት ያለው ልብ መፍትሔ ይፈልጋል የሚል ልቤን የኮረኮረኝ ጥቅስ ነበር።

ለተማሪዎቻችን ልባቸውን የሰጡ እና መስዋእትነት የሚከፍሉ በርካታ የሥራ ባልደረቦች እና የማህበረሰብ አባላት ስላሉን እድለኞች ነን። በጋራ ሆነን፣ ለሁሉም ተማሪዎች ዋነኛ እሴታችን የሆነውን አላማችንን እንደምናከናውን እርግጠኛ ነኝ።

እጅግ መልካም የትምህርት ዓመት እንደሚሆንልን አስባለሁ!

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent
ጃክ አር. ስሚዝ ዶ/ር
የት/ቤቶች የበላይ ኃላፊ