Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: November 30, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣

የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ (Maryland State Department of Education) የትምህርት ቤቶችን ስኬታማነት የሚመዝን እና መሻሻል የሚገባቸውን ነገሮች እንዲያመለክት የተዘጋጀ የአካውንቴብሊቲ ሪፖርት ካርድ ሐሙስ ዲሴምበር 4 ለሁሉም ት/ቤቶች ያስተላልፋል። የሪፖርት ካርዱ የተዘጋጀው የህዝብ ትምህርት ቤቶች ለሁሉም ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት እንዳለባቸው ለማረጋገጥ በተደነገገው "ሁሉም ተማሪ ውጤታማ ይሆናል/Every Student Succeeds Act (ESSA)" የሚለውን የፌደራል ህግ ተግባራዊነትን ተመርኩዞ ነው።

የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ ዲዛይን የተደረገው በእንግሊዝኛ የቋንቋ ስነ-ጥበብ እና በሒሳብ ከስቴት የሚሰጡ ፈተናዎችን ጨምሮ፣ ከድህረ-ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ የሚኖራቸው ዝግጁነት፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች ያላቸውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት፣ የተመራቂዎች ብዛት መጠን፣ እና ተማሪዎች አጠቃላይ እውቀት የማግኘት እድል እና በጠቅላላ እውቀት የሚያገኙት ክሬዲትን በሙሉ በማካተት የት/ቤትን ውጤታማነት በተለያዩ በርካታ መንገዶች ለመለካት በሚያስችል ሁኔታ ነው። በመጪዎቹ ዓመታት፣ የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ በ (5 & 8 ክፍሎች እና በ 8ኛ ክፍል) የሳይንስ፣ እና የማህበራዊ ጥናት ክንውኖችን ያካትታል፣ እናም የተማሪ/የአስተማሪ አጠቃላይ ሁኔታ ዳሰሳን ይጨምራል። በእነዚህ የተግባር እንቅስቃሴዎች አመላካችነት በመመርኮዝ፣ ስቴቱ ለእያንዳንዱ ት/ቤት በመቶኛ (percentile rank) ደረጃ በማውጣት የተገኘ ነጥብ/ውጤት ፐርሰንት እና ከ1 እስከ 5 ባለው ደረጃ የኮከብ ምልክት ይቀመጣል።*

[ስለሜሪላንድ የሪፖርት ካርድ የበለጠ ለማወቅ ይህንን ቪድዮ ይመልከቱ፦]

የሜሪላንድ የሪፖርት ካርድ አሠራር በርካታ ገላጭ ዘዴዎችን በተለያዩ ፈርጆች በመጠቀም፣ የተማሪዎች አካደሚክ/የትምህርት እድገት እና ክንውን የሚለካበት ብቸኛ የሆነ አንድ የመረጃ ነጥብ—Partnership for Assessment of Readiness for College and Careers (PARCC) ውጤት ነው። PARCC የነጥብ አሠጣጥ ተመሣሣይነቱ በኮርሱ ፍጻሜ የተማሪ አሠራር፣ የታየው ለውጥና-እርምጃ/end-of-course view of students’ performance or progress/ ይመዛዘናል። ይህ አንድ ጠቃሚ መለኪያ ቢሆንም፣ የተማሪዎችን የትምህርት አያያዝ እና ክትትል ለመመዘን እና እንደየሁኔታው ምላሽ ለመስጠት እስከ ዓመቱ ፍጻሜ ድረስ መጠበቅ አያስፈልገንም፣ ወይም እስከ ሴሚስተር ማለቂያ እንኳ መጠበቅ አይኖርብንም።

ሪፖርት ካርዱ ስለ ትምህርት ቤቶቻችን ጠቃሚ መረጃዎችን/ኢንፎርሜሽን የሚሰጥ ቢሆንም፣ የተመረጡት የመረጃ/ውሂብ ነጥቦች ከሌሎች ዲስትሪክቶች ጋር ሲነፃፀር ስለ እኛ 163,000 ተማሪዎች የተሰጠው ማነፃፀሪያ ውሱን ነው። ትምህርት ቤትን ማሻሻል ከበፊቱም የአካባቢ ኃላፊነት ነው። የትምህርት ተጽእኖ ያረፈበ(ባ)ት ማን እንደሆነ/ች፣ ማን ጉጉት እንዳለበ(ባ)ት፣ እና ማን የእኛን እርዳታ እንደሚፈልግ/እንደምትፈልግ ስለ ተማሪዎቻችን የበለጠ የምናውቀው እኛ ነን።

የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድን ውሱንነት ለማሻሻል MCPS ያዳበረው Equity Accountability Model ስለ ትምህርት ቤት ስኬታማነት ይበልጥ ዝርዝር የያዘ ሪፖርት የሚሰጥ ሞዴል ተዘጋጅቷል። የ Equity Accountability Model በርካታ የሆኑ ተደጋጋሚ መመዘኛዎችን ት/ቤት የልዩነት ክፍተቶችን ለማስወገድ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሁሉንም ተማሪዎች ፍላጎት ለማሟላት በተማሪዎች ስኬታማነት ላይ እየሠራ/እያሟላ ከሆነ የተማሪን እርምጃ ለመወሰን ይጠቅማል። የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ እና local equity accountability model፣ የተማሪን የተሻለ የወደፊት ህይወት ስለሚያካትት ያ መልካም እርምጃ ነው።

[ስለ MCPS Equity Accountability Model የበለጠ ለማወቅ ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ፦]

ስለ ተማሪ ስኬታማነት የ MCPS ስትራተጂ ባለብዙ ፈርጅ እና የሁሉንም ተማሪዎች ለማሟላት የተቀረጸ (የተዘጋጀ) መሆን አለበት። ተመራቂዎቻችን በኮሌጅ፣ በሥራ እና በማህበረሰብ ዘንድ ውጤታማነታቸው በሚረጋገጥበት ሁኔታ ለመሥራት በቁርጠኝነት እንቀጥላለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር
Jack R. Smith, Ph.D.
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ኃላፊ

*Primary schools serving only grades prekindergarten through 2 will not get a star rating.