Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: January 3, 2019

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ባለፉት በርካታ ወራት ውስጥ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበብ/English Language Arts (ELA) እና የሂሳብ/Mathematics ማስተማሪያ አዲስ ከሪኩለም ምርጫ ላይ ስላደረጉት ተሳትፎ እናመሰግናለን። በአሁን ወቅት የምርጫውን ሂደት በማጠናቀቅ ደረጃ ላይ እንገኛለን። በውጤቱም መሠረት፣ጃኑወሪ 8/2019 ከሚካሄደው የቦርድ ስብሰባ አስቀድሞ የደረስንበትን ደረጃ ለማሳወቅ ነው የምጽፈው።

ባለፉት በርካታ ሣምንታት፣ብርቱ የግምገማ ደረጃ አሰጣጥ፣ግብረመልስ እና መረጃ/ዳታ በማሰባሰብ ክለሳ እና የትንታኔ ሥራዎች ተከናውነዋል። ከእነዚህ የመረጃ/ዳታ ምንጮች አንዳንዶቹ የሚያካትቱት፦ ቴክኒካዊ ግምገማዎች፣ የውጭ ባለሙያ ግምገማዎች፣ ከሌሎች ዲስትሪክቶች ጋር ማመሳከር፣ የይዘቱ ዋና ቡድን ያከናወናቸው ግምገማዎች፣ ቬንደሮች ያቀረቧቸውን ማወዳደር፣ ቃለመጠይቆች፣ በድረ-ገጽ ላይ ለህዝብ አስተያየት ማቅረብ፣ እና ከበላይ ኃላፊዎች/መሪዎች ጋር የተካሄዱ ውይይቶች ናቸው። ለማጠቃለያ ውድድር ከተመረጡት ጋር የኮንትራት ድርድር ለማድረግ ጀምረናል።

እነዚህ የተመረጡት የማጠቃለያ ተወዳዳሪዎች የሚያካትቱት፦

  • PreK-5 Mathematics: Eureka Math (Great Minds)
  • Grades 6-8 Mathematics: LearnZillion Illustrative Mathematics (LearnZillion)
  • Grades 6-8 ELA: StudySync (McGraw Hill Education)

እነዚህ ለማጠቃለያ/ለፍጻሜ ውድድር የተመረጡት ጃኑወሪ 8/2019 ለሚደረገው የትምህርት ቦርድ ለውሳኔ ይቀርባሉ። ስለዚህ ይህ ውድድር የሚከናወነው በትምህርት ቦርድ ውሳኔ እና ከእያንዳንዳቸው ጋር ውጤታማ ድርድር ሲደረግ ብቻ መሆኑን እባክዎ እንዲገነዘቡ ያስፈልጋል። ስለ አጠቃላይ ሂደቱ እና የተመረጡት ማቴሪያሎች ስለሚኖራቸው ጠንካራ ጠቀሜታ በዝርዝር ጃኑወሪ 8 በሚካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ ሲቀርብ እንዲመለከቱ እንጋብዝዎታለን።

በተጨማሪም፣ ስለ PreK-5 ELA የግምገማ ሂደት እና ማመሣከሪያዎች እስካሁንም በሂደት ላይ መሆናቸውን ለማስገንዘብ እንወዳለን። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ELA ማቴሪያል ፌብሯሪ 12/2019 ለትምህርት ቦርድ እንዲቀርብ እየተሠራበት ነው። በተጨማሪ፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት “Algebra I” ግምገማ እና የመምረጥ ሂደት እስካሁን ድረስ በመካሄድ ላይ ነው።

እባክዎ፦ ስለ ከሪኩለም መረጣ እና ለህዝብ ስለሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ድረ-ገጽ MCPS Curriculum Review webpage በተከታታይ ይጎብኙ፦ በዚህ ሂደት ስለሚያደርጉት ተሳትፎ
በድጋሚ አመሰግናለሁ መልካም አዲስ አመት!

ከመልካም ምኞት ጋር

Maria V. Navarro, Ed.D. ማሪያ ቪ. ናቫሮ የትም/ዶክተር
Chief Academic Officer የአካደሚ ዋና ኃላፊ
Montgomery County Public Schools ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ