Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: December 3, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ባለፉት በርካታ ሣምንታት፣ ስለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበብ እና የሒሳብ ሥርዓተ-ትምህርት (ከሪኩለም) እና የማስተማሪያ ማቴሪያሎችን በሚመለከት 118 አባላትን የያዘ የሠራተኞች ቡድን ለጥያቄዎቻችን የተሰጡትን አስተያየቶች/proposals ገምግመዋል የፕሮፖዛል ጥያቄ። ከእነርሱ በቀረቡት አስተያየቶች ላይ ተመሥርቶ ሦስት የአንደኛ ደረጃ እና ሁለት የመካከለኛ ደረጃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበብ ሥርዓተ-ትምህርት (ከሪኩላር) ውጤቶችን/products፣ እና ሁለት የአንደኛ ደረጃ እና ሦስት የመካከለኛ ደረጃ የሒሳብ ሥርዓተ-ትምህርት (ከሪኩላር) ውጤቶችን/products በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተግባራዊ ይደረጋሉ።

 መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ወላጆች እና ማህበረሰቡ እንዲመለከቱት ስለእያንዳንዱ ውጤት/product ሻጮች/ቬንደሮች አውደርዕይ እንዲያዘጋጁ ተጠይቀዋል። እያንዳንዱ አቀራረብ/ዝግጅት በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ስለሚገኝ እስከ ዕሁድ፣ ዲሴምበር 9/2018 ድረስ በ MCPS Curriculum Review webpage/ድረ-ገጽ ላይ ለማየት ይቻላል። ከአቀራረቡ በተጨማሪ፣ በሚቀጥሉት ፍሬሃሳቦች ዙርያ የእርስዎን ሃሳብና አስተያየት የሚጠይቅ የግብረመልስ-ቅጽ ይገኛሉ።

  • የተማሪ ተሞክሮ፦ ይህ ዓይነቱ product/ዝግጅት ተማሪዎች በንቃት እንዲሣተፉና ለሁሉም ተማሪዎች መማር/ማወቅ የሚፈልጉትን/የሚያዘነብሉትን ምላሽ ይሰጣል?
  • የመምህር(ት) ተሞክሮ፦ ይህ ዓይነቱ product/ዝግጅት የሁሉንም ተማሪዎች የመማር/የማወቅ ዝንባሌ ምላሽ ለመስጠት፤ ሁሉም መምህራን ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያቅዱ እና ለማስተማር እንዲችሉ/እንዲያስተላልፉ ይረዳል/ይደግፋል?
  • የወላጅ ተሞክሮ፦ ይህ ዓይነቱ ዝግጅት/product ከመማሪያ ክፍል ውጭ ወላጆች/ሞግዚቶች ተማሪዎቻቸውን ለመርዳት እንዲችሉ ለወላጆች/ለሞግዚቶች ስለ ሥርዓተ-ትምህርቱ (ከሪኩለም) በቂ መረጃ/ኢንፎርሜሽን ይሰጣል?

በከሪኩለም/የሥርዓተ-ትምህርት ምርጫ ሂደት ላይ እንዲጨመር፣ ሁሉም የግብረመልስ-ቅጾች እስከ ዲሴምበር 9/2018 ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል። ስለ ቅጽ አሞላል የሚያሳይ መመሪያ በ "MCPS Curriculum Review webpage" ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።

በዚህ እጅግ አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ የእርስዎን አስተዋጽኦ ለማግኘት እንጠብቃለን።

አመሰግናለሁ።

ከመልካም ምኞት ጋር።

Maria V. Navarro, Ed.D.
Chief Academic Officer
Montgomery County Public Schools
ማሪያ ቪ. ናቫሮ የትም/ዶክተር
የአካደሚ ዋና ኃላፊ
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ