Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: January 26, 2018

elementary students at recess

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

ከሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የተላለፈ መልእክት:- በብዙሃን መገናኛ መስመር ላይ ደህነትን መጠበቅ

ይህን የምጽፈው ትኩረት እንድንሰጥበት ስለቀረበልን የማህበራዊ መገናኛ አውታር እንቅስቃሴ/social media activity እና በአውታረ-መረብ የልጅዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ መገልገያዎችን/resources ለመስጠት ነው።

አንድ ወይም ሁለት ግለሰብ ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶችን (የMCPS ተማሪዎችን ጨምሮ) እርቃነ-ስጋ በማጋለጥ በግል የማህበራዊ መገናኛ አውታረ መረብ ላይ እንደሚለጥፉ ለሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ከበርካታ የማህበረሰብ አባላት ሪፖርቶች ደርሰውናል። እኛ እንደሚገባን ብዙዎቹ እርቃነ-ስጋቸውን በግል የማህበራዊ መገናኛ አውታረ-መረብ ላይ የተለጠፉት ፎቶዎች ተወስደው ወይም በፎተግራፎቹ ላይ የሚታዩት ተማሪዎች ተስማምተው ሊሆን ይችላል።

MCPS ተማሪዎችን ለዲጂታል/አሃዛዊው ዓለም ለማዘጋጀት በቁርጠኝነት ይሰራል። በማህበራዊ መገናኛ-መረብ ሲሳተፉ ለተማሪዎቻችን ደህንነት ውጤታማ መጠቀሚያዎችን/resources ለመስጠት በምናደርገው ጥረት/የእንቅስቃሴ አካል የተፈጥሮ እውቀት/አጠቃላይ የጋራ ግንዛቤ ትምህርት ለመስጠት በአጋርነት እንሳተፋለን። እነዚህ መጠቀሚያዎች/resources በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ። http://www.montgomeryschoolsmd.org/digital-citizenship/index.html. እባክዎን ጥቂት ጊዜ ይውሰዱና ማቴሪያሎቹን ከድረ-ገጽ ላይ ተመልክተው/አንብበው በዚህ የዲጅታል/አሃዛዊ ዘመን ላይ የእርስዎ ልጆች ማድረግ ስለሚኖርባቸው ምርጫ እና ጥንቃቄ ከልጆችዎ ጋር ተወያዩ/ተነጋገሩ። በተጨማሪም፣ እባክዎን ስለቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውም ክትትል ማድረግዎን ይቀጥሉ።
የተማሪዎቻችን ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። MCPS በጉዳዮ ላይ ምርመራና ክትትል እንዲደረግ የሞንጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ መምሪያን አነጋግሯል። እነርሱም ምርመራ እያካሄዱ ናቸው።
ልጅዎ ከዚህ ነገር ጋር ግንኙነት አለው/አላት ወይም ኢንፎርሜሽን አለው/አላት ብለው የሚያምኑ ከሆነ በስልክ ቁጥር፦ 240-773-5400 ለፖሊስ ደውለው እንዲያነጋግሩ አበረታታዎታለሁ። በተጨማሪ፣ ተማሪዎችን ለመደገፍ ካስፈለገ የምክር አገልግሎት/ካውንስሊንግ ለመስጠት ት/ቤቶችም የተዘጋጁ ሠራተኞች አሏቸው።

የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ በምናደርገው ጥረት በጋራ ለመስራት ስለሚያደርጉልን ድጋፍ እና አጋርነት አመሰግናለሁ።

ከአክብሮት ጋር

Derek Turner
Director of Communications