Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: January 23, 2018

elementary students at recess

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የአየር ሁኔታ-ማካካሻ ቀን እቅድ

ጃኑዋሪ 24, 2018

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፦

በትምህርት ካላንደር ላይ ከዚህ ቀጥሎ ስላለው (የአሁኑን) የትምህርት ወቅት ላሳውቃችሁ እፈልጋለሁ።
እንደምታውቁት፣ በቅርቡ የተከሰተው ከባድ የአየር ሁኔታ የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ጃኑዋሪ 4 እና ጃኑዋሪ 17፣ በሁለቱ ቀናት ት/ቤቶች እንዲዘጉ አስገድዷል። 2017-2018 የ MCPS የትምህርት ቤት ካላንደር የሚያካትተው 182 የትምህርት ቀናት፣ በሜሪላንድ ስቴት ከሚጠበቀው ገደብ ሁለት ቅናትን የበለጠ ነው። ስለዚህ፣ በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የተዘጉት ሁለት የትምህርት ቀናት በትምህርት ካላንደሩ ላይ ሌላ ማሻሻያ ሳይደረግ ለማካካስ ያስችላል።

ነገር ግን፣ ማናቸውም ሌላ ተጨማሪ ት/ቤት የሚያዘጋ ድንገተኛ የአየር ሁኔታ ከተከሰተ፣ ከስቴቱ የሚጠበቀውን ቀናት ለማሟላት ከ MCPS የትምህርት ቤት ካላንደር ላይ አንድ ወይም ሁሉንም የመጠባበቂያ/ማካካሻ ቀኖች መጠቀም ያስፈልጋል። ከዚህ በታች ያለው ቀኖቹን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው በቅደምተከተል ያሳያል።

  • ለአንድ ተጨማሪ ድንገተኛ የአየር ሁኔታ ት/ቤት ከተዘጋ፣ የትምህርት ዓመቱ ጁን 13/2018 በአንድ ቀን ይራዘማል።
  • ለሁለት ድንገተኛ የአየር ሁኔታ ት/ቤት ከተዘጋ፣ የትምህርት ዓመቱ እስከ ጁን 14/2018 ይራዘማል።
  • በድንገተኛ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሦስት ተጨማሪ ከተዘጋ፣ የትምህርት ዓመቱ እስከ ጁን 15/2018 ይራዘማል ማለት ነው። (ማስታወሻ፦ በስቴት ህግ መሠረት፣ በ MCPS የትምህርት ዓመትን ከጁን 15 ማሳለፍ አይቻልም)
  • በድንገተኛ የአየር ሁኔታ ተጨማሪ አራት ቀን ከተዘጋ፣ ማርች 26/2018 (የመጀመሪያው የስፕሪንግ የእረፍት ቀን) እንደ ማካካሻ ቀን እንጠቀማለን።
  • በድንገተኛ የአየር ሁኔታ ምክንያት ተጨማሪ አምስት ቀን ከተዘጋ፣ ማርች 27/2018 (ሁለተኛው የስፕሪንግ የእረፍት ቀን) እንደ ማካካሻ ቀን እንጠቀማለን።

የትምህርት ዓመቱን ከጁን 12 በላይ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ ጁን 12 ሙሉውን ቀን የትምህርት ቀን ይሆንና አዲሱ የመጨረሻ የትምህርት ቀን በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀን/early release day ይሆናል።
እባክዎ ያስታውሱ፦ MCPS በስቴት የተሰጠውን የትምህርት ቀናት ገደብ ያሟላ ቢሆንም፣ ለበረዶ ቀን ማካካሻ የመጀመሪያ ቅርበት ያለው ጃኑዋሪ 26/2018 ይህ ዓርብ ቀን MCPS ለተማሪዎች ዝግ ይሆንና ለሠራተኞች የፕሮፌሽናል ቀን ሆኖ ይውላል።

ያለመታደል ሆኖ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ተጨማሪ ቀኖች የሚዘጉ ከሆነ፣ MCPS ቢያንስ 180 የትምህርት ቀናት የሚለው ገደብ እንዲነሣለት ስቴቱን ይጠይቅ ይሆናል። ገደብ እንዲነሣ የትምህርት ሥርዓቱ የማካካሻ ቀናትን መጨመር ያለበት በትምህርት ዓመት መጨረሻ ላይ ብቻ ሳይሆን ስለሚደረገው ጥረትና ትጋት ተአማኒነትን ለማሳየት የትምህርት ካላንደሩን በተማሪዎች የትምህርት ቀናት ጭምር የባከኑ ጊዜያትን ማካካስ ይጠበቅባቸዋል።

የእኛ ግባችን የተማሪ ትምህርት/መማር ሆኖ ሳለ፣ የቅድሚያ ትኩረታችን መሆን ያለበት የተማሪዎቻችን እና የሠራተኞ ደህንነት ነው። MCPS መጥፎ የአየር ሁኔታዎችን በአንክሮ እየተከታተለ በትምህርት ቤት ካላንደር ላይ ተጽእኖ የሚያስከትል ወቅታዊ መረጃ ማሳወቅ/ማስተላለፍ ይቀጥላል። ስለ MCPS የት/ቤት ካላንደር የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ይጎብኙ፦ http://www.montgomeryschoolsmd.org

ከአክብሮት ጋር

ጃክ ስሚዝ (ዶ/ር) Jack Smith, Ph.D.
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ Superintendent of Schools