Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: February 15, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

A Message from Superintendent Jack R. Smith:
የአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት

Emergency Preparedenss Video

በ ፍሎሪዳ፣ ማርጆሪ ስቶንማን ዳግላስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Marjory Stoneman Douglas High School in Florida) የተከሰተው የግድያ ሁኔታ ሁላችንንም በጥልቅ አሳዝኖናል እና አናውጦናል። የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች ቤተሰቦች ልባችን እና ሃሳባችን በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ከፍተኛ ሃዘን ከደረሰባቸው ቤተሰቦች ጋር ነው።

እንደዚህ ዓይነት አሳዛኝ ድርጊቶች በማህበረሰባችን ውስጥ ከባድ ጭንቀት እና ስጋትን እንደሚፈጥሩ፣ ይህንን ዓይነት ሁከት ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አንስተው ለመነጋገርም ከባድ እንደሚሆንባቸው ይገባኛል። ለውይይቶች እንዲረዳ፣ አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን/helpful resources በዚህ የመገናኛ አውታር ለጥፈናል፦ http://www.montgomeryschoolsmd.org/emergency/preparedness/index.aspx#other  በተጨማሪ፣ እንደዚህ ዓይነት አሳዛኝ ድርጊቶችን/ሁኔታዎችን ተከትሎ በተፈጥሮ ከሚመጣው ጭንቀትና የስሜት መጎዳት እንዲላቀቁ ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ለመርዳት የተዘጋጁ የት/ቤት ካውንስለሮች አሉ።

በተጨማሪ፣ አስቸኳይ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ዲስትሪክቱ ምን እንደሚያደርግ በርካታ ወላጆች ጥያቄዎችን ያቀርባሉ። ለተማሪዎቻችን እና ለሠራተኞቻችን ደህንነት ጥብቅ ትኩረት የምንሰጥ መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ። MCPS የት/ቤቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ባለ ብዙ-ፈርጅ ዘዴዎችን ይጠቀማል። አንደኛ፣ አስቸኳይ ሁኔታ ሲያጋጥም ደህንነታቸውን በመጠበቅ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ ሁሉንም ት/ቤቶች ለአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን እንዲለማመዱ እና በተጠንቀቅ እንዲሆኑ MCPS ይፈልጋል። ይህም የሚያካትተው፦ መቆለፍ፣ ከለላ መያዝ፣ በመሬት ላይ መውደቅ፣ ተሸፋፍኖ መቆየት፣ ከባድ የአየር ሁኔታ፣ ካሉበት በፍጥነት መልቀቅ፣ እና ሰላም መሆኑ ሲረጋገጥ ወደ ቦታ መመለስ። ቪዲዮችን ጨምሮ በርካታ መረጃዎች/ኢንፎርሜሽን በዚህ ድረገጽ ላይ ስለሚገኙ ይመልከቱ፦ http://www.montgomeryschoolsmd.org/emergency/preparedness/.

በየቀኑ የት/ቤቶችን ደህንነት እና ጤናማነት ለመጠበቅ MCPS ከአካባቢው የህግ አስከባሪ ኃይሎች ጋር በቅርብ ይሠራል። በት/ቤት ጥበቃ ኦፊሰር ፕሮግራም አማካይነት/School Resource Officer (SRO)፣ ቃለመሃላ የፈጸሙ የፖሊስ መኮንኖች ከት/ቤት አስተዳደር ሠራተኞች እና ከት/ቤት የጥበቃ ቡድኖች ጋር በ MCPS ት/ቤት ክልል ውስጥ ደህንነት በመጠበቅ ይሰራሉ።

በእኛ በኩል ከምናደርጋቸው የአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት እና የፖሊስ አጋርነት በተጨማሪ፣ የት/ቤቶችን ጊቢ/ክልል ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ግንባታዎችን ኢንቨስት አድርገናል። ይህ የሚያካትተው የመግቢያ ቁጥጥር ሲስተም እና የጎብኚዎች ማኔጅመንት ሲስተም በሁሉም ት/ቤቶች የተዘረጉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ስውር ካሜራዎች በት/ቤቶች ህንፃዎች ከውስጥ እና ከውጭ ተተክለዋል።

ከሁሉም በላይ፣ ለተማሪዎቻችን የመማሪያ አካባቢዎች ደህንነት እና ጤንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን በቁርጠኛነት የሚሰሩ መምህራን እና አስተዳዳሪዎችን MCPS አሰማርቷል። እነዚህ ሠራተኞች ከጥበቃ/የፀጥታ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ትምህርት ቅድሚያ ትኩረታችን ቢሆንም ደህንነት ከምንም የበለጠ ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያረጋግጣሉ።

ከአክብሮት ጋር
Dr. Jack R. Smith ዶር. ጃክ አር. ስሚዝ
Superintendent of Schools የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ