Is this email not displaying correctly?View it in your browser Date: March 12, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

ከት/ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ ጃክ አር. ስሚዝ/Superintendent Jack R. Smith ስለ ማርች 14 የተማሪዎች ሰላማዊ ትርኢት የተላለፈ መልእክት:-

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፦

ባለፈው ሳምንት ብዙዎቻችሁ ስለ ማርች 14 የተማሪዎች የተደራጀ ሰላማዊ ሰልፍ አስተያየቶቻችሁን ለማካፈል ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ደውላችኋል ወይም ጽፋችኋል። አብዛኛዎቻችሁ ከልጃችሁ ት/ቤት ርእሰ መምህራን የሰማችሁ ቢሆንም እኔም በበኩሌ ስለ እረቡዕ ቀን ያለኝን ሃሳብና ስጋት ልገልጽላችሁ እፈልጋለሁ።

በ Parkland, Fla፣ በት/ቤት ውስጥ የተፈጸመው አሳዛኝ ግድያ ሁላችንንም ነክቶናል፣ ነገር ግን ተፅእኖው በከባድ ሁኔታ የወደቀው የአደጋው ሠለባ በሆኑት እና ከአደጋው በተረፉት መካከል ራሳቸውን በሚመለከቱ ተማሪዎች ላይ ነው። ይህ አሳዛኝ ድርጊት እውነተኛ የሆነ ስጋትና ፍርሃት ፈጥሯል። እንዲሁም ደግሞ በት/ቤት ውስጥ ስለራሳቸው ደህንነት እና ሠላም መረጋገጥ የሚችልበት ስልት እንዲፈጠር ለማስቻል ተማሪዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲነሳሱ አድርጓል። የዜጎች ተሳትፎ የዲሞክራሲያችን መሠረት እንደሆነ እና ተማሪዎቻችን አስፈላጊ መብታችን ነው ብለው ባመኑበት ጉዳይ ማቀንቀናቸውን MCPS ያከብራል ይደግፋልም። ይህ ድጋፍ በተብራራ ሁኔታ JFA-RA የተማሪ መብቶችና ግዴታዎች ላይ ተገልጿል፣እናም ስለ ትምህርት ቤቶች እና የማህበረሰብ ሠላምና ደህንነት ፌብሯሪ 26 በትምህርት ቦርድ የድጋፍ ውሳኔ ተሰጥቷል።

Parkland ላይ ህይወታቸውን ላጡት 17 ሰዎች መታሰቢያነት እና ስለ ት/ቤቶቻቸው ሰላምና ደህንነት በተመለከተ ፌብሯሪ 14 በርካታ ተማሪዎች አገር አቀፍ ት/ቤትን ጥሎ የመውጣት ተሳታፊ በመሆን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለማሰማት እና ለማቀንቀን እንደሚፈልጉ ይገባኛል። የተማሪዎችን አቀንቃኝነት ብንደግፍም፣ በዚህ የዜጎች እንቅስቃሴ ለመሳተፍ የሚመርጡ ተማሪዎች ስጋት በሌለበት እና ድጋፍ በሚደረግላቸው የትምህርት ቦታ ት/ቤት ውስጥ ቢያደርጉት ይመረጣል። ከ MCPS መሪዎች መመሪያ በማግኘት፣ የት/ቤት አስተዳዳሪዎች ከተማሪዎች መሪዎች ጋር ለማርች 14 ተማሪዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ደህንነታቸውና ሰላማቸው ስጋት በማይኖረው በት/ቤት ግቢ ሆነው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለማስደመጥ የሚያስችላቸውን ስልት ለማዘጋጀት አብረው እየሠሩ ናቸው። ተማሪዎች እነዚህን ሠላማዊ ትእይንቶች የሚመሩት በራሳቸው ተነሳሽነት ነው። ማንም ተማሪ አይገደድም ወይም ከመሳተፍ ተስፋ የማስቆረጥ ነገር አይደረግም።

እንዲሁም ደግሞ አንዳንድ ተማሪዎች ከት/ቤት ጥሎ በመውጣት ለመሳተፍ ሊወስኑ እንደሚችሉ በጥልቀት እገነዘባለሁ። ፌብሯሪ 22 ባስተላለፍኩት መልእክቴ እንዳካፈልኳችሁ፣ ት/ቤትን ጥሎ መውጣት የሌሎችን የመማር/ማስተማር ሁኔታ ከማደናቀፉም በላይ በተለይም እየጨመረ ባለው በት/ቤት የማስፈራራት ዛቻ ከባድ የደህንነት ስጋት ሊያስከትል ይችላል። ተማሪዎች በት/ቤት ክልል ጊቢ ውስጥ ካልሆኑ በስተቀር የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅና ለማረጋገጥ MCPS ሠራተኞች እና መገልገያዎች አይኖሩትም። ከተመደበው ሠዓት በፊት ያለፈቃድ የት/ቤት ህንፃ ጥለው ከወጡ ወይም የሚማሩበትን ክፍል ሠዓቱ ሳይደርስ አቋርጠው ቢወጡ ከት/ቤት ያልተፈቀደ መቅረት ተደርጎ እንደሚወሰድ ልጅዎ እንዲያውቀው/እንድታውቀው ከልጅዎ ጋር እንዲነጋገሩ እጠይቃለሁ። ያለፈቃድ ከት/ቤት መቅረት ምን ዓይነት ተጽእኖ እንደሚኖረው ስለ ተማሪዎች መብቶችና ግዴታዎችእና የተማሪ ስነምግባር ኮድላይ ኢንፎርሜሽን ይገኛል። ልጅዎ ያለፈቃድ ትምህርት ቤት ለቆ/ለቅቃ መሄዱን/መሄዷን አስተዳዳሪዎቹ ካወቁ፣ በተቻለ ፍጥነት እርስዎን ለማነጋገር ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

በተጨማሪም፣ ስለ Parkland አሰቃቂ ሁኔታ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያወቁ ቢሆንም ብዙ ቤተሰብ በኤለመንተሪ ዕድሜ ካሉት ልጆቻቸው ጋር በዚህ ጉዳይ እንዳልተነጋገሩበት እናውቃለን። በተለይም እነዚህን ጉዳዮች በሚመለከት የኤለመንተሪ ት/ቤቶች ከተማሪዎች ጋር ይህን በመሰለ ጉዳይ መነጋገር ወይም በተማሪዎች የሚመራውን የተደራጀ ትዕይንት እንዲሳተፉ አይደግፉም። ቢሆንም ግን፣ የት/ቤት ሠራተኞች እና መገልገያዎች/resources ስለ ት/ቤት ሰላምና ደህንነት ለመናገር ለሚፈልጉ በማናቸውም ደረጃ ያሉ ተማሪዎችን ለመደገፍ ዝግጁ ናቸው።

ስለነዚህ ጉዳዮች ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንዲነጋገሩ/እንዲወያዩ አደፋፍራለሁ። ተማሪዎች ሃሳባቸውን እና አመለካከታቸውን የመግለጽ እድል እንዲኖራቸው MCPS ለተማሪዎች ድጋፍ የመስጠት ቁርጠኝነት እንዳለው እባክዎ ይገንዘቡ።
ከአክብሮት ጋር
Jack R. Smith, Ph.D ዶር. ጃክ አር. ስሚት
Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ