Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: June 29, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

 

የሥርዓተ ትምህርት/ከሪኩለም ክለሳ

 

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፦

ለሰመር ጊዜዎ ጥሩ ጅማሬ እንደነበርዎ ተስፋ አደርጋለሁ። እምጽፍላችሁ ከK-8ኛ ክፍልስለ እንግሊዘኛ ቋንቋ ስነ-ጥበብ (ELA)ና ሂሳብ፣ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አልጄብራ 1 አዲሱ የትምህርት ስርዓት እና የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ግምገማ እና ምርጫን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለማቅረብ ነዉ። ባለፈው መልዕክቴ ላይ እንደጠቀስኩት፣ በ2018-2019 የትምህርት አመት መጀመሪያ ላይ የሥርዓተ-ትምህርት መረጣውን ሂደት ለመቀጠል እቅድ አለን። ይህን ጥረት እንደገና ለማስጀመር ስንዘጋጅ፣ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ የተከናወነውን የመጀመሪያዉን ደረጃ/ምእራፍ ሂደቱን ለማጥራት እና የተገኙ ቁልፍ ትምህርቶችን ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብረመልስ የመቀበል እና ግኑኝነቶችን ስናደርግ ቆይተናል።

ባለፈዉ ወር፣ሁሉንም የሰራተኛ ማህበራት፣ በመጀመሪያዉ ደረጃ/ምእራፍ ተካፋይ የነበረዉን የግምገማ ዋና ቡድን፣የስርአተ ትምህርቱ አማካሪ ጉባኤ፣ የማዕከላዊ የአገልግሎቶች ሠራተኞች፣እና ሌሎች የት/ቤት ሠራተኞችን በፕሮፖዛል የቀድሞዉ ጥያቄ (RFP) ላይ ዝርዝር ግብረ መልስ ለማግኘት ግንኙነት አድርገናል። በተጨማሪም የአዲስ ስርዓተ-ትምህርት ጥናት፣ ማለትም ከ 1,700 በላይ የሆኑ ወላጆች፣ መምህራን፣ እና ተማሪዎችን ጨምሮ  ከMCPS ማህበረሰብ አባላት የተገኘዉን ምላሽ ተንትነናል። በኦገስት 2018 መጨረሻ ዳግም እንዲታተም/እንዲወጣየታቀደውን RFP፣ ለመከለስይህንአስተያየት/ግብረመልስ እንጠቀማለን። የ RFP መዉጣትን/ህትመትን ተከትሎ፣ ሥርዓተ-ትምህርት ፕሮፖዛል በፎል 2018 መጨረሻ ላይ እንደሚገመገም የታሰበ ሲሆን፣በ 2018-19 የትምህርት ዓመት መካከል ለትምህርት ቦርድ አቅርቦ የማጽደቅ አማራጮችም እንደሚኖር ይጠበቃል።

በ 2018 ፎል መጨረሻ ላይ አዲሶቹን ቁሳቁሶች ለመገምገም በምንዘጋጅበት ወቅት፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ የMCPS ማህበረሰብ ሙሉ የተሳትፎ መንገዶች ላይ ለመወያየት ከተጨማሪ የባለ ድርሻ አካላት ቡድኖች ጋር እንገናኛለን።  ስለ የመጨረሻ የስርዓተ-ትምህርት ቁሳቁሶች ምርጫ፤ የዚህ ተነሳሽነት ጊዜ እና ተፅእኖ፤ የባለሙያ ትምህርት ንድፎች፤እና አዳዲስ ቁሳቁሶችን ለትምህርት ቤቶች እና ለመማሪያ ክፍሎች የማሰማራት/የማድረስ አቀራረቦችን በተመለከተ ከመምህራን፣ከአስተዳዳሪዎች፣ከወላጆች፣እና ከማህበረሰቡ ጋር ትብብርን ያካትታል። ይህ ግብረመልስ የቦርድ ማፅደቁን ተከትሎ እና ወደ 2019-20 የትምህርት አመት ስንቃረብ አንድ የተወሰነ የአፈፃፀም እቅድ እና የጊዜ ገደብ ለማዘጋጀት ያገለግላል። በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ ከእርስዎ ጋር ዘወትር በመደበኛነት እንገናኛለን።  ለኢንፎርሜሽን እና ወቅታዊ መረጃዎች የስርዓተ ትምህርት ግምገም ድረገፅን እንዲጎበኙ አበረታታዎታለሁ።

በመሰጠት በታታሪነት ለተማሪዎቻችን ላበረከቱት ስራ እያመሰገንኩ ቀጣይ ትብብራችንን በጉጉት እጠብቀዋለሁ።
ከሰላምታጋር፣

ዶ/ር.ማሪያ ቪ. ናቫሮ Maria V. Navarro Ed.D.
የኣካዴሚ ዋና መኰንን Chief Academic Officer
የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)