Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 18, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በርካታ ተማሪዎቻችን ባስመዘገቧቸው ከፍተኛ ደረጃ ውጤቶች በአካባቢም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ዝናን አትርፏል። ነገር ግን ብዙ የሚለው በቂ አይደለም። የእኛ ቁርጠኝነት ለሁሉም ነው። ጥቂት/አንዳንድ ተማሪዎቻችን ያላቸውን ያክል የመማር አቅም ሙሉ በሙሉ እንዳልተጠቀሙበት እናውቃለን። ሁሉንም ተማሪዎች በኮሌጅ፣ በሥራ መስክ እና በማህበረሰብ ስኬታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ለትምህርት የሚያስፈልጓቸው መገልገያዎችና መጠቀሚያዎች፣ መመሪያ፣ የማግኘት እድል የመስጠት ኃላፊነት አለብን። ተማሪዎቻችን ስኬታማ እንዲሆኑ የምናስችልበት አንዱ መንገድ ሁሉም ተማሪዎች የላቸውን የመማር ችሎታ አሟጠው እንዲጠቀሙ ለማመቻቸት ሥርዓተ ትምህርቱን ማበልጸግና ለመምህራን የሙያ እድገት እንዲያገኙ በማስቻል ነው።

እንዴት ወደዚህ ግብ ለመድረስ እንደምንችል ለማወቅ እንዲረዳን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሥርዓተ ትምህርታችንን ክለሳ ለማድረግ ከሙዓለህፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ እንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበብ እና ሂሳብ (English Language Arts (ELA) and mathematics) እየተሠራ ነው። ክለሳው በመቶዎች የሚቆጠሩ የትምህርት ባለሙያዎች ሥርዓተ ትምህርቱን መርምረው/ተመልክተው፣ በክፍል ከተገኙ ተሞክሮዎችና ከተማሪዎች አድራጎት ቁልፍ የሆኑ በርካታ ግንዛቤዎችን/ድምዳሜዎችን አግኝተዋል።

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሥርዓተ ትምህርት በ 2008-2009 በተዘጋጀበት ወቅት ጣራ ላይ የነበረ ቢሆንም፣ ከቅርብ ዓመታ ወዲህ የሥርዓተ ትምህርት/ካሪኩለም እድገቶች የዲጂታል አሠራር ግኝቶችን፣ ይበልጥ ብቁነትን እና ከስቴት መስፈርት ጋር የተሻለ መጣጣምን አስከትሏል/ጨምሯል።
  • ሙያዊ ትምህርት በስኬታማነት ለማስተማር፣ በተለይም በአዲስ መስፈርት እና ሥርዓተ ትምህርት መሠረታዊ ማረጋገጫ ነው።
  • የሥርዓተ ትምህርት እና የሙያ ትምህርት ስኬታማ ሽግግርን ለማረጋገጥ ብዙ-ዘመን፣ ብዙ-የትኩረት ጫፍ ለመድረስ የሚደረግ ጥረት ይጠይቃል።

እነዚህን ለማጠቃለል እያሰብን ሳለ ሁሉንም ተማሪዎች ባቀፈ መልኩ ወደ ግባችን እንድንደርስ ሥርዓተ ትምህርታችንና የሙያ ማዳበር/እድገት አስፈላጊ መሆኑን ይህ ሪፖርት ያረጋግጥልናል።

እንደምታውቁት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኤፕሪል ላይ አዲስ ካሪኩለም/የሥርዓተ ትምህርት እቅድ የመምረጥ ሒደት ላይ ገብቶ ነበር። የተመረጠው ካሪኩለም/ሥርዓተ ትምህርት ፎል ላይ በአነስተኛ ቁጥር የናሙና ት/ቤቶች እንደሚተገበር በቀጣዮቹ ዓመታትም ትግበራው በሌሎች ት/ቤቶች እየቀጠለ እንደሚሄድ ነው። በተመረጠው አካሄድ ያልተጠበቁ ክስተቶችን መፍትሔ እስከምናገኝ ይህንን እቅዳችንን በጊዜያዊነት ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ በቅርቡ ወስነናል። አሁን ያለው RFP ይሰረዝና በአዲስ ይተካል። በዚህ አስፈላጊ ጥረት ላይ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ሙሉ ተሳትፎ ለማረጋገጥ የአመራረጡን ሒደት በአዲሱ የትምህርት ዓመት ለመጀመር አስበናል። በመጪው የትምህርት ዓመት ለመጀመር የታቀደውን ይህ አሠራር ለትምህርት ቤቶቻችን አንዳንድ መስተጓጎሎችን እንደሚያስከትል ብናውቅም የዚህ መዘግየት ስለሒደቱ የበለጠ ግልጽነትንና መተማመንን ይፈጥራል የሚል እምነት አለን። መዘግየቱ ከባለድርሻ አካላት የሽግግር ጊዜን አስመልክቶ ያገኘናቸውን ግብረመልሶች/feedback ለመተግበርም እድል ይሰጠናል።

አዲስ ሥርዓተ ትምህርት/ካሪኩለም ማግኘቱ የዘገየ ቢሆንም በካሪኩለም ክለሳው ወቅት የተነሱ ስጋቶችን ምላሽ ለመስጠት/ለማስተካከል ለሠራተኞች የሙያ ማበልፀጊያ ማበረታቻ መስጠታችንን እንቀጥላለን። እነኚህ ትኩረቶች የሚያካትቱት በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ሁሉንም ተማሪዎች ለመደገፍ/ለመርዳት የሚያስችሉ የማስተማር ስልቶችን፣ ይበልጥ ውስብስብ በሆኑ ትምህርቶች ላይ የበርካታ/ከፍተኛ የተማሪዎችን ተሳትፎ፣ እና በሂሳብ ትምህርት ላይ ጥልቅ የሆነ መረዳትን እና በክፍል ደረጃ የሚመጥን ችሎታ ማጎልበት ላይ ይሆናል።

ለጠቅላላ ተማሪዎቻችን እና ለት/ቤቶቻችን ስለምታደርጉት የማያወላውል ድጋፍ አመሰግናችኋለሁ። በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራትም ስለካሪኩለም/ሥርዓተ ትምህርት እና ለአስተማሪዎቻችን የሙያ ብቃት ማዳበር ስለምናደርገው ጥረት የደረስንበትን ደረጃ ለማሳወቅ ከእናንተ ጋር የተለመደ ግንኙነታችንን እንቀጥላለን።

በአክብሮት
Maria V. Navarro, Ed.D.
Chief Academic Officer