Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: July 5, 2016

elementary students on playground

መልእክት ከSuperintendent Jack R. Smith

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፣

አዲሱ የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪያችሁ በመሆን ዛሬ ስፅፍላችሁ ደስታ ይሰማኛል። እጅግ በጣም ከተከበሩት የሀገሪቱ የት/ቤት ሰርአቶች አንዱ የሆነውን Montgomery County Public Schools (MCPS)ን ለመምራት ደስተኛ ነኝ ምስጋናም ይሰማኛል።

ቀደም ብለው በነበሩት በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምርያ የት/ቤቶች የስቴት የበላይ ተቆጣጣሪና ተጠባባቂ የስቴት ተቆጣጣሪ ሚናዎቼ፣ በሜሪላንድ ውስጥ ስለሚገኙ 24 የት/ቤት ስርአቶች ስለእያንዳንዳቸው ብዙ ተምሬአለሁ። ስለ Montgomery County ጎላ ብለው ይታዩኝ የነበሩት ግዙፍነቱ፣ ሚዛኑ፣ እና የስኬት ደረጃው ነበሩ። ከ500 ስኩዌር ማይሎች በላይ ከ157,000 ተማሪዎች በላይ ጋር እየሸፈነ፣ MCPS እጅግ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ውጤት ፀንቶ ያፈራል። ይህ ስኬት የመነጨው፣ ባብዛኛው፣ በየክፍሉና በየደረጃው የተማሪን ግኝት ለማረጋገጥ በተማጠኑ ከፍተኛ ተሰጥኦ ባላቸው ሰራተኞች፣ አስተዳዳሪዎች፣ እና ድርጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች አማካይነት ነው።

Superintendent Jack Smith on the Pony Truck

ባለፉት ጥቂት ሳምንቶች፣ የኛ ፖኒ ሲስተም ተብለው በሚጠሩት—ጥዋት የፖስታ መስመሮች በመጓዝ ስለ ት/ቤቱ ስርአት በገዛ ራሴ የመማር ልዩ መብት ነበረኝ። የፖኒ የጭነት መኪና ሾፌሮች ኒክ ሬጋልያ፣ ስታን ጃክሰን፣ እና ጊዴዎን ዱሊን ወደ ት/በቶቻችንና የት/ቤት መገልገያዎች መልእክቶች ለማሰራጭት ካውንቲውን ከዳር እስከዳር ሲዳስሱ፣ ክነሱ ጋር እንድቀላቀል በጎ-ፈቃደኞች ነበሩ። እስከዛሬ፣ በቅርብ ጊዜ 204 ከሚደርሱት ት/ቤቶች ውስጥ ከ110 በላይ ይሆኑትን ጎብኝቻለሁ እናም ወሩ ከማለቁ በፊት ሁሉንም ለማየት ተስፋ አደርጋለሁ። ከጎበኝኋቸው ት/ቤቶች፣ ልንግራችሁ የምችለው እያንዳንዱ ጉልህና ልዩ መሆኑን፣ ነገር ግን—ልክ እንደተማሪዎቻችን—በጋራ ክር አንድላይ የተያያዙ መሆናቸውን ነው።

በየቀኑ ወደ እያንዳንዱ የመማርያ ክፍል እያንዳንዱ/ዷ ተማሪ የራሱ(ሷ)ን ልዩ የተሞክሮ ክምችትና ሀሳብ/ፍላጎት ይዞ/ዛ ይመጣል/ትመጣለች እናም የት/ቤት ስርአት እንደመሆናችን በመስረተትምህርት፣ ፅሁፍ፣ እና በሂሳብ ክሂሎቶች የጋራ ክር እንድ እንድናደርጋቸው እና ስክሌታማ የመሆን እድል እና በህይወታቸው የፈለጉትን መንገድ እንዲከተሉ አማራጮች የመስጠት ሀላፊነት አለብን።

ይህ ክር፣ ዘር፣ ትውልድ፣ ፆታ፣ የተወሰነ የእንግሊዘኛ ችሎታ፣ ማህበራዊ-ኤኮኖሚያዊ ይዘት፣ ወይም ስንክልና የፈለገውን ይሁን፣ ሁሉም ተማሪዎቻችን ጋ መድረስ አለበት። የተማሪዎቻችን ግኝቶችን በሚመለከት MCPS የተመሰገነ ቢሆንም፣ ወደ ውጤቶች መዛባት የሚያመራ የእድል ክፍተት አሁንም አለ። ይህን ፈተና ፊት ለፊት ለመጋጠም በአቅሜ ውስጥ በሚገኙ በሁሉም መገልገያዎች ለመጠቀም አላማ አለኝ።

Middle School students in class

በመምህርነት፣ ርእሰመምህርነት፣ እና የበላይ ተቆጣጣሪነት የተሞክሮ አስሮች አመታት በመምህርነት ስኬታማ ለምሆን የሳይንስ፣ ኪነጥበብ፣ እና የልብ መቀየጥ ይጠይቃል። ሳይንሱ የማስተማር እድገት ምርምርን ተግባራዊ ማድረግ እና የተማሪን አፈፃፀም ለመከታተል አሀዞችን መተንተን ነው። ኪነጥበቡ፣ አንድን የሙዚቃ ጓድ እንደመምራት፣ ተማሪዎች በተቻላቸው ልቀት እንዲፈፅሙና ወደ ኋላ የቀሩ ወይም መስመር የሳቱትን ለማገዝ ተማሪዎችን የመቀስቀስ ችሎታ ነው። ልቡ፣ መምህር ለተማሪ፣ ተማሪ ለመምህር፣ እና ተማሪ ለተማሪ ሁሉም ደህንነት፣ ተቀባይነት፣ እና መከባበር እንዲሰማቸው ለማስቻል የምንገነባቸው ግንኙነቶች ናቸው። እነዚህ ንጥረነገሮች፣ አንድ ላይ፣ ተማሪዎቻችን በት/ቤቶቻችን ለመበልፀግ እድል እንዲኖራቸው ያረጋግጣሉ።

ለዚህ ታላቅ ሀላፊነት አደራ በመሰጠቴ ክብር ይሰማኛል። በሚመጡት ጥቂት ወራት ወደ ማህበረሰብ በመውጣት ወላጆቻችንና ሰራተኞቻችንን በመገናኘት ስለ አስገራሚው የት/ቤት ስርአታችን ይበልጥ እማራለሁ። በሚመጡት ወራት እና አመታት ከዚህ ግሩም ሰራተኛና ማህበረሰብ ጋር አብሬ ለመስራት ተስፋ አደርጋለሁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር

Dr. Jack R. Smith/ ዶር. ጃክ አር. ስሚዝ
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ

ማሳሰብያ፡- ባለፉት ወራት ከመሪዎችና የማህበረሰብ አባላት ጋር ስገናኝ ነበር፣ በኔ ቦታ ቢሆኑ ምን ምን ላይ እንደሚያተኩሩ ጠይቄአቸው ነበር። ከናንተም መስማት እፈልጋለሁ። መልስ ለመስጠት፣ እዚህ ላይ ጠቅ አድርጉ.

  Share Your Ideas