Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: February 08, 2017

ቀጣይ ጥረታችን ለሰላማዊና ኣስተናጋጅ ት/ቤቶች

የተከበራችሁ የ MCPS ቤተሰቦች፦

Montgomery County Public Schools (MCPS) ለሁሉም ተማሪዎች ሰላማዊና ኣስተናጋጅ የመማርያ ኣካባቢ ለማቅረብ ግዴታ ገብቷል።  ይህን ግዴታ ለማሟላት ከመናደርጋቸው ቀጣይ ጥረቶች ኣንፃር፣ ለሁሉም ወላጆችና ኣሳዳጊዎች በት/ቤቶች ማሸማቀቅና ወከባን ለመከላከል የሚያግዙንን መገልገያዎች ልናበረክትላቸው እንፈልጋለን።  መገልገያዎቹ በድርጣቢያችን በhttp://www.montgomeryschoolsmd.org/info/bullying/ ሊደረስባቸው ይቻላል።

በተጨማሪ፣ የማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት መመዝገቢያ ፎርም ቅጂ ከልጃችሁ ሪፖርት ካርድ ጋር ኣያይዘናል።  ትኩረት ኣድርገን ለተማሪዎች እምቅ ችሎታቸውን እዲደርሱበትና በኮሌጅና በስራዎቻቸው ስኬታማ እዲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን እውቀት፣ ክሂሎቶች፣ ተሞክሮዎች፣ እና እድሎች ለመስጠት እንድንችል MCPS በያንዳንዱ ት/ቤት ሰላማዊ የመማርያ እካባቢ ለማቅረብ ግዴታ ገብቷል።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
የMCPS የተማሪና የቤተሰብ ድጋፍና ተሳትፎ ፅ/ቤት