Skip to main content Skip to footer site map

የMCPS ጎረቤት ለጎረቤት

የMCPS የስራ ማስኬጃ በጀት መመሪያ (ቱል ኪት)

logo

ደረጃ 1


አንድ ቡድን አሰባስቡና ቦታ ምረጡ

የጎረቤት ለጎረቤት ውይይትን ለማስተናገድ እያንዳንዱ ሰው ተጋብዟል። በPTA ስብሰባ ጊዜ፤ መደበኛ ባልሆነ የምሳ ላይ ስብሰባ (brown bag lunch)፤ በአካባቢ በሚገኝ ቢዝነስ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ፤ ወይም በጎረቤት ወይም በቤተሰብ አባል ቤት ሊካሄድ ይችላል። የቡድኑ መጠን እንደ ጋባዡ (አስተናጋጁ) ይወሰናል፣ ነገር ግን እየንዳንዱ/ዷ ለመሳተፍ እድል ማግኘት እንደሚችል/ምትችል አረጋግጡ።

ተሳታፊዎች በጀት 101ን (The Budget 101) እና የዚህ መመሪያ (ቱል ኪት) አካል የሆኑትን የኦን ላይን የበጀት ሰነዶችን በድረ-ገጽ ላይ መመልከት እንዲችሉ፣ ቦታ ስትመርጡ ኢንተርኔት ያለው ቢሆን ይመረጣል። የተዘጋጀ የኢንተርኔት ገጽ/ሳይት ካልተገኘ፣ መረጃውን አስቀድማችሁ አትማችሁ ቅጅዎችን አዘጋጁ።

ደረጃ 2

የበጀት 101 (The Budget 101) ድረ-ገጽን ጎብኙ እና ሰነዶችን መርምሩ

በጀት 101 (The Budget 101) ድረ-ገጽ  በMCPS የሥራ ማስኬጃ በጀት ውስጥ ምን እንደተካተተ አጠቃላይ ግንዛቤ ይሰጣችኋል። ቪዲዮ ያካተተው ገጹ፣ ፈንድ ከየት እንደሚገኝ፣ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል፣ እና የእያንዳንዱ/ዷን ተማሪ ፍላጎት ማሟላታችንን ለማረጋገጥ አንዴት ት/ቤቶችን በተናጠል በሰራተኛ እንዲሟሉ እንደምናደርግ ያሳያችኋል። ለውይይታችሁ የበጀት 101 (The Budget 101) ድረ-ገጽ፣ እታች ስለ ቀረበው የ2017 በጀት አመት (FY) የሥራ ማስኬጃ በጀት ከሚገኘው መረጃ ጋር በመሆን፣ መሰረት መስጠት ይኖርበታል። ከበጀት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ቢኖራችሁ፣ ለpio@mcpsmd.org ኢ-ሜይል አድርጉ እና እኛ በተቻለ ፍጥነት መልስ እንድታገኙ እንጥራለን።

 

የበጀት መገልገያዎች

·         የ2017 በጀት አመት የሥራ ማስኬጃ በጀት ድረ-ገጽ FY 2017 Operating Budget website

·         ስለ ቀረበው የ2017 በጀት አመት የሥራ ማስኬጃ በጀት ፈጣን እውነታዎች

·         በበላይ ተቆጣጣሪው የቀረበው የ2017 በጀት አመት የሥራ ማስኬጃ በጀት በአጭሩ

·         በበላይ ተቆጣጣሪው የቀረበ የ2017 በጀት አመት የሥራ ማስኬጃ በጀት

ጠቃሚ የኢንተርነት መገናኛዎች

·         የMCPS ጨረፍታ ስእል

·         የMCPS ስልታዊ ተቀዳሚዎች/MCPS Strategic Priorities

·         MCPS የድስትርክት የአፈጻጸም ዕቅድ/MCPS District Implementation Plan

ደረጃ 3

ውይይታችሁን አድርጉ

ውይይታችሁን የምትጀምሩበት ሰአቱ አሁን ነው። ውይይቱን ለማስጀመር እታች ትንሽ ጥያቄዎች ይገኛሉ ነገር ግን ይህ የጎረቤት ለጎረቤት (Neighbor to Neighbor) ውይይት ለእናንተ እና በቡድናችሁ ውስጥ ለሚገኙት በጣም አንገብጋቢ በሆኑ በበጀት ዙሪያዎች ላይ ትኩረቱን ማድረግ አለበት። የውይይት መሪና ማስታወሻ የሚይዝ መመደባችሁን አረጋግጡ፣ ከMCPS ማህበረሰብ ጋር ለመጋራት የተወሰኑ ፎቶዎችም ተነሱ።

የውይይት መነሻ ጥያቄዎች:-

·         ባለ/በተገኘ ውስን በሆነ ፈንድ፣ MCPS ማዋል/መጠቀም የሚኖርበት በጣም ጠቃሚ ጉዳዮች ብላችሁ የምታምኑት ምንድን ናቸው?

·         ከ2008 ጀምሮ፣ በውስን ሀብቶች የተነሳ ለMCPS ት/ቤቶች የሚደረጉ የበጀት ጭማሪዎች ዝቅተኛ ነበሩ። እነዚህ አስቸጋሪ የበጀት አመቶች በእኛ ት/ቤቶች እና ተማሪዎቻችን ላይ እንዴት ተጽእኖ አድርገውባቸዋል?

·         ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ከእኛ ተመራጭ መኮንኖች ጋር የMCPS በጀትን ፈንድ የማድረግ ጠቀሜታን በተመለከተ አስተያየታቸውን መለዋወጥ የሚችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

ደረጃ 4

ሃሳበችሁን አካፍሉ።

እባካችሁን የየራሳችሁን ማስታወሻዎች እና ልትለዋወጧቸው የምትፈልጓቸውን ማንኛቸውንም ፎቶዎችለpio@mcpsmd.org  ኢ-ሜይል አድርጉ። በቡድናችሁ ያሉትን የእያንዳንዱን ስም መስጠት/መላክ አያስፈልጋችሁም፣ ነገር ግን ለአዘጋጁ/ጇ (ጋባዡ/ዋ) ስም እና የሚገኙበትን መረጃ መስጠት ጠቃሚ ነው።  እባካችሁን በማስታወሻዎቻችሁ ላይ የማንንም ልጅ ስም አትጥቀሱ።

ሁሉንም ማስታወሻዎች ከትምህርት ቦርድ እና ከበላይ ተቆጣጣሪው ጋር እንለዋወጣለን። ፎቶዎቹ ጎረቤት ለጎረቤት (Neighbor to Neighbor) ድረ ገጽ እና በሌሎች የMCPS መገልገያዎች ላይ ሊለጠፉ ይችላሉ።

ጥያቄ አለ?

ስለ ጎረቤት ለጎረቤት (Neighbor to Neighbor) ጥያቄ ካላችሁ፣ ለሕዝብ መረጃ እና የድህረ-ገጽ አገልግሎቶች መምሪያ (Department of Public Information and Web Services) በ(301) 279-3853 ደውሉ ወይም በpio@mcpsmd.org ኢ-ሜይል አድርጉ

 

Click here to log in