student smiling
student smiling

ለእንጊሊዘኛ ቋንቋ ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው

ልጄ የእንጊሊዘኛ ቋንቋን ለመማር የተለዩ ክፍሎችን መከታተል ይኖርበት ይሆን?

በዩናይትድ ስቴት የተወለዱ ወይም ላለፉት ሁለት አመታት በሌላ ሀገር ትምህርቶችን ያልተከታትሉ ተማሪዎች በአቅሪያባቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች የመመዝገብ ሂደቱን መጀመር ይችላሉ (የመመዝገቢያ ማስታወቂያውን፣ ከታች ይመልከቱ)። ሌሎች ተማሪዎች በRocking Horse Road Center በሚገኘው ሪዝደንሲና አለም አቀፍ ምዝገባዎች (Residency and International Admissions) የመመዝገብ ሂደቱን ይጀምሩ። ስለ ተማሪው የቤት ውስጥ ቋንቋ ወላጆች በሰጡት መረጃ መሰረት፣ የMontgomery County Public Schools (MCPS) የስቴት ውስጥ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቃት መመዘኛ መስጠት በህግ ይጠበቅበት ይሆናል። በሪዝደንሲና አለም አቀፍ ምዝገባዎች መመዝገብ ለጀመሩ ተማሪዎች፣ ይህ ፈተና የሚሰጠው በእንግሊዘኛ ለሌላ ቋንቋዎች ለሚናገሩ (English for Speakers of Other Languages, ESOL) የፈተናና ግብ ማዕከል ነው። የተቀሩት ተማሪዎች የሚፈተኑት በአዲሱ ትምህርት ቤታቸው ነው። የፈተናው ውጤት መሰፈርት ለማሟላትና ለተፅእኖ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እድገት ፕሮግራም መመደብን ይወስናል። እነዚህ ፕሮግራሞች የተነደፉት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ለማጆች መደበኛውን የአሜሪካ እንግሊዘኛና በMCPS ካሪኩለም ውስጥ ያሉትን ሌሎች የትምህርት አይነቶችን በግስጋሴ መቻልን ለመርዳት ነው።

ለበለጠ መረጃ 

የመመዝገቢያ ማስታወቂያ፦የሀይስኩልተማሪዎችሆነውአዲስየሆኑለሰሜንምስራቅኮንሶርቲያምርጫናማመልከቻፕሮግራምአገልግሎቶች (Northeast Consortia Choice and Application Program Services)ወይምለዳውንካውንቲኮንሰርቲየም (Downcounty Consortium)የመመዝገቢያሂደታቸውንለኮንሰርቲየምክፍል፣ምርጫ፣እናማመልከቻፕሮግራምአገልግሎቶች(Division of Consortium, Choice, and Application Program Services, DCCAPS), በስልክቁጥር301-592-2040በመደወልይጀምራሉ። 

top

እንዴት ነው ልጄ የእንጊሊዘኛ ቋንቋን የሚማረውና በሌሎች የትምህርት አይነቶች በቀጣይነት መሻሻል የሚያሳየው?

የDivision of English for Speakers of Other Languages/Bilingual Programs (ESOL) የአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛና 2ኛ ደረጃ ትም/ቤትች የአንግሊዘኛ ለማጆች ለትምህርታቸው ስኬት ወሳኝ የሆነውን የትምህርት ቤት አንግሊዘኛ እንዲያገኙ ለመርዳት ጥብቅ የሆነ ስርአተ ትምህርቶች አዘጋጅቷል። ሁሉም የESOL ስርአተ ትምህርት መገልገያዎች በንባብ/ቋንቋ ስነ ጥበባት፣ በማህበራዊ ጥናቶች፣ እና በሳይንስ ስኬት እስፈላጊ በሆኑ የእካዴሚ ቋንቋ ዙርያ ነው የተቀናጁት። የESOL ትምህርት የሚከናወነው ከትምህርት ቀን በከፊል ሲሆን በተማሪው መደበኛ የትምህርት ፕሮግራም ላይ ተጨማሪ ሆኖ ነው።

የESOL ስረአተ ትምህርት የተመሰረተው ደግሞ በጥናት በተደገፉ በትምህርት ይዞታ ውስጥ ቋንቋን መማርን ለመደገፍ ነው። ስረአተ ትምህርቱ በአራት የንባብ፣ የመፃፍ፣ የማዳመጥና የመናገር ችሎታዎች ላይ የቋንቋ እድገት ለማምጣት በባህልና ቋንቋ ቅይጥ ለሆኑ ተማሪዎች ልዩ ሆነው የተነደፉ ዘዴዎችን መጠቀም ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል። ተማሪዎች ከአዋቂዎችና እኩያዎቻቸው ጋር እንዲግባቡ፣ ተግባራዊ የሆነ የመማር ልምዶችና ወሳኝ የሆነ ማሰብን የሚያበረታቱ እንቅስቃሴዎችን እንዲለማመዱና በትምህርታዊ ቋንቋ ላይ ተግባራዊ እንዲያደርጉት እድሎች ተሰጥትዋቸዋል።

top

በሰመር እረፍት ወቅት የእንግሊዘኛ ቋንቋን ለመማር እድሎች አሉ ወይ?

በአንደኛ ደረጃና ሀይ ስኩል ሰመር ትምህርት ማዕከሎች ጠለቅ ያለ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክፍሎች በጀማሪ ደረጃ ለESOL ተማሪዎች ይሰጣሉ። የአንደኛ ደረጃ ክፍሎች አራት ሳምንቶችና ሀይ ስኩል ክፍሎች ስድስት ሳምንቶች ናቸው። የመናገር ችሎታዎች ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት የሚያገኝ ሲሆን፣ ሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ቮካቡላሪና ስትራክቸር (Vocabulary and Structure) እነሱም ከእድሜያቸው፣ ብስለታቸውና የክፍል ደረጃቸው ጋር የተመጣጠነ ሁኔታዎች ላይ መለማመድን ይማራሉ።

top

በማስተማሪያ ቋንቋ ለውጥ፣ የትምህርት ቤት ባህልና አዲስ ሀገር በመኖር የሚመጡ ጭንቀቶችን ለመቋቋም ምን አይነት እርዳታ ልጄ ያገኛል?

የESOL ካውንስሊንግ ቡድን የብዙ ቋንቋ የማማከር አገልግሎቶች ለESOL ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው ይሰጣል። ሰለ ልጅዎ በMCPS ወይም በዩናይትድ ስቴት መላመድን በተመለከተ ጭንቀት ካለብዎት፣ የልጅዎ ትምህርት ቤት ሰራተኞችን ያናግሩ። የትምህርት ቤቱ ሰራተኛ ከልጅዎና ከልጅዎ አስተማሪዎች ጋር የሚወራ የESOL አማካሪ ያገኝልዎታል። የESOL አማካሪዎች በሚከተሉት ዝርዝር ሁኔታዎች ዙሪያ ያሉ ማናቸውንም ጭንቀቶችን ያስተናግዳሉ፦

  • የESOL ተማሪዎች ባህላዊ፣ ማህበራዊና ስሜታዊ መላመድ በMCPS
  • የመቋቋም ችሎታዎች
  • ቀውስ መፍታት
  • በባህል መካከል አለመግባባቶች ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን ከመፍታት ጋር የተያያዘ
  • ውሳኔ የመወሰን ችሎታዎች
  • ትምህርታዊ፣ ባህላዊና የሙያ አማራጭ በMCPSና ከዚያም ባሻገር
  • የሙያና የተግባር ሙያ ምክር

  

top

በማስተማሪያ ቋንቋ ለውጥ፣ የትምህርት ቤት ባህልና አዲስ ሀገር በመኖር የሚመጣ ጭንቀቶችን ለመቋቋም ምን አይነት እርዳታ ወላጆች ያገኛሉ?

የESOL የወላጅ አውትሪች (Outreach) ቡድን የESOL ተማሪዎች ወላጅ ማህበረሰብ ውስጥ በMCPS ትምህርት ፕሮግራዎች በሙሉ መሳተፍ እንዲችሉ የቡዙ ቋንቋዎች አውትሪች አገልግሎቶች ይሰታል። ቡድኑ ተከታታይ የሆነ አገልግሎቶች ለወላጅ ቡድኖች ይሰጣል፣ ነረር ግን በግልዎና ለብቻዎ ሊረድዎም ይችላሉ። ስለልጅዎ ፕሮግራም ወይም በቤት ውስጥ ለልጅዎ መማር እርስዎ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጥያቄዎች ቢኖርዎ፣ የልጅዎን ትምህርት ቤት ሰራተኞች ያነጋግሩ። የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች ለጥያቄዎችዎ መልስ እንዲሰጥና ከርስዎ ጋር በመስራት ጭንቀትዎን እንዲፈታ ከESOL ወላጅ አውትሪች ቡድን አንድ አባል ያገኝልዎታል። የESOL ወላጅ አውትሪች ቡድን አባል በሚከተሉት ዝርዝር ሁኔታዎች ዙሪያ ያሉ ማናቸውንም ጭንቀቶችን ያስተናግዳሉ፦

  • በትምህርት ቤቶችና በአለም አቀፍ ወላጆች መካከል መገናኘትን።
  • በትምህርት አስተዳደር ቡድን (Educational Management Team)፣ የግል ትምህርት ፕሮግራም (Individualized Education Program)ና የእንግሊዘኛ ቋንቋ ለማጆች (English Language Learner) ቡድን ስብሰባዎች ወቅት ወላጆች ስብሰባዎቹን እንዲረዱና በሂደቶቹ ውስጥ በአግባቡ እንዲያልፉ መርዳት።
  • አለም አቀፍ ወላጆችን በተማሪዎችና ወላጆች መብቶችና ግዴታዎች፣ ልዩ የትምህርት አገልግሎቶች፣ የወላጆች ኮንፈረንስ፣ የወላጅ ተሳትፎ፣ እና የመረጃና መጠቆም አገልግሎቶችና በMCPSና በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሀብቶችን በተመለከተ መርዳት።

top

የእንግሊዘኛ ቋንቋን በደንብ መናገር ባልችል ምን አይነት አርዳታ አገኛለሁ?

የልጅዎን ትምህርት ቤት ወይም ለማናቸውም የMCPS ቢሮ ለመደወል ወይም ለመጎብኘት በፍፁም አያመንቱ። አንድም ሰራተኛ የርስዎን ቋንቋ መናገር ባይችል፣ መማር የሚኖርብዎ እንግሊዘኛ ቢኖር የራስዎን ቋንቋ መለየት እንዲያስችል፡- "I speak Amharic," "I speak Tigrinya," "I speak Cantonese," "I speak Kono," "I speak…" ማለት ብቻ ነው። ማናቸውም የMCPS ትምህርት ቤትና ቢሮ የስልክ ትርጉም አገልግሎት ማግኘት ይችላል። እርስዎ እየጠበቁ፣ እነሱ የሚረዳዎ አስተርጉዋሚ ማግኘት ይችላሉ። በልጅዎ ትምህርት ጉዳይ ላይ ሙሉ ለሙሉ መሳተፍ እንዲችሉ ትምህርት ቤቶቹ ለወሳኝ ሰነዶች ተርጓሚና ለስብሰባዎች አስተርጓዋሚዎች በMCPS የቋንቋ እርዳታ አገልግሎቶች ክፍል በኩል ያገኙልዎታል።

top

Montgomery County Public Schools

Contact MCPS

Call: 301-309-6277 | Spanish Hotline: 301-230-3073
E-mail: ASKMCPS@mcpsmd.org

Contact Employee & Retiree Services Center

Call: 301-517-8100 | E-mail: ersc@mcpsmd.org

©1995–2018 Montgomery County Public Schools, 850 Hungerford Drive, Rockville, Maryland 20850

Click here to log in